ዮናስ
የኢህአዴግ
ስራ
አስፈፃሚ
ኮሚቴ
ከነሃሴ
10-15/2008 ዓ.ም
ድረስ
ባካሄደው
መደበኛ
ስብሰባ
ያለፉትን
አስራ
አምስት
ዓመታት
የለውጥ
ጉዞ
በመገምገም
በአንድ
በኩል
በእስካሁኑ
ትግል
የተመዘገቡ
ውጤቶችን
አጠናክሮ
ለመቀጠል፣
በሌላ
በኩል
ደግሞ
ልማታዊና
ዴሞክራሲያዊ
ስርዓቱን
የሚፈታተኑ
ችግሮችን
በመቅረፍ
የህዝብ
መብትና
ተጠቃሚነትን
ለማጎልበት
የሚያስችሉ
ውሳኔዎችን
ማሳለፉን
የተመለከተ መግለጫ አውጥቷል፡፡ ይህ ተረክም ሃገሪቱ ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ ተነስቶ የስራ
አስፈጻሚውን ግምገማ ያሄሳል ።
ስራ አስፈፃሚ
ኮሚቴው
በድርጅቱ
የቀረበውን
የአስራ
አምስት
ዓመታት
የለውጥ
ሂደት
የሚመለከት
የግምገማ
ሃሳብ
መነሻ
በማድረግ
በዚህ
ሂደት
በአገራችን
የተመዘገቡ
አዎንታዊ
ለውጦችና
በተጨባጭ
የሚታዩ
ድክመቶችን
በዝርዝር
መገምገሙን
ቢያወሳም አሁን ካለንበት ተጨባጭ እና ከሃገሪቱ ሰላምና ጸጥታ ጋር ተያይዞ በመግለጫው የተመለከተው ግን ከችግሩ አንጻር ሚዛን
ደፍቶ አላገኘሁትም፡፡
በዚህ ግምገማ
ስለተገለጸ ብቻ
ሳይሆን
በተጨባጭም
መላ
ህዝብ
አገራችን
ላለፉት
አስራ
አምስት
ዓመታት
በሁሉም
የህይወት
መስኮች
ከፍተኛ
ለውጥ
እያመጣች
በመሆኑ
ላይ ልዩነት ይኖረዋል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ለማንም
ግልፅ
እንደሚሆነው
በአገራችን
ታሪክ
ለመጀመሪያ
ጊዜ
ህገ
መንግስታዊ
ዴሞክራሲያዊ
የፖለቲካ
ስርዓት
ግንባታ
በመካሄድ
ላይ
ነው፡፡
በዚህ
የዴሞክራሲያዊ
ፖለቲካዊ
ስርዓት
ግንባታ
ሂደት
የዜጎችና
የልዩ
ልዩ
ማህበረሰቦች
የፖለቲካ
መብቶች
ህጋዊ
እውቅናና
ዋስትና
አግኝተው
ተከብረዋል፡፡
የብሄር
ብሄረሰቦችን
ማንነት
ያስከበረ
አዲስ
ዓይነት
ፌደራላዊ
የእኩልነት
ስርዓት
ተገንብቷል፡፡
የሃይማኖት
እኩልነት
ተከብሮ
መንግስትና
ሃይማኖት
ተነጣጥለዋል፡፡
የዜጎችና
የመላ
ህዝባችን
ሰብዓዊና
ዴሞክራሲያዊ
መብቶች
እንዲከበሩ
ቅድሚያ
ሰጥቶ
የተጀመረው
የዴሞክራሲያዊ
ስርዓት
ግንባታ
ህዝብ
የሚጠቀምበት
ማህበራዊና
ኢኮኖሚያዊ
ስርዓት
በመገንባት
ረገድ
ረጅም
ርቀት
ተጉዟልና፡፡
ይህ ብቻ አይደለም በግምገማው እንደተመለከተውም በገጠርም
ይሁን በከተማ የተባሉት ውጤቶች መመዝገባቸውን የሚክድም ካለ የዜሮ ድምር ፖለቲካ ሰለባ ብቻ ነው የሚሆነው። ድርጅቱ ያወጣው
ግምገማውን የተመለከተው መግለጫ የ5ቱ ቀናት ግምገማ አሁን የገጠሙንን ግጭትና ትርምሶች ብዙ ቦታ ሳይሰጥ የተመዘገቡ ድሎች ላይ
ሰፊ ጊዜ የወሰደ መሆኑን ማመላከቱ ነው የዚህ ሂስ መነሻ።
የኢህአዴግ
ስራ
አስፈፃሚ
ኮሚቴ
ባካሄደው
ግምገማ
መሰረት
ባለፉት
15 ዓመታት
እነዚህና
እነዚህን
የመሳሰሉ
በርካታ
ውጤቶች
ሊገኙ
እንደቻሉ
ማረጋገጠን
ይዘረዝርና
ይህም
በአገራችን
ዋነኛ
ተልዕኮው
ህዝብን
ማገልገልና
በዚህ
ቅኝት
መንቀሳቀስ
እንጂ
የግል
መጠቀሚያ
ያልሆነ
መንግስት
ለመገንባት
የተደረገው
ጥረት
ያስገኘው
መልካም
ዕድገት
እንደሆነም
አስምሮበት
ሲያበቃ፡፡
በአሁኑ ጊዜ
ልማታዊ
ዴሞክራሲያዊ
ስርዓቱን
ከሚፈታተኑት
ችግሮች
መካከል
አንዱ
የመንግስት
ስልጣን
የህዝብን
ኑሮ
ለማሻሻልና
አገራዊ
ለውጡን
ለማስቀጠል
እንዲሆን
ከማድረግ
ይልቅ
የግል
ኑሮ
መሰረት
አድርጎ
የመመልከትና
በአንዳንዶችም
ዘንድ
የግል
ጥቅም
ከማስቀደም
ጋር
የተያያዘ
እንደሆነ
ስለማረጋገጡ
ማውሳቱ ግራ አጋቢና እርስ በእርስ የሚጣረስ፤ ለነገሩ የሰጠውን አነስተኛ ቦታም የሚያጠይቅ ነው፡፡ ለነገሩ ስለሰጠው አነስተኛ
ቦታ ለማሄስም ድርጅቱ በድረ ገጹ ላይ ካሰፈረው መግለጫ ተከታዩን ነጥብ መመልከት በቂ ነው።
አገራዊ ለውጡ በስኬት ሲጓዝ የቆየው መንግስታዊ ስልጣንን ለህዝብ ጥቅም ማስከበሪያ ማድረግ በመቻሉ የሆነውን ያህል ይህ ስልጣን ያለአግባብ ለመጠቀም ለሚሹ ግለሰቦች በመሳሪያነት ማገልገል ሲጀምር የተጀመረው ልማት ይደነቃቀፋል፡፡ መልካም አስተዳደርም ይጠፋል፡፡
በአሁኑ ጊዜ ህዝብን በማስመረር ላይ ያለው ችግር ዋነኛ መንስዔ ይህ ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ደረጃውና መጠኑ ምንም ይሁን ምን የመንግስት ስልጣንን ካለ ያለአግባብ ለግል ኑሮ መሰረት ለማድረግ የሚታየው ዝንባሌና ስህተት መታረምና መገታት እንዳለበት፣ ይህን ለማድረግ የሚያስችል ተጨማሪ እርምጃም መውሰድ እንዳለበት ወስኗል፡፡ ዝንባሌው በሚታይባቸው ቦታዎች ሁሉ በአግባቡ እየተፈተሸ እንዲስተካከልና የድርጅታችን ጥራትና ጥንካሬ ተጠብቆ እንዲቀጥል አስፈላጊ የሆነው ርምጃ ሁሉ እንዲወሰድ ወስኗል፡፡ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በዚህ ረገድ ከራሱ ጀምሮ የሚታዩ የጥገኝነት አስተሳሰቦችና መገለጫ የሆኑትን ጠባብነትና ትምክህተኝነት እንዲሁም የጥገኝነት ተግባራትን በጥብቅ በመታገል ይህ አዝማሚያ እንዲገታ ለማድረግ የሚያስችሉ ዝርዝር ዕቅዶችም አዘጋጅቷል፡፡
ከ6ተኛው ዙር የድርጅቱ ጉባኤ ጀምሮ
ዛሬም እቅድ ተዘጋጅቷል የሚል ሃሳብ ጉንጭ አይነፋም። በመልካም
አስተዳደር ጉዳይ ላይ መንግስትና ገዥው ፖርቲ በየወቅቱ የተለያዩ ዕቅዶች በማዘጋጀትና ስልቶችን በመንደፍ ምላሽ ለመስጠት
ጥረት እንደሚያደርጉ ተነግሮን የነበረው የዛሬ 8 አመት ግድም ነው፡፡ እንዲሁም የመሪው ፓርቲ የዛሬ 8 አመት 6ኛው
ድርጅታዊ ጉባኤውን ዋና ስያሜ ”እመርታ በመልካም አስተዳደር” ብሎም በማከናወን ንቅናቄ ለመፍጠር ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑንም
ነግሮን የነበረ መሆኑ ሲታወስ ዛሬም እቅድ አዘጋጅቻለሁ ማለቱ ግራ ገብ ይሆናል፡፡ በእርግጥ በእነዚህ ጥረቶች የመጡ ከአካባቢ አካባቢ
የሚለያዩ የተሻሻሉ ጉዳዩች እንደተጠበቁ ሆኖ አሁንም በፌዴራልም ሆነ በክልል ተቋማት የሚታየው የመልካም አስተዳደር ችግር ለነገ
ሳይባል ሊፈታ የሚገባውና ተመጣጣኝ የሆነ የአመራር ትኩረት የሚሻ መሆኑን በ10ኛው ጉባኤው የነገረን ኢህአዴግ የጥፋት ሃይሎች የሚፈጥሩት ሴራ ከህዝቡ ምሬት ጋር ተዳምሮ ስጋታችን
ባሻቀበበት ሰአት ላይ ዛሬም እቅድ አዘጋችቻለሁ ማለቱ ግራ ቢያጋባን እንጂ ወደን አይደለም፡፡
በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ረቂቅ ዕቅድ ላይ በተካሄዱ
ውይይቶች ወቅት ከሞላ ጐደል በአብዛኛዎቹ መድረኮች የመልካም አስተዳደር ጉዳይ በጣም ያወያየ፣ ለዕቅዱ መሳካት እንቅፋት ይሆናል
ተብሎ በስጋት መልክም የቀረቡ፣ እውነት ትፈታላችሁ ወይ? የተባለ እና በብዙ መልኩ በሚገለጽ አግባብ ጐልቶ የወጣ ጥያቄ መሆኑን
ካመነና አምኖም በመቀበል ሊተጋ ዝግጁ መሆኑን በይፋ ካረጋገጠ ድርጅት ዛሬም ስለእቅድ መዘጋጀት መስማት ያማል፡፡ ለምን ቢባል በችግሩ
መኖር ላይ ምንም የሚያጠያይቅ ነገር እንደሌለ በየአመቱና በተደጋጋሚ የነገረን እርሱው፤ አመራሩ የችግሩን መኖር ያውቀዋል ወይ?
ከተባለም ይህ የሚያጠያይቅ ነገር እንዳልሆነም ያወሳልነ እርሱው፤ አመራሩ የችግሩን ስፋት፣ ጥልቀት፣ አንገብጋቢነት፣ አደጋውን በደንብ
ተገንዝቧል ወይ? ከተባለ ግን ይኸ በዝርዝር ማየትን የሚጠይቅ ነው ብሎን የነበረው እርሱ፡፡ አመራሩ ያወቃቸውን የገመገማቸውን የመልካም
አስተዳደር ችግሮች በብቃት እየፈታ ነው ወይ? ከተባለ በርካታ ችግሮች ያሉበት መሆኑንም የተነተነልን እርሱ፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ
አመራሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መኖራቸውን አውቆ ሲያበቃ፣ በሱፐርቪዥንም አረጋግጦ ሲያበቃ፣ ህዝቡም በየመድረኩ ነግሮት ሲያበቃ
ከወር ወር፣ ከአመት አመት ችግሮቹ በተሟላ መልኩ የማይፈቱበት ምክንያትና መንስኤው ምን እንደሆነ በዝርዝር መታወቅ እንዳለበት
ማስመሩንም የነገረን እርሱ፡፡ ስለሆነም የጥፋት ሃይሎች በመልካም አስተዳደር እጦት የተገፋን ህብረተሰብ ለሌላ እና ጽንፈኛ ፖለቲካ
ማራመጃ አጀንዳ እያዋሉት መሆኑ በተጨባጭ እየታየ ባለበት በዚህ ወቅት ከስራ አስፈጻሚው ግምገማ መስማት የሚገባን እና የስራ አስፈጻሚው
ልዩ የግምገማ ትኩረት መሆን የነበረበት በዝርዝር መታወቅ አለባቸው ሲል የነገረን እና ከላይ ማነቆነታቸው እንደማያጠያይቅና የስጋታቸውም
ልክ ገደብ እንዳለፈ የተመለከቱት አጀንዳዎች ናቸው ወይስ ስላለፉት 15 አመታት የምናውቃቸውን እና እየኖርንባቸው ያሉትን የልማት
ውጤቶች?።
ዛሬም በድጋሜ :-
ባለፉት ዓመታት በአገራችን የህዝብ መብትና ጥቅም ቅድሚያ አግኝቶ የተከበረበት ስርዓት ለመገንባት ባካሄድነው ትግል ካላግባብ የመጠቀም ዝንባሌ ወይም ኪራይ ሰብሳቢነት ትልቁ ፈተናችን እንደሆነ ለአፍታም ቢሆን ሳይነሳ የቀረበት ጊዜ የለም፡፡ መላው የአገራችን ህዝቦችም ቢሆኑ ካላአግባብ መጠቀም የሚሹ ሰዎች የመንግስት ስልጣንን የግል ብልፅግና ማረጋገጫ ለማድረግ በመሻት በሚፈጥሩት እንቅፋት የለመለመ ተስፋቸው ለአደጋ ሊጋለጥ እንደሚችል ያላነሱበት ጊዜ የለም፡፡
ሲል በመግለጫው
የሚነግረን ኢህአዴግ። በመቀጠልም :-
…… የተጀመረው አገራዊ የለውጥ እንቅስቃሴና እንደገና የመታደስ ጥረት ለላቀ ፍሬ እንዲበቃ መላ የአገራችን ህዝቦች ሰላማዊና ህጋዊ ትግላቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ በዚህ አጋጣሚ የውጭም ሆነ የውስጥ ፅንፈኛ ፀረ ሰላምና ፀረ ልማት ኃይሎች ህዝቡ በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ትግሉ የገነባውን ስርዓት በቀጣይነት ለማሻሻል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ መጠጊያ አድርገው ሁከትና ትርምስን ለማስፋፋት የሚያደርጉትን ጥረት በፅናት እንዲመክትና በሀገራችን ህዝቦች ብሔሮችና ብሔረሰቦች መካከል ያለውን መልካም ግንኙነትና አብሮነት በአስነዋሪ የዘረኝነት ፕሮፓጋንዳቸው ለማላላት የሚያደርጉትን አፍራሽ እንቅስቃሴ እንዲያመክነው ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ሲል ላቀረበው ጥሪ ይሁንታ የሚበቃ ምላሽና ግምገማ
ለማድረግ ስለምን እንደተሳነው እና በየጊዜው የሚዝትባቸውን ቀበኞች በማስወገድ ቀዳዳውን ለመድፈን ስለምን አዲሱን አመት መጠበቅ
እንዳሻው ሰአታትን እና ደቂቃዎችን ለትርምስ አጀንዳ ከመጠቀም ከማይቦዝኑቱ የጥፋት ሃይሎች አኳያ ሲሰላ ግራ አጋቢና ምናልባትም
ኪሳራ ነው። ህብረተሰቡና መንግስት በታችኛው መዋቅር ጸረ ህዝባዊነት እና ኪራይ ሰብሳቢነት እንደተራራቁ በሚታወቅበትና ከላይ
በተመለከተው አግባብ ነጥሮ የወጣ አደጋ መሆኑ በሚታወቅበት አግባብ በከተሞች እና በገጠሩ ከጥቃቅን እና አነስተኛ እንዲሁም
ከስራ እድል ፈጠራ ጋር ተያይዞ ተመዝግቧል በሚል በሪፖርቱ የተመለከተውንም ለመቀበል አዳጋች ነው። ወይ በታችኛው መዋቅር
ሪፖርት የተንሸዋረረ ነው ወይም ደግሞ በአምቻ ጋብቻና ብልሹ አሰራር ተጠላልፎ የተከናወነ ዘላቂነት የማይኖረው ውጤት ነውና
እንደገና በጥልቀት ሊፈተሽ ይገባል። ለምን ቢሉ እያልን ያለውና የግምገማው ውጤት አራባና ቆቦ መሆናቸው ስለማያከራክር።
No comments:
Post a Comment