ወንድይራድ ኃብተየስ
ጥቃቅንና
አነስተኛ በአገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት ተጨባጭ አስተዋጽዖን በማበርከት
ላይ የሚገኝ ዘርፍ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ ለውጦች እየታዩ ቢሆንም ጥቂት የማይባሉቱ ለጥቃቅንና አነስተኛ መልካም የሆነ
ዕይታ የላቸውም። አንዳንዶች ጥቃቅንና አነስተኛን የደኃና የሥራ አጥ መሰባሰቢያ እንደሆኑ አድርገው የመመልከት ችግር አለ። ይሁንና
ሁሉም የበለፀጉ አገራት ጥቃቅንና አነስተኛን በአግባቡ መጠቀም በመቻላቸው አሁን ላሉበት ደረጃ መድረስ ችለዋል። ለአብነት ጃፓን
አሁን ድረስ የኢንዱስትሪው ዘርፍ ከ50 በመቶ የሚሆነውን ግብዓት የሚያገኘው ከእነዚህ ዘርፍ ነው።
እነዚህን
ዘርፎች ማጠናከር ለዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠሩ ባሻገር ለኢኮኖሚው ዕድገት ወሣኝ አስተዋጽኦ አለው። በእኛ አገር አንዳንዶች ለቃሉ
ራሱ አዲስ ይመስላሉ። ጥቃቅንና አነስተኛ ሁለት የተለያዩ ተቋማት
ናቸው። ጥቃቅንና አነስተኛ በአደረጃጀቶቻቸው ተመሳሳይነትና ተመጋጋቢነት ቢኖራቸውም
በመጠን ውይም በይዘት የተለያዩ ናቸው። ጥቃቅንና አነስተኛ አደረጃጀቶችን ስንመለከት በኢንዱስትሪው ዘርፍ ማለትም
ማኑፋክቸሪንግ፣ ኮንስትራክሽንና ማዕድን ወዘተ…እንዲሁም በአገልግሎት
ዘርፍ ደግሞ ችርቻሮ ንግድ፣ ትራንስፖርት፣ ሆቴልና ቱሪዝም፣ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና ጥገና ወዘተ…በማለት መክፈል ይቻላል።
ጥቃቅንና አነስተኛ ትኩረት የሚሰጣቸውን ዘርፎች
ስንመለከት ደግሞ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ጨርቃጨርቅና ስፌት፣ ቆዳና
የቆዳ ውጤቶች፣ የምግብና መጠጥ ዝግጅት፣ የብረታ ብረትና የኢንጂነሪንግ ምርቶች፣ የእንጨት፣ ባህላዊ የዕደ ጥበብና የጌጣጌጥ ሥራዎች
እንዲሁም አግሮ ፕሮሰሲንግ ናቸው። የኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚባሉት ደግሞ ሥራ ተቋራጭነት፣ ንዑስ ሥራ ተቋራጭነት፣ የግንባታ ግብዓቶች
ምርት፣ ባህላዊ የማዕድን ሥራዎች፣ የከበሩ ድንጋዮች ልማት፣ ኮብል ስቶን እና የመሠረተ ልማት ግንባታ ንዑስ ተቋራጭነት ናቸው።
የንግድ ዘርፍ የሚባሉት ደግሞ
የአገር ውስጥ ምርቶች ጅምላ ሽያጭ፣ የአገር ውስጥ ምርቶች ችርቻሮ ንግድ እና የጥሬ ዕቃ አቅርቦት ነው። የአገልግሎቶች
ዘርፍ የሚባሉት አነስተኛ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ ካፌና ሬስቶራንቶች፣
የማከማቻ፣ የቱሪስትና የማሸጊያ፣ የሥራ አመራርና የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች እንዲሁም የኘሮጀክት ኢንጂነሪንግ፣ የምርት ዲዛይንና
ልማት አገልግሎቶች፣ የግቢ፣ የውበትና የጥበቃ እና ፅዳት፣ የጥገና አገልግሎት፣ የውበት ሣሎን ሥራዎች፣ የኤሌክትሮኒክስና ሶፍት
ዌር ልማት፣ የዲኮር ሥራ እና ኢንተርኔት ካፌ ናቸው። በግብርና ዘርፍ (የከተማ ግብርና) ደግሞ፣ ዘመናዊ የእንስሳት ዕርባታ፣ የንብ
ማንባት፣ የዶሮ እርባታ፣ ዘመናዊ የደን ልማት፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ዘመናዊ የመስኖ ሥራ፣ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ወዘተ…
ናቸው።
የኢፌዴሪ የጥቃቅንና አነስተኛ አደረጃጀቶች
ራዕይ “ለኢንዱስትሪው ልማት አስተማማኝና ሰፊ መሠረት ያለው ተወዳዳሪ ዘርፍ ተፈጥሮ ማየት” የሚል ነው፤ አራት ዓላማዎችም አሉት። የመጀመሪያው ዓላማ ሰፊ የሥራ ዕድል
በመፍጠር የዜጎችን ገቢ ለማሻሻልና ድህነትን ለመቀነስ እንዲሁም ፍትሃዊ
የኃብት ክፍፍል እንዲፈጠር ማድረግ ነው። ሁለተኛው ዓላማ ደግሞ ተወዳዳሪና
ቀጣይነት ያለው ፈጣን ልማት ለማስመዝገብ የሚያስችል የገጠር ልማትን
በማፋጠን ለኢንዱስትሪው ልማት አስተማማኝ መሠረት መጣል ሲሆን፤ ሦስተኛው ደግሞ በከተሞች ሰፊ መሠረት ያለው ልማታዊ ባለሀብት በመፍጠር
የዘርፉን ልማት ማስፋፋት ናቸው።
የጥቃቅንና አነስተኛ በአደረጃጀቶቻቸው ስንመለከታቸው፤
ጥቃቅን የሚባለው አደረጃጀት በኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚቋቋም ከሆነ ማለትም በማኑፋክቸሪንግ፣ ኮንስትራክሽንና ማዕድን ዘርፍ የሚመሠረት ድርጅት
እስከ አምስት ሰዎችን የሚይዝ ሆኖ በሀብት ደረጃም እስከ 100000 ብር (መቶ ሺህ ብር) የሚኖረው ይሆናል። በተመሳሳይ አነስተኛ
የሚባለው አደረጃጀት በኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚቋቋም ከሆነ ከ6 እስከ 30 ሰዎችን የሚቀጥር ድርጅት ሲሆን ጠቅላላ ሀብቱ
ደግሞ ከብር 100,001 እስከ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚሆን ሃብት ይኖረዋል።
በሌላ በኩል ጥቃቅን የሚባለው አደረጃጀት
በአገልግሎት ዘርፍ ማለትም በችርቻሮ ንግድ፣ ትራንስፖርት፣ ሆቴልና
ቱሪዝም ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና ጥገና የሚሰማሩ ከሆነ እስከ አምስት ሰዎች የሚቀጥር ሆኖ ጠቅላላ ሀብቱ ደግሞ እስከ
ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር)ይደርሳል። በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ አነስተኛ የሚባለው አደረጃጀት ደግሞ ከ6 እስከ 30 ሰዎችን የሚቀጥር ሆኖ ከብር 50,001 –
500,000 ብር የሚደርስ ገንዘብ ይኖረዋል።
ጥቃቅንና አነስተኛ ሦስት የዕድገት ደረጃዎች
ያሏቸው ሲሆን እነዚህም የምሥረታ /ጀማሪ (Start-up)፣ የታዳጊ ወይም የመስፋፋት (Expansion) እና የመብቃት
(Maturity) የሚባሉ ናቸው። እነዚህን የዕድገት ደረጃዎች ለማለፍ ድጋፍና ክትትል ያስፈልጋቸዋል።
የኢፌዴሪ መንግሥት ጥቃቅንና አነስተኛን የልማት አቅጣጫ እንዲሆኑ የተመረጡበት ሁኔታ በውሱን ካፒታልና
በአነስተኛ ቴክኖሎጂ የሥራ እድል መፍጠር የሚያስችሉ፣ ልማታዊ ባለሃብት መፍጠሪያ፣ ዜጎች የሥራ ክህሎትና ልምድ የሚያዳብሩበት፣ የሥራ ፈጣሪነትና አክባሪነት እንዲሁም የቁጠባ ባህልን ለማዳበር
ምቹ፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት እንዲስፋፉ የሚያግዙ ብሎም የአገሪቱ የኢኮኖሚ መሠረት የሆነው ግብርናን ከኢንዱስትሪ
ጋር ለማስተሳሰር የሚያስችሉ መሆናቸው ነው።
የጥቃቅንና አነስተኛ የድጋፍ ማዕቀፎች የሚባሉት
የሰው ኃይል ልማትና የቴክኖሎጂ ዕድገት፣ የገበያ ልማትና የግብይት፣ የፋይናንስና ብድር አገልግሎት የድጋፍ ሥርዓት፣ የማምረቻና
የመሸጫ ማዕከላት ልማት፣ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ በፍላጎትና በውጤት ላይ የተመሠረተ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት የሚሰጥበትን
መንገድ መፍጠር፣ የብድር አጠቃቀምና የቁጠባ ዘዴ ማስፋት ናቸው።
ጥቃቅንና አነስተኛ የህዳሴው ጉዟቸውን ሲጠናቀቅም
በኢንዱስትሪ በተለይም በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ዋናዎቹ አምራች ኃይሎች ሆነው መቀጠላቸው የማይቀር ነው። ኢንዱስትሪን በተለይም የማኑፋክቸሪንግ
ዘርፍ በከፍተኛ ፍጥነት ለማሳደግ በቅድሚያ የአነስተኛና ጥቃቅን ተቋሞች ልማትን ማፋጠን በሁሉም መስክ አዋጪ ነው። ሁሉም በአነስተኛና
ጥቃቅን ተቋማት ውጤታማ ላይሆኑ የሚችሉባቸው አጋጣሚዎች እንደሚፈጠሩ ታሳቢ ማድረግ ተገቢ ነው። ጥቂቶች በጊዜ ሂደት ወደ መካከለኛ
ደረጃ ያድጋሉ። በርካቶች ባሉበት የሚቀጥሉ ሲሆን አንዳንዶች ደግሞ
ሊከስሙ ይችላሉ።
አነስተኛና ጥቃቅን ተቋሞች ዋነኛ የሥራ ዕድል ፈጣሪ ኃይሎች የሚሆኑት እንደኛ ባሉ አገሮች ብቻ ሳይሆን እንደ አሜሪካ፣ ጃፓንና ጀርመን ባሉ የበለፀጉ አገሮችም ጭምር ትልቅ የልማት ማፋጠኛ ሞተሮች ናቸው። አነስተኛና
ጥቃቅን ለአሁኑ ብቻ ሳይሆን ለዘለቄታውም ዋናዎቹ የሥራ ዕድል ምንጮች በመሆናቸው ከወዲሁ ቅድሚያ ሰጥተን ልናጠናክራቸው የሚገባ ዘርፍ ነው። ጃፓን አሁን ድረስ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆነው የማኑፋክቸሪንግ ምርቷ የሚመረተው በአነስተኛና ጥቃቅን የማኑፋክቸሪንግ ተቋሞች ነው። አነስተኛና ጥቃቅን እንደኛ ላሉ ታዳጊ አገሮች ብቻ ሳይሆን አብዛኛዎቹ በእጅጉ ለበለፀጉ አገሮችም የሚያገለግሉ በመሆናቸው የመንግሥት የልማት
ትኩረት መሆን ችለዋል።
ለጥቃቅንና አነስተኛ ዋነኛ ተግዳሮት ሊሆን
የሚችለው የመጀመሪያው ችግር የአስተሳሰብ ችግርን ማስወገድ መቻል ነው። ሥራው አይመጥነኝም፣ ከትምህርት መስመሬ ጋር አይዛመድም፣
ገቢው አይመጥነኝም ወዘተ…የሚሉ አስተሳሰቦችን ማስወገድ ተገቢ ነው።
ሌላው ችግሮች ውጫዊ የሚባሉ ናቸው። የካፒታል እጥረት፣ የክህሎትና የገበያ ችግሮች መኖር፣ ዘመናዊ የንግድ አመራር እውቀትና ብቃት አለመኖር፣ የሥራ ፍቅር ያለመኖር፣ የሸቀጥና አገልግሎት ገበያ የማግኘት ችግር የሚያጋጥመው መሆኑ ተጠቃሾች ናቸው።
አገራችን ታዳጊ ናት። ይሁንና እስካሁን ባለው
ሁኔታ በዓመት እስከ ስምንት መቶ ሺህ የሚደርስ የሥራ ዕድል መፍጠር ችላለች። ይህ ቁጥር እጅግ ከፍተኛ የሚባል ነው። ይሁንና አንድ
ሦስተኛው ወጣት በሆነበት አገር ይህ የሥራ እድል በቂ ባለመሆኑ መንግሥት የቀድሞውን ፖሊሲ ማሻሻል አስፈልጎታል። በመሆኑም ወጣቶች
መንግሥት የተከተለውን ፖሊሲ የሚመጥን አደረጃጀት በመከተል ሥራ መፍጠር ይኖርባቸዋል። በጥቃቅንና አነስተኛ በመደራጀት የመንግሥትን
ጥረት ውጤታማ ማድረግ ይቻላልና።
No comments:
Post a Comment