ኢብሳ
ነመራ
ሰሞኑን የዓለም የቱሪዝም ቀን እየተከበረ ይገኛል። የዓለም የቱሪዝም
ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ37ኛ ግዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ29ኛ ግዜ ነው በመከበር ላይ የሚገኘው። ኢትዮጵያን
ጨምሮ
157 አገራትን
ያቀፈው
የዓለም
የቱሪዝም
ድርጅት
የሚያከብረው
የዓለም
አቀፍ
የቱሪዝም
ቀን
ዘንድሮ በታይላንድ
ዋና
ከተማ
ባንኮክ
ነው
የሚከበረው፡፡
በኢትዮጵያም ባለፉት
ዘጠኝ ዓመታት በተለያዩ ክለሎች ሲከበር የቆየው የዓለም የቱሪዝም ቀን ዘንድሮ በአዲስ አበባ ነው የተከበረው። ዕለቱ “ቱሪዝም ለሁሉም፣ ዓለም አቀፍ ተደራሽነትን ማረጋገጥ” በሚል መሪ
ሃሳብ
ነው በመከበር
ላይ የሚገኘው። በአሉን አስመልክቶ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ኢንጂነር
አይሻ
በሰጡት መግለጫ
የአገሪቱን
የቱሪዝም
ዘርፍ
ለማሳደግ
የአፈጻጸም
አቅምን
ማጠናከር
እንደሚገባ
አሳስበዋል። ፖሊሲና ስትራቴጂን
መሰረት
ባደረገ
መልኩ
ቱሪዝምን
ለሁሉም
ዜጎች
ተደራሽ
ለማድረግ
መስራት
ይገባልም ብለዋል።
በሃገር አቀፍ ደረጃ የዓለም የቱሪዝም ቀንን የሚያከብረው የአዲስ
አበባ
ከተማ
አስተዳደር
ባህልና
ቱሪዝም
ቢሮ ዕለቱ በከተማዋ
በተለያዩ
አቅጣጫዎች
የሚገኙ
ታሪካዊ፣
ባህላዊና
ተፈጥሯዊ
ቅርሶችን
በመጎብኘት
እንዲከበር
አድርጓል።
እስከ መስከረም
21 በሲምፖዚየም፣ በቁንጅና እና
ስፖርታዊ
ውድድሮች፣
የቱሪዝም
መዳረሻና
የልማት
ቦታዎችን
በመጎብኘት
ነው የሚከበረው።
ወደ አጠቃላይ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ኢንደስትሪ ስንመለስ ከቅርብ
ግዜ ወዲህ እመርታ ሊባል የሚችል እድገት ማሳየቱን መረጃዎች ያመለክታሉ። በዚህ በኢትዮጵያ በቱሪዝም ኢንደስትሪ ዙሪያ በቅርቡ ከውጭ
ጉዳይ ሚኒስትር የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው በ2008 ዓ/ም 104 አለማቀፍ
አስጎብኚ
ድርጅቶች
ኢትዮጵያን የቱሪዝም
ፓኬጃቸው
ውስጥ
አስገብተዋታል።
የውጭ
ጉዳይ ሚኒስቴር የውጭ ሀገር ዜጎች ኢትዮጵያን እንዲጎበኙና የመዝናኛ
መናኸሪያቸው
እንድትሆን
በቀጥታ
ከማስተዋወቅ
በተጨማሪ
ከአለም
አቀፍ
አስጎብኝ
ኩባንያዎች
ጋር
በቅርበት
እነደሚሰራም
አስታውቋል።
ይህ የሚንስቴር መሰሪያ ቤቱ ስራ 104 አስጎብኚ ኩባንያዎች ለማስጎብኘት
ከሚፈልጓቸው
የዓለም አካባቢዎች መሃከል ኢትዮጵያን አንዷ አድርገው እንዲመርጧት አስተዋጽኦ አበርክቷል። ይህ ባለፈው ዓመት ከቱሪዝም
ኢነደስትሪ የተገኘው ገቢ ከምንግዜውም የበለጠ እንዲሆን አስተዋጽኦ አበርክቷል።
የኢፌዴሪ
መንግስት ለቱሪዝም ኢንደስትሪ ዘርፍ ልዩ ትኩረት ሰጥቷል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራና የየክልል መንግስታትን ርእሰመስተዳድሮች
በአባልነት ያካተተ የቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት መቋቋሙ ለዚህ በቂ አስረጂ ነው። በዚህ ጽሁፍ የኢፌዴሪ መንግስት ለቱሪዝም
ኢንደስትሪ የተሰጠው ትኩረትና የኢንደስትሪውን ቀጣይ መድረሻ በመጠኑ በአንድ አጭር ጽሁፍ ለመመልከት የሚቻለውን ያህል ለማሰቃኘት
አሞክራለሁ።
እንግዲህ
ስለቱሪዝም ኢነደስትሪ ሲነሳ ቱሪዝም ምንድነው? የሚለው ጥያቄ መነሳቱ ሰለማይቀር የቱሪዝምን ፍቺ ከመመልከት እንጀምር። ቱሪዝም በርካታ ትርጉሞች
ተሰጥቶታል። ለዚህ ፅሁፍ ዓላማ በተባበሩት መንግስታት የዓለም የቱሪስዝም
ድርጅት (United
Nations Worled Tourizm Organazation UNWTO) የሰጠውን ትርጉም የሃሳቡ ወካይ ሆኖ ሰላገኘሁት ልጠቀሰው
ወድጃለሁ።
የዓለም የቱሪዝም ድርጅት ለቱሪዝም የሰጠው ፍቺ ቱሪዝም
ጎብኚ ተብለው በተለዩ ሰዎች የሚፈፀም ድርጊት ነው። ጎብኚ በመደበኛነት ከሚኖበት አካባቢ ተነስቶ ቢያንስ ለአንድ ዓመት ቆይታ
በአል ማክበርን፣ ግዜ ማሳለፍና መዝናናትን፣ ስራን፣ ህክምናን፣ ትምህርትን፣ ጨምሮ ለተለያዩ ጉዳዮች ወደሌላ መዳረሻ የሚጓዝ
ሰው ማለት ነው። ይላል።
እግዲህ ቱሪዝምና ቱሪስት ይህ ከሆነ አንድ ሃገር ወይም አካባቢ ከዘርፉ ገቢ
ለማግኘት ከላይ ለተጠቀሱት ዓላማዎች ወደዚያ ሃገር ወይም አካባቢ ለጉብኝት ከሚመጡ ሰዎች የሚገኝ ነው። ገቢው ወደዚያ ሃገር
በሚመጡ ቱሪስቶች ወይም ጎብኚዎች ቁጥር ልክና በዚያ ሃገር በሚኖራቸው ቆይታ ልክ የሚወሰን ይሆናል። ጎብኚዎች ወደአንድ
ሃገር እንዲጓዙና በዚያ እንዲቆዩ የማድረግ ጉዳይ ግን ቀላል
አይደለም። በተፈጥሮ መሰጠትንም ጥረትንም ይጠይቃል። ስጦታው በተፈጥሮ የሚገኝ የሰዎችን ቀልብ የሚማርክ፣ ለምርምር የሚገፋፋ
ወዘተ ጸጋዎችን (ወንዝ፣ ሃይቅ፣ መልከዓምድራዊ አቀማመጥ፣ የአየር ንብረት፣ ደን፣ እጸዋትና እንስሳት፣ . . .)፣ ባህል፣
ወግና ቋንቋ፣ ታሪክና ታሪካዊ ቅርሶችን ያጠቃልላል።
እነዚህ በተፈጥሮ የሚታደላቸው ስጦታዎች ግን በራሳቸው ቱሪስቶችን ለመሳብና
ለማሰንበት በቂ አይደሉም። ከማስተዋወቅ ጀምሮ የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትና መሰረተ ለማቶች ያስፈልጋሉ። እነዚህም
የተለያዩ ሃገራት ዜጎች ለትምህርትና ለጤና አገልግሎት፣ ለምርምር እንዲመጡ ማድረግ የሚያስችሉ ጥራት ያለው አገልግሎት የሚሰጡ
ተቋማት፣ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን ማካሄድ የሚያስችሉ መሰረተ ልማቶች (ሁለገብ አዳራሾችና ሆቴሎች)፣ ሰላምና ፀጥታ፣ የመጓጓዣ፣
የመገናኛ መሰረተ ልማቶች፣ . . . ያጠቃለላሉ።
በኢትዮጵያ ወዳለው ሁኔታ ስንመለስ ሃገሪቱ በቂ ሊባል የሚችል የተፈጥሮና ታሪካዊ
ቅርሶች ባለቤት ነች። በተባባሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (The
United Nations
Educational, Scientific and Cultural Organization _UNESCO) የተመዘገቡ ቅርሶች ለዚህ አስረጂነት ሊጠቀሱ ይችላሉ።
እስካሁን በዩኔስኮ የተመዘገቡት የኢትዮጵያ ታሪካዊና የተፈጥሮ ቅርሶች አስራ አንድ ደረሰዋል፤ የሚጨበጡና የማይጨበጡ ቅርሶች። በሚጨበጡት
ወገን የአክሱም ሃውልቶች፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የጎንደር አብያተመንግስት፣ የሃረር ጆጎል ግምብ፣ የጢያ ትክል
ድንጋዮች፣ የሰሜን ብሄራዊ ፓርክ፣ የኮንሶ ሰው ሰራሸ የመሬት አቀማመጥ፣ የታችኛው አዋሽ ሸለቆ፣ የታችኛው ኦሞ ሸለቆ የገኛሉ።
በማይጨበጥ ቅርስ ወገን ደግሞ ሰሞኑን ያከበርነው የደመራና የመስቀል በአል፣ የሲዳማ የዘመን መለወጫ - ፊቼ ጨምበላላ ናቸው።
ሌሎች በምዝገባ ሂደት ላይ ያሉም አሉ። ከእነዚህ መሃከል የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ፣ የድሬ ሼህ ሁሴን መስጊድ፣ የሶፍ ኡመር
ዋሻ፣ የጌዲዮ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ መልከዓምድር፣ የማልካ ከንቱሬ
የአርኪዮሎጂ ስፍራ፤ ከባህላዊ ቅርሶች ደግሞ የኦሮሞ የገዳ ስርአት፣ የትግራይና የአማራ ክለሎች የአሸንዳና የሻይዳ
በአል ይገኙበታል። የኦሮሞዎች የዘመን መለወጫና የምስጋና በአል - ኢሬቻና የሌሎች ብሄረሰቦች ባህሎችንም የማስመዘገብ ጉዳይ
ተኩረት ተሰጥቶታል።
ከዚህ
በተጨማሪ ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ ሃገር ነች - ከ3 ሚሊየን ዓመታት በላይ እድሜ ያስቆጠረው የሉሲ ወይም ድንቅነሽ አፅም
መገኛ ሃገር። ኢትዮጵያ የአረቢካ ቡና ዝርያ መገኛ ሃገርም ነች። የዓለማችን ረጀሙ ወንዝ የጥቁር አባይ ወንዝ ምንጭም ነች።
የኤርታአሌ የእሳተ ገሞራ ሀይቅ፣ የዓለማችን እጅግ ረባዳና ሞቃት ስፍራ የሆነው ዳሎል በኢትዮጵያ ይገኛል። ኢትዮጵያ የንግስት ሳባ ሃገር ነች፣ የሙሴ ፅላትም በኢትዮጵያ ይገኛል
ተበሎ የታመናል - በአክሱም ፅዮን ቤተክርስቲያን። በሚገባ የመልማታቸው ጉዳይ አሁንም ጥያቄ መሆኑ ሳይዘነጋ ለመዝናናት አመቺ
የሆኑ በርካታ የስምጥ ሸለቆ ሃይቆችና ፍልውሃዎች፣ እንዲሁም የዱር እንስሳት ፓርኮችና ማቆያዎች ባለቤትም ነች።
ኢትዮጵያ በርካታ ተፈጥሯዊ፣ ሰው ሰራሽና ባህላዊ ቅርሶችን
በዩኔስኮ በማስመዝገብ በአፍሪካ ቀዳሚዋ ሃገር ለመሆን በቅታለች። ሌሎችም በርካታ የቱሪዝም መስህቦች ባለቤት ሃገር ነች። የኢትዮጵያ
የቱሪዝም ኢንደስትሪ ግን ሃገሪቱ በተፈጥሯዊ፣ ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶች የበለፀገችና የቱሪስት መስህብ ያላትና እነዚህን ቅርሶች
በበዛት በማስመዝገብም ከአፍሪካ ሃገራት ቀዳሚ የመሆኗን ያህል አላደገም። ኢትዮጵያ በጎብኚዎች ቁጥር ከአፍሪካ 17ኛ ከዓለም
ደግሞ 121 ደረጃ ላይ ነው ተየምትገኘው። በዩኔሰኮ በተመዘገቡ ቅርሶች ብዛት ከኢትዮጵያ የሚያንሱ ሆነው በበጎብኚዎች ቁጥር
ግን ከኢትዮጵያ የሚበልጡ የአፍሪካ ሃገራት አሉ።
ኢትዮጵያን የጎበኙ ቱሪስቶችን ቁጥርና ከዚህ የተገኘውን ገቢ
መለስ ብለን ስንመለከት፣ በ2004 ዓ/ም አፍሪካን ከጎበኙት 52 ነጥብ 3 ሚሊየን ቱሪስቶች መሃከል ወደኢትዮጵያ የመጡት 596
ሺህ 341 ብቻ ናቸው። ከአነዚህ የአፍሪካ ጎብኚዎች የተገኘው አጠቃላይ ገቢ ደግሞ 34 ቢሊየን ዶላር ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ
ኢትዮጵያ ያገኘችው 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ገደማ ብቻ ነው። ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው በ2006
የበጀት ዓመት ከቱሪዝም ዘርፍ የተገኘው ገቢ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ነው። ይህ ገቢ የተገኘው 600 ሺህ ከሚሆኑ
ጎብኚዎች ሲሆን፣ የገቢው መጠን ከዚያ ቀደም ከነበረው ዓመት ጋር ሲወዳደር በ35 በመቶ ገደማ ብልጫ አሳይቷል።
ቀደም ሲል በጽሁፌ መግቢያ ላይ እንዳነሳሁት የኢፌዴሪ መንግስት የቱሪዝም ኢንደስትሪውን ለዜጎች የስራ እድል ፈጠራና
የውጭ ምንዛሪ ምንጭ እንዲሆን ለማስቻል ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ሰጥቷል። በዚሁ መሰረት የቱሪዝም ዘርፉን ለማልማት ከባህልና ቱሪዝም
ሚኒስቴር በተጨማሪ የቱሪዝም ድርጅትና በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ የቱሪዝም ትራንስፎረሜሽን ምክር ቤት ተቋቁሟል።
በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው የቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን ምክር
ቤት የተቋቋሙበት ዓላማ ዘርፉን ወደላቀ ደረጃ ማሸጋገር ነው።
ምክር ቤቱ የተለያዩ ተቋማትና ታዋቂ ግለሰቦች ተወክለውበታል። እነዚህም የየክልሎቹ ርእሳነ መሰተዳድር፣ የአዲስ አባበና
የደሬደዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አሰፈፃሚ፣ የኢትዮጵያ ቱሪስት አሰጎብኚ ድርጅት
ፕሬዝዳንት፣ የኢትዮጵያ ሆቴሎችና ምግብ ቤቶች ማህበር፣ የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት፣ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮችና
ታዋቂ ግለሰቦች ናቸው።
የቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት ተግባራት በብሄራዊ ፓርኮች ያለውን የመሰረተ ልማት ደረጃ ማሻሻል፣ ፓርኮችና ሎጆችን
ከዋና መንገድ ጋር የሚያገናኙ መጋቢ መንገዶችን ደረጃ ማሻሻል፣ እንዲሁም በፓርክና በእንስሳ መጠበቂያ የሚገኙ የዱር እንሰሳ
አደንን መከላከል፣ ቅርሶች የሚገኙበትን አካባቢ መጠበቅና የመሳሰሉ ናቸው። ከዚህ በተጓዳኝ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የተፈጥሮና
ባህላዊ ቅርሶችን በመንከባከብና በማልማት፣ የባህልና የቱሪዝም ቁሳቁሶችን ለገበያ በማቅረብ፣ የአገልግሎት አሰጣጥን የላቀ በማድረግ፣
የባህልና የቱሪዝም የመረጃ ስርአት በማሻሻል፣ እንዲሁም የልማት አጋሮችን በማቀናጀት የሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎረሜሽን
እቅድ ማብቂያ ዘመን ላይ በአፈሪካ በቱሪስት መዳረሻነት 5ኛ ደረጃ ላይ ለመድረስ እየሰራ ይገኛል።
ታዲያ ይህ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው የቱሪዝም
ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት እስካሁን 3ኛ ጉባኤዎችን አካሂዷል። ከሶስት ወራት በፊት ሰኔ 2008 ዓ/ም የተካሄደውን የምክር ቤቱን 3ኛ ጉባኤ የመሩት ጠቅላይ
ሚኒስትር ሃይለማርያም፣ በቱሪዝም ዘርፍ
መዋቅራዊ
ለውጥ
ለማምጣት
ክልሎችና
ባለድርሻ
አካላት
ስር
ነቀል
ለውጥ
የሚያመጣ
ስራ
መስራት
እንዳለባቸው
አሳስበዋል።
ኢትዮጵያ
ያላትን
እምቅ
የቱሪዝም
ሀብት
በማልማት
ከዘርፉ
ማግኘት
የሚገባትን
ጥቅም
እንድታገኝ
ሁሉም
አካላት
መስራት
እንደሚጠበቅባቸውም
አሳስበዋል።
በተለይም
ሁሉም
ክልሎች
እና
ሁለቱም
የከተማ
መስተዳድሮች
በዘርፉ
ስር
ነቀል
ለውጥ
እንዲመጣ
ትኩረት
ሰጥተው
እንዲሰሩ
ጥሪ
አስተላልፈዋል።
በነገራችን ላይ በዚህ በያዘነው መሰከረም ወር አራት ክልላዊ
መንግስታት
ማለትም የኦሮሚያ፤
የአማራ፤
የትግራይ
እና
የደቡብ
ብሄሮች፣ በሄረሰቦችና ህዝቦች
የየራሳቸውን
የቱሪዝም
መሪ
እቅድ
አዘጋጅተው
መጨረሳቸውን
የባህልና
ቱሪዝም
ሚኒስቴር
አስታውቋል።
አራቱ
ክልሎች
የየራሳቸውን
የቱሪዝም
መሪ
እቅድ
ማዘጋጀታቸው
ሀገሪቱ
በቀጣይ
በአፍሪካ
ከቀዳሚዎቹ
አምስት
የቱሪስት
መዳረሻ
ሀገራት
መካከል
አንዷ
የመሆን
እቅዷን
ለማሳካት
እንደሚረዳም
ሚኒስቴሩ አስታወቋል። መሪ እቅዱ ሃገሪቱ በቀጣይ 10 አመታት
በቱሪዝም
ኢንደስትሪ
የምታከናውናቸው የልማት ተግባራት የሚመራበት ነው።
ወደቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን በምክር ቤት 3ኛ ጉባኤ
ስነመለስ፣
ጉባኤው
ከሁለተኛው
መደበኛ
ጉባኤው
ቀጥሎ
በተሰሩ
ስራዎች
ዙሪያ
ምክክር
አድረጎ ነበር።
በዚህም
የቱሪስት
መስህብን
በማልማት፣
የ10
ዓመት
የቱሪዘም
ስትራቴጂክ
እቅድ
የማዘጋጀት ጉዳይ፣
በትብብር
እና
በአቅም
ግንባታ
የተሻለ
ስራ
መስራት
ስለሚቻልበት ሁኔታ ውይይት ተካሂዷል። በጉባዔው
ላይ
በዘርፉ ያጋጠሙ ችግሮች
ናቸው
ተብለው
የተለዩ ጉዳዮች
ቀርበዋል።
በችግርነት ከተነሱት መሃከል የብድር
አቅርቦት
ችግር
እና
በሚፈለገው
ደረጃ
የመሬት
አቅርቦት
አለመገኘት የሚሉት
ተጠቃሾቹ ነበሩ ።
የምክር ቤቱ
ሰብሳቢ
ጠቅላይ
ሚኒስትር
ኃይለማርያም በዘርፉ
የሚስተዋሉ
ችግሮችን
ለመቅረፍ
የሚሰሩ
ስራዎች
ተጠናክረው
እንዲቀጥሉ ሲሉ
ማሳሰቢያ የሰጡ ሲሆን፣ በተለይ ከመሬት
አቅርቦት ጋር
ተያይዞ
የተነሳው
ችግር
መኖሩ
እንደሚታወቅ ገልጸዋል። በቀጣይ ይህንን
ችግር
በማቃለል
የግል
ባለሀብቶች
በዘርፉ
እንዲሰማሩ
እንደሚደረግ፣
በቱሪዝም
ዘርፍ
በመሰማራት
ማልማት
ለሚፈልጉ
አካላት
የመንግስትም
ይሁን
የግል
ባንኮች
ብድር
እንዲያመቻቹ
እንደሚደረግም
አሳውቀዋል። በተለይም
የኢትዮጵያ
ልማት
ባንክ
በቱሪዝም
ዘርፍ
ለሚሰማሩ
አልሚዎች
ብድር
ለማመቻቸት
መስማማቱን
አስታወሰዋል።
የበጀት ዓመቱን ማለትም የ2008 ዓ/ም አፈጻጸምምን እንደሚመስልም
ጠቅላይ ሚኒስትሩ መረጃዎችን አቅርበው ነበር። በዚህ መሰረት በበጀት
ዓመቱ
1 ሚሊየን
ጎብኚዎችን
ለመሳብ
ታስቦ
900 ሺህ
ጉብኚዎች
ወደ
ኢትዮጵያ
መጥተዋል። ሃገሪቱ ከእነዚህ ጎበኚዎች 3
ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ማግኘቷንም መረጃዎች አመልክተዋል።
ጠቅላይ ሚንስትር
ኃይለማርያም ሰሞኑን በተለያዩ ሚዲያዎችና ድረገጾች ከሃገሪቱ የቱሪዝም መስህቦችጋር
ለዓለም የተዋወቀውን አዲሱን የኢትዮጵያ የቱሪዝም
መለያም
ለመጀመሪያ ግዜ በጉባኤው ላይ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።
አዲሱ
የቱሪዝም
መለያ
“ኢትዮጵያ
የመገኛ
ምድር”
(Ethiopia Land of origin) የሚልና ይህን የሚያንፀባርቅ ምልክት ያለው ነው ።
የኢትዮጵያ ቱሪዝም
ድርጅት አዲሱ መለያ
ከተለያዩ
ባለድርሻ
አካላት
ጋር
በመወያየትና
ሰፊ
ጥናት
በማድረግ
የተቀረፀ
መሆኑን፣
እንዲሁም የቱሪዝም መዳረሻዎች፣ ሀይማኖታዊ
በዓላት፣
ባህላዊ
ትውፊቶች፣
የዱር
እንስሳት
ሃብትና
ሌሎችንም
የቱሪዝም
መዳረሻዎች
በተሟላ
መልኩ
እንደሚገልፅ
አስታውቋል።
በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የቱሪዝም እምቅ አቅም ቢኖራትም ከዘርፉ ስታገኝ
የነበረው ጥቅም እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም። አሁን ይህ እየተሰበረ ነው። በቀጣይነት ቱሪዝም ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ
የሚያስችል ሰፊ የስራ እድል መፍጠርና የውጭ ምንዛሪ ግኝትንም በጉልህ ሊያሳድግ የሚችል በመሆኑ ያሀገር ውስጥንም የውጭ
ጎብኝዎችን ቁጥር ለማሳደግ የማስተዋወቅና ጉብኝትን የማነሳሳት ስራ ሊሰራ ይገባል። ይህ ብቻ በቂ አይደለም የቱሪስቶችን የቆይታ
ግዜ ለማራዘም የመሰረተ ልማትና የቱሪዝም ፋሲሊቲዎችን ማስፋፋትም ይገባል። ይህ ሲሆን የቱሪዝም ዘርፉ በተለይ አሁን በሃገሪቱ
ጎልቶ የወጣውን የስራ አጥነት ችግር በመፍታት ህዝብን ቀጥተኛ ተጠቃሚ ማድረግ በማስቻል ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከት ይችላል።
No comments:
Post a Comment