Friday, 19 August 2016

የአመለካከት ለውጥ ያመጣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ጉብኝት!




ስሜነህ
የግብፅ፤ የሱዳን፤ የደቡብ ሱዳንና የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ሐምሌ 24 ቀን 2008 .ም ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጎብኝተዋል። ይህን የመስክ ጉብኝት ከምሥራቅ ናይል የቴክኒክ የቀጠና ቢሮ (ኢንትሮ) ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የስዊዲን ዓለም አቀፍ የውኃ ኢንስቲትዩት እንደሆነ ፕሮጀክት ጽ/ቤቱን ጠቅሰው በርካታ የግብጽ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡ ጋዜጠኞቹ ወደ መስክ ከመሄዳቸው በፊት ከሐምሌ 21 - 23 ቀን 2008 .. ድረስ በአዲስ አበባና በአሶሳ የምሥራቅ ናይል ተፋሰስንና ግድቡን በተመለከተ ሥልጠና የተከታተሉ መሆኑንም ጭምር ሚዲያዎቹ ዘግበዋል፡፡
የናይል ተፋሰስ አገሮች የጋዜጠኞች ቡድን የግድቡን የግንባታ ሂደት የተመለከተ ይፋዊ ጉብኝት ሲያደርግ ይህ የመጀመሪያው ነውና ሳያዩና ሳይሰሙ ሲጽፉና ሲያነበንቡ የነበሩ፤ በተለይ አንዳንድ የግብጹ አልሃራም ጋዜጠኞች ከጉብኝታቸው በኋላ የሰጧቸውን አስተያየቶችና የሰሯቸውን ዘገባዎች በጋራ ከመልማትና በጋራ ከማደግ አኳያ ይህ ተረክ ይመዝናል፡፡ ከጉብኝቱ አስቀድሞ የተሰጠው ሥልጠናና ስልጠናውን ተከትሎ በጋዜጠኞቹ መካከል የነበረው የሐሳብ ልውውጥ፤ የቀረቡትምሁራን ጥናቶች፤ ከየአገሮቹ ኃላፊዎች ጋር የተደረጉት ውይይቶች አዳዲስ ምልከታዎችን የፈጠሩ ስለመሆናቸው፤ ጋዜጠኞቹ በተለይ ከኢትዮጵያ ውጭ የመጡቱጉብኝቱ ትክክለኛ ግንዛቤ መጨበጣቸውን፤ ይልቁንም በግንባር የተመለከቱት ነገር በየአገሮቻቸው ያሉ አንዳንድ ልሂቃን በነሲብ ሲሰጧቸው ከነበሩትና በጆሮ ከሚሰሟቸው ኢፍትሃዊ መረጃዎች የተለዩ እንደሆኑ ራሳቸው በሰሯቸው ዘገባዎቻቸው እንደምታዎች ያረጋግጣሉ፡፡
ሃይተም ሞሐመድ፤ ባለፉት አምስት ዓመታት ለዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት የሠራ ግብፃዊ ጋዜጠኛ ነው፡፡ በእነዚህ አምስት ዓመታት ሃይተም ታላቁን የህዳሴ ግድብ ጨምሮ ስለ ግብፅ የፖለቲካ ሁኔታ ዘግቧል፡፡ የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪውና ጋዜጠኛው ሃይተም  ‹‹ናይል የግብፅ ሳምባና ልብ ነው፤›› ብቻ ብለው ከሚዘምሩት ጋር አብሮ ለ 5 ዓመታት የዘመረ እንደሆነ ገልጾ፤ ከጉብኝቱ በኋላ የነበረው ስሜት ስለመለወጡና በትብብር የመልማትን ዋጋ በሚገባ ማጤኑን እንደሚከተው መስክሯል፡፡
አሁን ወደ ኢትዮጵያ መጥቼ የአገሪቱን የኢኮኖሚናማኅበራዊ ሁኔታ በሚገባ ካየሁና ወደ ግድቡ መጥቼ ጉብኝት በማድረግ የግድቡን ሥራ አስኪየጅ ኢንጂነር ስመኘውንና ሌሎችግድቡ ላይ የሚሠሩ ሰዎችን ካናገርኩ በኋላ ያለኝ የግል ድምዳሜ የተለየ ነው፡፡ ጉብኝቱ በጣም ጠቃሚ ነበር፡፡ ግልጽነት የተሞላበትም ነበር፡፡ አሁን በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል የመተባበር ዕድል ማየት ችያለሁ፤
ሁለቱም አገሮች ጉዳዩን በጋራ ዓይን ማየት ቢችሉ የተሻለ ዕድል መፍጠር ይቻላል፡፡ ኢትዮጵያ በኃላፊነት ከሠራችና ግብፅም ከተባበረች ግድቡ ለማናቸውም ሥጋት አይሆንም፡፡ ይህ ከሆነ ግድቡ ለኢትዮጵያና ለግብፅ ብቻ ሳይሆን ለናይል ተፋሰስ ወንድሞቻችን ሁሉ የሚተርፍ ነው የሚሆነው፤›› ሲል ሃይተም የአከለው ሀሳብ በተዘዋዋሪ አገራችን ስትሄድበት የነበረው መንገድ ሁሉ ትክክል መሆኑን የሚያጠይቅ ነው፡፡
ሃይተም ከጉብኝቱ በኋላ የተናገረውን ጠቅሰው በግብጽ የሚገኙ ሚዲያዎች እንደዘገቡትም፤ ሚዲያዎች በምሥራቅ ናይል ተፋሰስ አገሮች የሚንፀባረቀውን የተለያየና አልፎ አልፎም የሚጋጭ ፍላጎት በማመዛዘን ማየት እንዳለባቸው በማስታወስ፤ ሃይተም፤-
ልማትንና ጥሩ መጪ ጊዜን መጋራት ሰብዓዊ የሆነ ሐሳብ ነው፡፡ ምክንያታዊና ኃላፊነት የሚሰማን ሆነን ከሠራን ግድቡ ሥጋት ሊሆን አይችልም፡፡ በኢትዮጵያ በነበረኝ የስድስት ቀናት ቆይታ ያገኘሁት ትምህርት ይህ ነው፡፡ ይህን መልዕክት ነው ለግብፃዊ ታዳሚዎቹ የማደርሰው፡፡ ውኃ ተፎካክረን የምናገኘው ዕቃ አይደለም፡፡ የሕይወት መሠረት የሆነ፤ ለማደግና ኢኮኖሚያችንን ለማበልፀግ፤ በሕይወትም ለመቆየት የሚያስፈልግ ነገር ነው፡፡ ሚዲያ እውነተኛውን መረጃ ለሕዝቡ በማድረስ ውሳኔ እንዲሰጡ ማድረግ አለበት፡፡ ኢትዮጵያ ብዙ ሰዎች እንዲመጡ መጋበዝ አለባት።
ሲል የሰነዘረውን ሀሳብ ጠቅሰው መምከራቸው በእርግጥም በአባይ ጉዳይ ላይ ሃገራችን የያዘችው አቋም በተግባርም የተረጋገጠ መሆኑን የሚያመላክትና ስለጋራ ልማትና እድገት አዎንታዊ መሆኗን የሚያጠይቅ ነው።እናም፤ ሃይተምን ጨምሮ ሌሎቹም እንዳሉት ተደጋጋሚ ጉብኝቶች ማዘጋጀት ከአገራችን የሚጠበቅ መሆኑን ልናሰምርበት ይገባል።  
ላለፉት ስድስት ዓመታት ድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን በተመለከተ ስትዘግብ የምትታወቀው ሌላኛዋ ግብጻዊት ጋዜጠኛ አያህ አማን፤ ባለፉት ስድስት ዓመታት ስለ እነዚህ ጉዳዮች የምዘግበው ወይም በተለይ ዋነኛ ጉዳይ የሆነውን የታላቁን የህዳሴ ግድብ ግንባታ አስመልክቶ ስጽፍ በዐይኔ ሳላይ ነበር።ብላ በልኡካኑ ፊት ተናግራ፤ በአልሞኒተር ኦን ላይን አምዷ ላይም የማስፈሯ እንደምታ የሚያጥይቅልን በባልደረባዋ ሃይተም ልክ ኢትዮጵያ የተፋሰሱን አገራት ሁሉ የላቀ ተጠቃሚ በሚያደርግ ግንባታ ላይ መገኘቷን የተረዳች መሆኗን ነው፡፡ እናም አያህ አማን ፤-
ግድቡን በአካል ማየት፣ ፎቶ ማንሳትና ስለታዘብነው ነገር ለሕዝብ መናገር ለምትጽፈው ነገር ተአማኒነትን ይገነባል፡፡ሕዝባችን ውስጥ ያለውን ቁጣና ፍራቻም ሊቀንስ ይችላል፡፡ ሁሉንም ነገር በአንዴ መቀየር አይቻልም፡፡ ነገር ግን፤ አሁን ቢያንስ የግድቡን እውነታ መቀበል ይቻላል፡፡ ግድቡ ጉዳት እንደማያመጣ በማመን፤ ሁለቱንም አገሮች አሸናፊ የሚያደርግ አሠራር ቢተገብሩ ጠቃሚ ነው ብዬ አምናለሁ፤
በማለት መናገሯ ትልቅ ትርጉም ያለውና በነሲብ ታላቁን ግድብ ለሚነቅፉት ሁሉ እውነተኛ የሆነውን የኢዮጵያ አሰላለፍ እንዲገነዘቡት የሚያስችል ነው፡፡
የናይል ተፋሰስ አገሮች ሲባል ስብስቡ ብሩንዲን፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን፣ ግብፅን፣ ኤርትራን፣ ኢትዮጵያን፣ ኬንያን፣ ሩዋንዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ታንዛኒያንና ኡጋንዳን የሚያቅፍ ቢሆንም፤ ኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን የሚገኙበት የምሥራቅ ናይል ተፋሰስ እጅግ ጠቃሚው ክፍል እንደሆነ ይታወቃል፡፡
በምሥራቅ ናይል ተፋሰስ አገሮች መካከል ያለው ውጥረትና አለመተማመን፤ ለትብብር ያለው አቅም፣ በቆዳ ስፋት የተፋሰሱን 60 በመቶ የሚሸፍን ሲሆን፤ ይህም በተፋሰሱ አገራት የሕዝብ ብዛት አንጻር ሲሰላ 54 በመቶውን የያዘና ለናይል ውኃ ሀብት 86 በመቶ የሚሆነውን መጠን አስተዋጽኦ የሚያደርግመሆኑ በመልማትና በዕቅድ ላይ ያሉት አብዛኛዎቹ ፕሮጀክቶች ታላቅ ጠቀሜታ እንደሚኖራቸው መገመት አይከብድም፡፡
ቀጣናው ያለበትን ችግር ለመቅረፍ ሚዲያ ቁልፍ አጋር ተደርጎ መወሰዱ አያጠያይቅም፡፡   ምክንያቱም፤ የውኃ ዲፕሎማሲ አገሮች በድርድር በሚያደርጓቸው ስምምነቶች ውኃን በጋራ ለመጠቀም እንዲሰሩ ያስችላልና፤ የትብብሩን ድርድር ለበርካታ ባለድርሻ አካላት  ለማስገንዘብና ውጤታማ እንዲሆን ለማድረግ የሚዲያው ሚና ከላይ በተመለከተው እንኳ ብናሰላው የላቀ መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡
ሚዲያው አለመግባባቶችን የማባባስ ሚና ሊጫወት የመቻሉን ያህል፤ ወደ ትብብርም ሊያሸጋግር የሚችል መሆኑንም የህዳሴው ግድብ የመሰረት ድንጋይ ከተቀመጠበት ጊዜ ጀምሮ በግብጽ ሚዲያዎች ሲወጡ የነበሩ ዘገባዎችን ከላይ ከተመለከቱት የአሁኑ የግብጽ ጋዜጠኞች አስተያየት አንጻር በመመዘን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
እንዲህ አይነቱ  የሚዲያ ሥልጠና የናይል ተፋሰስ አገሮች ገንቢ የሚዲያ ዘገባዎችን ለማጠናከር፤ የተሻለ ግንዛቤና ዕውቀት ለመፍጠርና በቀጣናው ትብብርን ለማጠናከር ታላቅ አስተዋጽኦ ያላቸው መሆኑንም ከዚህ በላይ ማጠየቂያ ማምጣት አያሻንም። በተለይ ኢትዮጵያን ለሚጠራጠሩ የተፋሰሱ አገራት ዜጎች እውነታውን በመግለጥ ተባባሪ እንዲሆኑ ያስችላልና አጥብቆ መያዝ ተገቢ ነው። ኢትዮጵያ ግድቡን ለልማቷና በአጠቃላይ ለተፋሰሱ አገሮች ደኅንነት ጠቃሚ አድርጋ ብትወስደውም፤ የታችኛው ተፋሰስ አገራት በተለይም ግብጾች ግድቡ ጥቅማችንን ይነካል በሚል ሥጋታቸውን ከመግለጽ ተቆጥበው አያውቁምና፡፡ ኢትዮጵያ ግድቡ መሠረታዊ ጉዳት እንደማያስከትል ባደረገችው ማጣራት ማረጋገጧን በመተማመን፤ ከግብፅና ከሱዳን ጋር በጋራ ግድቡ ሊኖረው የሚችለውን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመገምገም ፈቃደኝነቷን በተደጋጋሚ ማሳየቷ እና ኃላፊነት ወስዳ እየሰራች መሆኑ በግልጽና በአደባባይ የሚታወቀውም በእንዲህ አይነት ጉብኝቶችና ስልጠናዎች መሆኑንም ከላይ ከተመለከቱት ምስክርነቶች በላይ ማጠየቂያ ፍለጋ መኳተን አይገባም፡፡
ከውኃ አንፃር ትብብር ማለት በጋራና በተቀናጀ መልኩ በአካባቢ፤ በብሔራዊ፤ በክልልና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ውኃውን በጋራ ማስተዳደርና መጠቀም ነው፡፡ ይህ ስለሆነም ነው የምሥራቅ ናይል ተፋሰስ አገሮች ራሳቸውን ለትብብር ክፍት ማድረግ የሚያስገድዱ በርካታ ምክንያቶች እንዳሉ ጥናቶች የሚያመለክቱት፤ ከእነዚህም መካከል፤ በሕዝብ ቁጥር ዕድገት፤ በተጨማሪ የውኃ ጥያቄ፤ በውኃ ገብ አካባቢዎች መመናመን፤ በውኃ መጠን መቀነስ የሚጠቃው አካባቢ ትብብር የሚሻ መሆኑን የሚገልጸው ጥናት የመጀመሪያው አስረጅ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በውኃ አስተዳደር ላይ የጋራ ስምምነት መጥፋቱ ከሰላምና ከደኅንነት ጋር የተያያዙ ውጥረቶችን ማንገሱም የሚጠበቅብ እንደሆነም ጥናቶቹ ያረጋግጣሉ። እናም ይህ ከመሆኑ አስቀድሞ ሚዲያው በቂ ግንዛቤ ከያዘ፤ ውጥረቶች ሁሉ በቀላሉ ይረግባሉ። ለዚህም ነው በተደጋጋሚ እንዲህ ዓይነት ጉብኝቶች  አስፈላጊ ናቸው ማለታችን፤


No comments:

Post a Comment