Wednesday, 31 August 2016

ሠላምን ለማስፈን…!




አባ  መላኩ
የኢትዮጵያ  መንግሥት ከአገር ውስጥ አልፎ በአፍሪካ ቀንድ አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን  ያላሳለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል። በተለይ ደግሞ ድብቅ አጀንዳ አንግበው በአገሪቱ ሰላምን ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኞችን በመከታተልና በቁጥጥር ስር በማዋል ረገድ ቀላል የማይባል ተግባር እያከናወነ ይገኛል።
ሽብርተኝነት ንጹሃን ዜጎችን ዒላማ ያደረገ ኃላፊነት በማይሰማቸውና ፈጽሞ ሰብዓዊ ርህራሄ ባለፈጠረባቸው አሸባሪዎች የሚፈጸም አስከፊ የወንጀል ድርጊት ነው። መንግስት ንጹሃን ዜጎችን ዓላማ እያደረገ የሚሰነዘር የሽብር ጥቃትን በመከላከል ዜጎች ያለምንም ስጋት በፈለጉት  ጊዜና ቦታ ተንቀሳቅሰው እንዲሰሩ አስተማማኝ ከለላ በአስተማማኝ መልክ እየሰጠ እንደሆነ ያደባባይ ምስጢር ነው።
በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን  የዓለም  ስጋት ከሆነ ዓመታት አስቆጥሯል።  የዚሁ አስከፊ ወንጀል ሰለባ የሆኑ የዓለማችን ዜጎች ቁጥር ቀላል አይደለም።  በርካቶችም ለአካለ ጎዶሎነት ዳርጓል። በቢሊየኖች የሚገመት   የሕዝቦች ሀብትና ንብረትም  ወድሟል።

በምስራቅ አፍሪካ ቀንድ ሽብርተኝነትና የባሕር ላይ ውንብድና ከፍተኛ መሰናክል መሆን ከጀመሩ ዓመታት አልፈዋል። ሶማሊያ በሽብርተኞችና በባሕር ላይ ወንበዴዎች በተደጋጋሚ ከተጎዱ አገራት መካከል በቀዳሚነት የሚትጠቀስ አገር ነች።  የአገሪቱ ሰላም ለሁለት አስርት ዓመታት ደፍርሷል ሕዝቦቿም  ለሞት፣ ስቃይና ለስደት ተዳርገው ዓመታትን መዝለቅ የግድ ሆኖባቸዋል።
ሶማሊያዊያን በእንዚህ አሸባሪዎች ምክንያት የደረሰባቸው ችግር በቀላሉ የሚገለጽ አይደለም። በድርቅና በተናጡበት ወቅትም ከዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ሊደረግላቸው የሚገባውን የፈጥኖ ደራሽ ምግብ እርዳታ በአሸባሪዎች ምክንያት ያልተሳካበት ሁኔታ እንደነበርና በዚያ ሳቢያም በርካታ ሶማሊያዊያን ለሕልፈተ ሕይወት መዳረጋቸው የቅርብ ጊዜ ታሪክ ነውቅ። አሁንም ቢሆን ሽብርተኞች ባሉባቸው የተወሰኑ የሶማሊያ አካባቢዎች ያሉ ሶማሊያዊያን ከችግሩ ሙሉ በሙሉ ተላቀዋል ማለት አይቻልም።
በአፍሪካ አገራት አሸባሪዎች ካደረሷቸው የሽብር ጥቃቶች መካከል የተወሰኑትን ማየት የችግሩ አስከፊነት ምን እንደሚመስል ሙሉ ግንዛቤ ለመያዝ ያግዝ ይሆናል። በኬንያ የገበያ ማዕከል  በደረሰ የሽብር ጥቃት 65 ሠላማዊ ሰዎች ሕይወት ተቀጥፏል። ለአካል ጉዳተኝነት የተዳረጉትን በርካቶች ናቸው።  በሚለዮን የሚገመት ንብረት ወድሟል።

ኢትዮጵያን የወሰድን እንደሆነም  በርካታ ዜጎች  የሽብርተሽነት ጥቃት ሰለባ ሆነዋል።  የአገሪቱን ሰላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ ለማደናቀፍ  አሸባሪዎች በተለያየ ጊዜ በተለያዩ አካባቢዎች ባደረሷቸው የሽብር ጥቃቶች የበርካታ ንጹሃን ዜጎች ሕይወት ከማለፉም ባሻገር ቀላል የማይባል የአገርና የህዝብ ንብረት ወድሟል።  በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያም የሰላምና የመረጋጋት ገጽታ ለመቀየር ያስችላል፣ አዲስ አበባን የብጥብጥና የሁከት ማዕከል ለማድረግ አልሞ የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በሚካሄድበት ወቅት የሽብር ጥቃት ለማድረስ የተደረገው እንቅስቃሴ ከከሸፉ የሽብር ተግባራት አንዱ እንደሆነ ይታወቃል።
የዜጎችን ሰላም ለማስጠበቅና እየተመዘገበ ያለው ፈጣን ልማት በአስተማማኝ መልክ ለማስቀጠል መንግስት እያደረገ ያለውን ጥረት ለማሳካት የፀረ-ሽብርተኝነት ስትራቴጂክ ዕቅድ  በመንደፍ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል።  ኦነግ፣ አብነግና ግንቦት ሰባት ከአገር ውስጥና አልሸባብና አልቃይዳ ከውጭ አገራት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት ተፈርጀዋል።
የሸብርተኝነት ወንጀልን በመከላከል የዜጎች ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነቱንና ግዴታውን ለመወጣት የፀረ-ሽብር ግብር-ኃይል አቋቁሞ የፀረ-ሽብርተኝነት ትግሉን በፅናት እያካሄደ  ሕዝቡ የጠራ ግንዛቤ እንዲኖረው የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት የፀረ-ሽብርተኝነት ትግሉን እንዲያቀጣጥል ያላሳለሰ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።
መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም ለፀረ-ሽብርተኝነት ህጉ ተፈጻሚነትና የፀረ-ሽብር ግብር-ኃይሉ በአገሪቱ የሰፈነው አስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እያደረገ ላለው ሁለንተናዊ ጥረት ስኬት ከመንግሥት ጎን ተሰልፎ የሚጠበቅበትን ድጋፍ ሁሉ በማድረግ ላይ ነው።
ከዚሁ ጋር ታያይዞ በአገሪቱ የሚታየውን ፅንፈኝነት  የሽብርተኝነት መገለጫ እየሆነ መጥቷል።  ሃይማኖትን ሽፋን አድርገው ድብቅ የፖለቲካ አጀንዳቸውን ለማሳካትና በአገሪቱ የሰፈነውን አስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት ለማደፍረስ  የሚንቀሳቀሱ ፀረ-ሰላምና ፀረ-ልማት ኃይሎችን በማጋለጥ ረገድ ህዝቡ ያልተቆጠበ ጥረት እያደረገ ቢሆንም  ፀረ-ሰላምና ፀረ-ልማት ቡድኖቹ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ለመናድ የተለያዩ ተግባራት በመፈፀም ላይ ናቸው።
ፅንፈኝነትና  ሽብርተኝነት  ሃይማኖታዊ ባህሪ የሌላቸው ሃይማኖትን በሽፋንነት የሚጠቀሙ ግን  ሕቡእ  አጀንዳ  ለማራመድ የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች የተሰባሰቡባቸው አደረጃጀቶች ናቸው። 
ኢትዮጵያ አስተማማኝ ሠላምና መረጋጋት፣ የፈጣን ልማትና ዕድገት  ቀጠናነቷ በዘላቂነት እንዲረጋገጥ እየተካሄደ ያለውን የተቀናጀ የፀረ-ሽብርተኝነት ትግልን ከመንግሥት ጎን ተሰልፈን አጠናክረን እንቀጥል። ሀገራችንን ከጥፋት ኃይሎች የመጠበቁና የመከላከሉ ተግባር የሁላችንም መሆኑን ተገንዝበን ያለንን ወሳኝ አገራዊ ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ሁሉም ዜጋ ተግቶ ሊሰራ ይገባል።
በምስራቅ አፍሪካ አልሸባብ፣ በናይጀሪያ ቦኮ ሀራም፣ በማሊ አሳር ዲን በማግርብና ሳህል በረሃ ሙጃኦን አበዒ እንዲሁም አዘዋድ ኢስላዊ ንቅናቄ የተባሉ አሸባሪ ቡድኖች እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ይታወቃል።
ናይጀሪያ ውስጥ እስላማዊው አክራሪ ቡድን ቦኮ ሃራም  በርካታ ጥፋቶች እየፈጸመ ይገኛል። ናይጀሪያን ካሜሩን በሚያዋስነው ድንበር ጥቃት ማድረሱ ታውቋል። 300 ያህል ሰዎች ተገድለዋል። ከዚህ ሌላ፤ ከትምህርት ቤት ተጠልፈው የተወሰዱ 276 ልጃገረዶች፣ በዚህ አሸባሪ ድርጅት ቁጥጥር ሥር ነው የሚገኙት። ፈተናው ለሃጋሪቱ ብርቱ ራስ ምታት ሆኗል። ቦኮ ሃራም ያመጣውን ቀውስ ባፋጣኝ ማስወገድ የሚቻል አይመስልም።
በናይጀሪያ የሕዝቡ ቁጣ በመጨመር ላይ ነው። እስላማዊው አሸባሪ ድርጅት ቦኮ ሃራም፤ አንዳንዴ በአንድ ሳምንት ውስጥ ተደጋጋሚ አደጋ ነው የሚጥለው። በመዲናይቱ በአቡጃ መዳረሻ ንያንያ በተባለው ሠፈር ሁለት ቦታ ላይ ነበረ የማጥቃት ርምጃ የወሰዱት። መዲናይቱ አቡጃ ድረስ ዘልቀው በመግባት ህዝቡን ማሸብር ከጀመሩ ውሎ አድሯል። ሕዝቡም ተጨንቋል። «ሰዎቻችሁ ወደዚህ መጥረው ሊረዱን ይገባል። ሁኔታው አስከፊ ነው። እኛ ናይጀሪያውያን በመሠቃየት ላይ ነን። በዚህ አገር ምንም የሚያስተማምን ሁኔታ የለም። ፕሬዚዳንቱ በእርግጥ ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው ሆኖም፣ ሁሉንም መለወጥ አይችሉም።»
ዩናይትድ ስቴትስ በመካሉ ልዩ ቡድን ልካለች፤ ብዙዎች ናይጀሪያውያን ይህ እንዴት በቂ ሊሆን ይችላል? በማለት ይጠይቃሉ። ቦኮ ሃራም ከተደራጀ 12 ዓመት ሆነው። መሥራቹ ሙሐመድ ዩሱፍ 2009 ም፣ ከሞቱ ወዲህ፤ ንቅናቄው ይበልጥ አክራሪ መሆኑና አያሌ የጭካኔ ርምጃዎች መውሰዱ ይነገርለታል።
በቅርቡ ከካሜሩን ጋር በምታዋስነው ጋምቡሩ እንጋላ በተባለው ሠፈር፣ ሰኞ 300 ያህል ሰዎች ናቸው የተገደሉት። «ደራስያን ለሰብአዊ መብት» የተሰኘው የናይጀሪያ ደራስያን ድርጅት ባልደረባ ኢማኑኤል ናዶዚ ኦንውቢኮ ሂደቱ አስፈሪ ነው ይላሉሰዎቹ ጨለማን ተገን አድርገው አደጋ ከጣሉ በኋላ ነው የሚሠወሩት። ጦር መሣሪያ በገፍ ነው የታጠቁት። በሚገባ የጦር ሥልጠና ያገኙም ናቸው። ለዚህም ነው የኛ ወታደሮች ሰፋ ያለ ሥልጠና ያስፈልጋቸዋል የምንለው።»
ጥያቄ መቅረብ ከጀመረ ቆይቷል። በጦር ኃይሉ ውስጥ ጉዳዩን በጥሞና የሚያነሱ ወገኖች፤ ወታደሮቹ በመደበኛ የጦር ስልት የሠለጠኑ እንጂ በፍጥነት ከቦታ ቦታ የሚሽሎከለኩ አሸባሪ ደፈጣ ተዋጊዎችን ለመዋጋት የሚያስችል ዘዴን አላካተቱም። አሸባሪዎቹ አደጋ ጥለው ያላንዳች ችግር ተሽሎክልከው ካሜሩን ወይም ቻድ ይገባሉበመደበኛ ጦር አሸባሪዎችን መዋጋቱ የራሱ የሆነ ሳንክም ሆነ ገደብ እንዳለው ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ በሚገባ ታይቷል።
አምና ከግንቦት ወር አጋማሽ ገደማ አንስቶ 3 የሰሜን ናይጀሪያ ፌደራል መስተዳድሮች የአስቸኳይ ሁኔታ አዋጅ እንደታወጀ ነው። ይህም አ።ሸባሪዎችን ለመውጋት የሚያስችል ነበረ። ይሁንና ያን ያህል የተሳካ ውጤት አይደለም የተመዘገበው። አክራሪዎቹ ኃይሎች ከምን ጊዜውም በላቀ ሁኔታ ተጠናክረው ነው የተገኙት። በአቡጃ የጀርመኑ አደናዎር ድርጅት መሪ ከአሸባሪው ታጣቂ ኃይል ጋር ውይይት ማድረጉ ሊበጅ ይችላል ይሁን እንጂ የተሳካ ውጤት የሚያስገኝ መሆኑ ያጠራጥረኛል ባይ ናቸው።

No comments:

Post a Comment