ዘአማን በላይ
የኢፌዴሪ
ህገ መንግስት ፌዴራላዊ የመንግስት ስርዓትን አቋቁማል፡፡ የዚህ ስርዓት ዋና መለያ የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የራስን ዕድል
በራስ የመወሰን መብታቸውን መሰረት ያደረገ ፌዴራላዊ የመንግስት አወቃቀር፣ አደረጃጀት እና አሰራር ማቋቋሙ ነው። የኢትዮጵያ ብሔሮች
ብሔረሰቦችና ሕዝቦ የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው የመወሰን መብታቸውን በመጠቀም በራሳቸው ነፃ ፍላጎት ባፀደቁት ህገ መንግስት በሀገራችን
ዘላቂ ሰላም፣ ዋስትና ያለው ዴሞክራሲ እንዲፍን፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገታችን እንዲፋጠን ለማድረግ በሕግ የበላይነትና በራሳቸው
ፈቃድ ላይ የተመሰረተ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ የመገንባት ዓላማ ያላቸው መሆኑን በግልፅ ቋንቋ አውጀዋል።
ለዚህ
ዓላማቸው መሳካትም በህገ መንግስቱ የግለሰብና የብሔር ብሔረሰብ መሰረታዊ መብቶች መከበራቸው፣ የፆታ እኩልነት መከበር፣ ሃይማኖቶችና
ባህሎች ያለአንዳች ልዩነት እንዲራመዱ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ፅኑ እምነት ያላቸው መሆኑን ገልፀዋል። እርግጥም ይህ ፌዴራላዊ ስርዓት
የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በህገ መንግስታቸው የጋራ ጉዳዮቻቸውን በጋራ ለማስተዳደር፣ የፌዴራል መንግስት መስተዳድርን
ለማቋቋም፣ እያንዳንዳቸው ራሳቸውን የማስተዳደር መብታቸውን ተግባራዊ ለማድረግ በሰፈሩበት መልክዓ ምድር ራሳቸውን የሚያስተዳድሩበት
መንግስታዊ ተቋማትን ለማቋቋም፤ እንዲሁም በክልልና በፌዴራል መስተዳድሮች ውስጥ ሚዛናዊ ውክልና የማግኘት ምቹ ተቋማዊ ማዕቀፍን
ፈጥሮላቸዋል።
ህገ
መንግስቱ እንደማናቸውም የፌዴራል መንግስት ስርዓት እንዳላቸው ሀገሮች ሁሉ፤ የመንግስትን ስልጣን በሕግ አውጪ፣ በሕግ አስፈፃሚውና
በዳኝነት አካላት መካከል ብቻ ሳይሆን ብዛት ባላቸው የስልጣን ማዕከላት ማለትም በፌዴራልና በክልል መስተዳድሮች መካከል ያከፋፍላል።
ባለፉት ድርዓቶች ገቢራዊ ሆኖ የነበረው አሃዳዊ ስርአት በኢትዮጵያ የህዝቦች መካከል ቅራኔንና መካረርን እንዲሁም የመበታተን አደጋን
ፈጥሮ ነበር። ላለፉት 25 ዓመታት ዕውን የሆነው ፌዴራላዊ ስርአት ግን በመፈቃቀድ፣ በየደረጃው ገቢራዊ በሚሆን እኩል ተጠቃሚነትና
በሰፊ የክልሎች ስልጣን በመመስረቱ ለልማትና ለዴሞክሲያዊ አንድነት እንዲሁም ለሰላም ዋስትናን ፈጥሯል። እርግጥ በእነዚህ ዓመታት
ብሔራዊ ጭቆናንና የአሃዳዊ ስርአት አስተሳሰብንና ተቋማዊ አደረጃጀትን ስር ነቀል በሆነ መንገድ በማስወገድ በፅኑ መሰረት ላይ የተገነባ
የፖለቲካ ማዕቀፍ መፍጠር መቻሉ የሀገራችን ፌዴራላዊ ስርአት መገለጫዎች ናቸው ተብለው ሊጠቀሱ ይችላሉ። እናም ይህን ስርዓት ዕውን
ያረገውን ህገ መንግስት ማክበርና ማስከበር የግድ ይላል።
እስቲ
እዚህ ላይ ‘ለፌዴራላዊ ስርዓቱ ዕውን መሆን ፈር የቀደደው ህገ መንግስት የማን ነው?’ የሚል ጥያቄ እናንሳ። የኢፌዴሪ ህገ-መንግስት
የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ነው። እነዚህ ህዝቦች የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው የመወሰን መብታቸውን ተጠቅመው በራሳቸው
ነፃ ፍላጎት ያፀደቁትም ነው፤ የዛሬ 21 ዓመት ገደማ። ለዚህም ነው—በህገ-መንግስታቸው መግቢያ ላይ “….እኛ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣
ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች” በማለት የእምነታቸው ማሰሪያ እንዲሆናቸው ቃል ኪዳን መግባታቸውን ያረጋገጡት። ለዚህም ነው— እነርሱ የአዲሲቷ
ኢትዮጵያ የማይገሰስ የስልጣን ባለቤቶች መሆናቸውን በህገ መንግስቱ አንቀፅ 8 ላይ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤቶች መሆናቸውን ያወጁት።
ለዚህም ነው— እነርሱ በሚመርጧቸው ተወካዮቻቸውና በቀጥታ በሚያደርጉት ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ አማካኝነት ለመረጡት አካል ውክልና እንደሚሰጡ
በማወጅ ህገ መንግስቱ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች መሆኑን በማያወላዳ ሁኔታ ያረጋገጡት። እናም የፌዴራላዊ ስርዓቱ መነሻ የሆነው
ህገ መንግስት የእነርሱና የእነርሱ ብቻ መሆኑን ግንዛቤ መያዝ የሚገባ ይመስለኛል።
በህገ
መንግስቱ የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በሀገራችን ዘላቂ ሰላምና ዋስትና ያለው ዴሞክራሲ እንዲሰፍን፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ
ዕድገታችን እንዲፋጠን ለማድረግ በነፃ ፍላጎታቸው በህግ የበላይነትና በራሳቸው ፈቃድ ላይ የተመሰረተ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ
የመገንባት ዓላማ አላቸው። መጪው የጋራ ዕድላቸው መመስረት ያለበት ከታሪካቸው የወረሱትን የተዛባ ግንኙነት በማረምና የጋራ ጥቅማቸውን
በማሳደግ ላይ መሆን እንዳለበት የተቀበሉ መሆናቸውን በተደጋጋፊነት በፍትሐዊና ፈጣን ልማት ለማሳደግ አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ
መገንባት አስፈላጊ ነው ብለው እንደሚያምኑ በህገ መንግስቱ ገልፀዋል።
በህገ
መንግስቱ ለዚህ ዓላማቸው መሳካት የግለሰብና የቡድን መሰረታዊ መብቶች እንዲከበሩ፣ የፆታ እኩልነት መረጋገጡ፣ ሃይማኖቶችና ባህሎች
ያለአንዳች ልዩነት እንዲራመዱ አድርገዋል። ኢትዮጵያ የየራሳቸው አኩሪ ባህል ያላቸው ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ሀገር መሆኗን፣
የየራሳቸው መልክዓ ምድር አሰፋፈር የነበራቸውና ያላቸውን በተለያዩ መስኮችና የግንኙነት ደረጃዎች ተሳስረው አብረው የኖሩባትና የሚኖሩባት
ሀገር በመሆኗ ያፈሩት የጋራ ጥቅምና አመለካከት አለን ብለው የሚያምኑ መሆናቸውንም በህገ መንግስታቸው ላይ በማያሻማ ሁኔታ ደንግገዋል።
በህገ
መንግስቱ የስልጣን ምንጭ ማዕከላዊ መንግስት ሳይሆን ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች መሆናቸው ተገልጿል። ለራሳቸው በቂ ስልጣን አስቀርተው
ለጋራ ጉዳይ የሚያስፈልግ ስልጣንን ለማዕከላዊ መንግስት ቆርሰው ሰጥተዋል። ታዲያ እዚህ ላይ ኢፌዴሪ ህገ-መንግስት ልየ ባህሪያት
ያሉት መሆኑን መገነዘብ ያሻል። ህገ መንግስቱ የብሔሮች የብሔረሰቦችና የህዝቦች እንደ መሆኑ መጠን፤ የህገ-መንግስት የበላይነትን
ለማረጋገጥ ህገ-መንግስቱ በማናቸውም የመንግስት አካላት ብቸኛ ውሳኔ ሊሻሻል እንደማይችል በማስቀመጥ አንዱ የሌላው የበታች እንዳይሆን
ይከላከላል። የክልሎች ሃሳብ በፌዴራል ምክር ቤቶች እንዲወከሉ በማድረግም በፌዴራል የጋራ ጉዳዮች ውሳኔ አሰጣጥ ላይ እንዲሳተፉ
አድርጓል። ህግ- መንግስትን የመተርጎም ስልጣን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በመሰጠት፤ በህገ-መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ኮሚሽን የውሳኔ
ሃሳብ አቅራቢነት የሚወሰንበትን ስርአት ህገ-መንግስቱ ዘርግቷል።
በኢትዮጵያ
ህገ-መንግስት የተመሰረተው ብሔር ተኮር ፌዴራሊዝም (multi-ethnic federalism) በመሆኑ በግዛት ላይ የሰፈሩ ብሔራዊ
ማህበረሰቦች የራሳቸውን ጉዳይ በሚመለከት የራስ አስተዳደርና የጋራ ጉዳዮች ላይ የጋራ አስተዳደር ስልጣን እንዳላቸው ያረጋግጣል።
ሌላኛው
የህገ መንግስቱ የተለየ ባህሪ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብትን መሰረት ያደረገ ፌዴራላዊ የፖለቲካ ስርዓትን ማጎናፀፉ ነው።
ይህም የፖለቲካዊ ስርዓቱ ምሶሶ ነው ማለት ይቻላል።
በዚህም
መሰረት በኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 39 (1) መሰረት ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን
እስከ መገንጠል ያለው መብቱ በማናቸውም መልኩ ያለገደብ የተጠበቀ ነው። እንዲሁም በህገ-መንግስቱ መግቢያ በመጀመሪያዎች ሁለት ተከታታይ
አንቀፆች ላይ እንደተገለፀው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦና ሕዝቦ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ ለመገንባት የተስማሙትና ቃልኪዳን የገቡት
በነፃ ፍላጎታቸው የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው የመወሰን መብታቸውን በመጠቀም ነው። ይህም ስለ ኢትዮጵያ የፌዴራል ፖለቲካ ስርዓት
የሚደረጉ ማናቸውም ህጋዊ ውይይቶች የራስን ዕድ በራስ የመወሰን መብት ላይ የሚያጠነጥኑና የሚቆራኙ ውይይቶችን የግድ መጋበዛቸው
አይቀርም።
ያም
ሆኖ እዚህ ላይ ‘የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ባለቤት ማን ነው?’ የሚል ጥያቄን ማንሳት የሚያስፈልግ ይመስለኛል። በህገ
መንግስቱ አንቀጽ 39 (1) መሰረት ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰብ፤ ሕዝብ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ባለቤት ነው
የሚል ድንጋጌ ተቀምጧል። በአንቀጽ 39 (5) ላይ ደግሞ “ብሔርና ብሔረሰብና ሕዝብ” ማለት ሰፋ ያለ የጋራ ጠባይ የሚያንፀባርቅ
ባህል ወይም ተመሳሳይ ልምዶች ያሉት፣ የጋራ የስነ ልቦና አንድነት ያላቸውና በአብዛኛው በተያያዘ መልክዓ ምድር የሚኖሩ አባላት
ያሉት ማህበረሰብ መሆኑን ለመረዳት ይቻላል፡፡ ምንም እንኳን ህገ መንግስቱ በአንቀጽ 54 (2) እና (3) ውስጥ “አናሳ ብሔረሰቦችና
ሕዝቦች” የሚል ፅንሰ ሐሳብን በፌዴራሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ የተለየ ውክልናን ለመስጠት የተጠቀመ ቢሆንም፤ የራስን
ዕድል በራስ የመወሰን መብት ባለቤትነትን በተመለከተ አናሳ መሆን መብቱን የሚገድብ ወይም የሚነፍግ አይደለም። በመሆኑም እያንዳንዱ
ብሔር፣ ብሔረሰብና ህዝብ የዚህ መብት ባለቤት ነውና፡፡
የራስን
ዕድል በራስ የመወሰን መብት በሕገ መንግስታችን ሶስት ዋና ዋና የሆኑና የተቆራኙ መብቶችን ያቀፈ ፅንስ ሐሳብ ነው፡፡ አንደኛ ማናቸውም
የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰብና ሕዝብ በቋንቋው የመናገር የመፃፍና የማሳደግ እና ባህሉን የመግለፅ እንዲሁም የማዳበርና የማስፋፋት
እንዲሁም ታሪኩን የመንከባከብ መብት አለው፡፡
ሁለተኛ
ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰብ ሕዝብ ራሱን የማስተዳደር ሙሉ መብት አለው፡፡ በዚህም መሰረት እያንዳንዱ ብሔር ብሔረሰብና
ሕዝብ በሰፈረበት መልክዓ ምድር ራሱን የሚስተዳድርበት መንግስታዊ ተቋማት የማቋቋም መብት ያለው ከመሆኑም በተጨማሪ በክልልና በፌዴራል
አስተዳደሮች ውስጥ ሚዛናዊ ውክልና የማግኘት መብት አለው፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች
በፌዴራልም ሆነ በክልል መስተዳድሮች የስልጣን እርከኖች ውስጥ በመንግስት አስተዳደር ስራ ውስጥ መሳተፍ እንዲችሉ ህገ መንግስታዊ
ዋስትና የሚሰጣቸው መብት ነው፡፡
ይህ
መብት በአንድ በኩል በየሰፈሩበት መልክዓ ምድር ለእያንዳንዱ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የራስ አስተዳደርን ለማቋቋም
የሚያስችላቸው መሆኑን፤ በሌላ በኩል ደግሞ በፌዴራል እና በክልል መስተዳድሮች ሚዛናዊ ውክልና እንደሚኖራቸው በመደንገግ የራስ አስተዳደርን
እና የጋራ አስተዳደርን ስርዓቶች በማጣመር ስራ ላይ የሚውሉበትን ህገ መንግስታዊ መሰረት ይጥላል።
የራስን
ዕድል በራስ የመወሰን መብት ፅንሰ ሃሳብ ውስጥ የተካተተው ሶስተኛው ጉዳይ የመገንጠል መብት ነው። የዚህ መብት ህገ መንግስታዊ
ዕውቅና ያስፈለገበትን ምክንያት ለመረዳት በህገ መንግስቱን መግቢያ ላይ በደንብ የሰፈረ ይመስለኛል። ይኸውም የኢትዮጵያ ብሔሮች፣
ብሔረሰቦችና ህዝቦች አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ ለመመስረት በህገ መንግስቱ የወሰኑት በራሳቸው ነፃ ፍላጎት እንደሆነና የሚገነቡትም
አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ በራሳቸው ፈቃድ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ይገልፃል። የሚገነባው ማህበረሰብም በእያንዳንዱ ብሔር፣ ብሔረሰብና
ህዝብ ፈቃድና ፍላጎት ላይ ብቻ የተመሰረተ ነው። በመሆኑም የመገንጠል መብት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መሰረት የህዝቦች ፈቃድና
ፍላጎት መሆኑን የሚያበስርና ዋስትና የሚሰጥ መብት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።
ይሁንና
ይህ “የመገንጠል መብት” አንቀፅ በአንዳንድ ወገኖች በበጎ መልኩ አይታይም። እነዚህ ወገኖች ይህን መብት “ሀገርን የሚገነጣጥል
ነው” ሲሉም ይቃወሙታል። ሆኖም ቀደም ሲል ለመጥቀስ እንደሞከርኩት አንቀፁ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በመፈቃቀድና በአንድነት
መኖር የሚያስችላቸውን ዴሞክራሲያዊ አንድነት ዕድልንም አብሮ የሚሰጥ ነው። እርግጥ ይህን ዴሞክራሲያዊ አንድነት ለመፍጠር ህዝቦች
የእኩልነት መብታቸው መከበር ይኖርበታል። በመሆኑም በአንፀቁ አማካኝነት የእኩልነት ማረጋገጫ የሆኑት የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች
ቋንቋዎች፣ ባህሎች፣ ታሪኮች…ወዘተ. ተከብረዋል። ከሁሉም በላይ ደግሞ በፖለቲካው አስተዳደር በኩል እኩል የመሳተፍ መብት ያገኙ
ሲሆን፤ በልማት ስራው ላይም እኩል የመሳተፍ መብት እንዲያገኙና በውጤታቸው መሰረት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል።
እርግጥም
እነዚህን ሁሉ መብቶች ያረጋጋጠ ማንኛውም ብሔር፣ ብሔረሰብና ህዝብ ከፌዴሬሽኑ ሊገነጠል የሚችልበት ምክንያት ሊኖረው የሚችል አይመስለኝም።
ቀደም ሲል የጠቀስኳቸው መብቶች ባለቤት በመሆኑም ጥቅሞቹን እያጣጣመ የፌዴራል ስርዓቱን ያጠናክራል እንጂ፤ በምን ዓይነት የሂሳብ
ቀመር ሊበታተን እንደሚችል አይገባኝም። እናም በአንቀፁ ላይ ስጋት እንዳላቸው የሚገልፁ አንዳንድ ወገኖች ቀደምት በኃይል ላይ የተመሰረቱ
አሃዳዊ ስርዓቶችን ከመናፈቅ የመነጨ ካልሆነ በስተቀር እስካሁን ድረስ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የመበታተንን ስጋት የሚያሳይ አይደለም።
ከዚህ ይልቅ ፌዴራላዊ ስርዓቱ ዴሞክራሲያዊ አንድነትን እያጠናከረ ዛሬ ላይ መድረሱን የሚያሳይ ነው። በመሆነም በእኔ እምነት አንቀፁ
የአንድነታችን ዋስትና እንጂ የመበታተናችን ስጋት ሊሆን አይችልም። በመሆኑም አንቀፁ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችንና ህዝቦችን የራስን
ዕድል በራስ የመወሰን መብት እስከ መገንጠል መብት የሰጠ ቢሆንም ቅሉ፤ ዓላማው በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ አንድነትን ማረጋገጥ
መሆኑን መገንዘብ የሚገባ ይመስለኛል።
No comments:
Post a Comment