Sunday, 1 January 2017

“አይደገምም! የበደልነውን ህዝብም እንክሰዋለን”




                                  አባ መላኩ
“አይደገምም! የበደልነውን ህዝብም እንክሰዋለን” የሚለውን  የታራሚዎችን ቃል ስሰማ ከልቤ ደስታ ተሰማኝ። ምክንያቱም እነዚህ አካላት በቅርቡ በአገራችን በተከሰተው ሁከት በአንድም ይሁን በሌላ ግንባር ቀደም ተሳታፊ ነበሩ ናቸው። ይሁንና እነዚህ አካላት ህዝባችንን በድለናል፣ ያወደምነው ንብረት የራሳችንን ነው፣ በድርጊታችን አፍረናል፣ ተጸጽተናል፣ ህዝባችንን ይቅርታ እንጠይቃለን፣ በቀጣይም በምንችለው ሁሉ እንክሰዋለን  ወዘተ የሚሉ  ቃላትን ሲናገሩ በማድመጤ ደስ ብሎኛል። እነዚህ አካላት የተናገሩት ከልባቸው ነው ብዬ አምናለሁ። ምክንያቱም  ሊዋሹ የሚችሉባቸው መነሻ  አይኖርም። እነዚህ ዜጎች በአገራችን በቅርቡ በተነሳው ሁከት  ሳቢያ  ተጠርጣሪ ሆነው በቁጥጥር ስር ከዋሉት ጊዜ ጀምሮ ከታህድሶ መዕከል እስኪሰናበቱ  ድረስ  ማንም ምንም ጫና አላደረገባቸውም።
እነዚህ ታርመው ከመዕከል የተሰናበቱ አካላት በአብዛኛው  ወጣቶች  በመሆናቸው እውነትም  ህዝባቸውን ለመካስ ገና በርካታ አማራጮች  እንዳሏቸው  ማየት አይከብድም። በመሆኑም  ለመዋሸት የሚያነሳሳቸው አንዳችም ምክንያት አይኖርም።  እነዚህ አካላት  ከመናገር  አልፈው በተጨባጭ የንብረት ማውደምና ህይወት ማጥፋት ተግባር የተሰማሩ ቢሆንም በታህድሶ መዕከል  በቆዩበት ጊዜ ምንም አይነት በደል አልተፈጸመባቸውም። ይልቁንም የአገራችንን ተጨባጭ  ሁኔታ የሚገነዘቡበት  ትምህርት እንዲቀስሙ ተደርጓል።  
በቅርቡ በአገራችን ተከስቶ በመበረው ሁከት አሳታፊና ተሳታፊ ናቸው በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ   በርካታ ዜጎች የተሰጣቸው የተሃድሶ ስልጠና አጠናቀው ወደየመጡበት ተመልሰዋል። በመጀመሪያ ዙር ተጠርጥረው ቁጥጥር ስር ከዋሉ ዜጎች መካከል 9 ሺህ 800 የሚሆኑት የተሰጣቸውን የተሃድሶ ስልጠና በአግባብ  አጠናቀው  ወደ ሕብረተሰቡ ተቀላቅለዋል። የጥፋት ሃይሎች ተላላኪና አስፈጻሚ የነበሩ  አንዳንድ ግለሰቦችም በአገሪቱ የወንጀል ህግ መሰረት ወደ ፍርድ ቤት የሚቀርቡበት ሁኔታም ተመቻችቷል። እነዚህ ተጠርጣሪ ግለሰቦች ላይም ቢሆን ከህግ አግገባብ ውጭ የሚመጣባቸው ነገር አይኖርም። 
በሁከት የተጠረጠሩ  አካላት በቁጥጥር ስር በዋሉበትና ወደ ስልጠና በገቡበት  በጥቅምት 2009 ዓ ም መጀመሪያ አካባቢ  ጽንፈኛ የዳያስፖራ ሚዲያዎች እንደለመዱት የሃሰት ፕሮፓጋንዳቸውን በመርዘኛ ሚዲያዋቻቸው ሲያናፍሱ ነበር። መንግስት የበቀል እርምጃ ይወስድባቸዋል፤ በመሆኑም ልጆቻችሁ አለቀላቸው፣ አበቃላቸው በማለት ህብረተሰቡን ለማደናገር ጥረት አድርገው ነበር። በተመሳሳይ አንዳንድ ሰልጣኞችም በውስጣቸው  ይህን አይነት ፍራቻ አድሮባቸው  እንደነበር አሁን ላይ ከሚሰጡት አስተያየት መረዳት ችለናል።
አንዳንድ ታራሚዎች ሲናገሩ እንዳደመጥነው  በሁከቱ ከፍተኛ አገራዊ ጉዳት በመድረሱ መንግስት አስተምሮ ይለቀናል የሚል ግምት አልነበረንም።  ይሁንና  የገጠመን በተቃራኒው ነው።  ታራሚዎቹ እንዳሉት በጸጥታ ሃይሎቻችን ህዝባዊነት እጅግ ኮርተናል። መዕከሉን ከተቀላቀልንበት ጊዜ ጀምሮ ህገመንግስታዊ መብቶቻችን  ተጠብቆልናል።  ታራሚዎች የነበሩበትንም ሁኔታ  በአንደበታቸው ለህብረተሰቡ ተናግረዋል። ዛሬ ላይ ኢሳትና ኦ ኤም ኤን ደግሞ ምን ዘመቻ ይከፍቱ ይሆን።
አገራችን ህገመንግስታዊ አገር መሆናን በተግገባር አሳይታለች። ማንም እንኳን ተጠርጣሪ ይቅርና ወንጀለኛም ቢሆን በቁጥጥር ስር የሚውል ማንኛውም ግለሰብ ህገመንግስታዊ መብቱ የተጠበቀ ነው።  በኢፌዴሪ ህገመንግስት በአንቀጽ --- ላይ በቁጥጥር ስር የሚውሉ አካላት ተገቢው አያያዝ እንደሚደረግላቸው በተደነገገው መሰረት እነዚህ ተጠርጣሪ ዜጎችም  በአግገባብ ተይዘው ተገቢው ትምህርትና ስልጠና ተሰጥቷቸው ወደ ማህበረሰቡ ተሰናብተዋል።
ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር በነበሩበት ወቅት  ስለህገመንግስት፣ ስለ ቀለም አብዮት ምንነት፣ ስለ ኢትዮጵያ ታሪክና የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በቂ ግንዛቤ እንድንጨብጡ ተደርጓል። ተጠርጣሪዎች “አይደገምም'' የሚል የጸጸት አቋም እንዲይዙ ያደረጋቸው ትክክለኛ ትምህርት መሰጠቱን ያመለክታል።  
ግንቦት ሰባትና ኦነግ ከጽንፈኛው ዳያስፖራ ጋር አብረው  በማህበራዊ ሚዲያና  በኢሳት እንዲሁም  በኦኤም ኤን  በረጩት ተለያዩ አፍራሽ ፕሮፓጋንዳ አገራችንን ወደ ሁከት እንድታመራ አድርገው ነበር።  በዚህም ሳቢያ የንጹሃን ህይወት ጠፍቷል፣  ለህብረተሰቡ አገልግሎት የሚሰጡ ንብረቶች ወድመዋል፣ የግል ባለሃብቱ ንብረት በተለይ የኢንቨስተሮች ንብረት ወድሟል። ከዚህም ባሻገር የአገራችን መልካም ስም ላይ መጥፎ ስጋት ፈጥሮ ነበር።   ለዘመናት  ተሳስበውና  ተዋደው በአንድ ላይ በሚኖሩ የተለያዩ የብሄር ተወላጆች መካከል መቃቃርን ተፈጥሮ ነበር።
አገራችን ህገመንግስታዊ አገር ናት። ማንም የመሰለውን ሰላማዊ በሆነ መንገድ የማራመድ መብት  አለው። ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ተሃድሶ ወስደው ከጦላይ  ላጠናቀቁና ወደ ህብረተሰቡ ለሚመለሱ አካላት በጦላይ ማሰልጠኛ ተገኝተው እንዳሉት ነገም ከመንግስት አቋም የተለየ አቋም ልታራምዱ ትችላላችሁ፤ ይሁንና  የሚከለክለው የተለየ አቋም ሰለያዛችሁ ሳይሆን አቋማችሁን በሃይልና በነውጥ ለማስፈጸም የምታደርጉትን ጥረት ነው፤  በመሆኑም እምነታችሁንና አቋማችሁን ሰላማዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ  ብቻ ማራመድ ይኖርባችኋል  ሲሉ አሳስበዋል።  ህገመንግስታችን ማንም የፈለገውን ሃሳብ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማራመድ የሚችልበትን ሁኔታ ፈጥሯል። ማንኛውም ዜጋ  የተለየ አቋም የመያዝና አቋሙንም ሰላማዊ በሆነ መንገድ የማራመድ ህገመንግስታዊ  መብት አጎናጽፎታል። ማንም ህገ-መንግስቱ ያጎናጸፈውን መብት ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማራመድ እስከቻለ ድረስ ገደብ የለበትም።
ጽንፈኛው ዳያስፖራ  የህብረተሰቡን ትክክለኛ ጥያቄዎች ሽፋን በማድረግ  ወጣቱን ለጥፋት አነሳስተው የግል ምኞታቸውን ለማሳካት ጥረት አድርገዋል። አንዳንድ ወጣቶችንም አሳስተው የአገራችንን ልማት አደናቅፈዋል። በሁከቱ ንብረት ወድሟል፣ ንብረት ወድሟል እንዲሁም ህዝቦችን አቃቅሯል። በመሆኑም አሁን ታርመው የወጡ አከላት  በሁከቱ ጉዳት ለደረሰባቸውና ለአካባቢው ነዋሪዎች ይቅርታ መጠየቅም ሆነ በቀጣይ ህብረተሰቡን በማገልገል መካስ  ይኖርባቸዋል። እንዲሁም የተለያዩ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የሚኖሩባት ኢትዮጵያ ጠባብነትና ትምክህት  እንደማይጠቅሟት ይልቁንም በዘመነ ግሎባላይዜሽን እርስ በርስ ተደጋግፎና ተረዳድቶ የመኖር ባህልን ማሳደግ  ብቸኛ አማራጭ መሆኑን መመስከር ይኖርባቸዋል። ከዚህ በተጨማሪም በተሃድሶ መዕከል የነበረውን ትክክለኛ ሁኔታ መመስከር ይኖርባቸዋል።  
ከዚህም ባሻገር ታራሚዎች በተሃድሶ መዕከሉ  የቀሰሙትን  እውቀት  ማለትም ስለህገ መንግስት፣ ስለቀለም አብዮት ምንነት፣ በኢትዮጵያ ሕዳሴና በወጣቶች ሚና ለሌሎች ጓዶቻቸው ማካፈል ይኖርባቸዋል። እንዲሁም የአካባቢያቸውን ሰላም በማስጠበቅ ልማትን ማፋጠን ይኖርባቸዋል።  ወጣቱ በጥፋት ሃይሎች በሚናፈስ ውዥንብርና አሉባልታ ተገፋፍቶ ወደ  ጥፋት መግገባት አይኖርበትም። በቀጣይም ኦነግና ግንቦት ሰባት በማህበራዊ ሚዲያም ሆነ በመርዛማ ሚዲያዎቻቸው ማለትም በኢሳትና ኦኤምኤን የሚረጩት የተሳሳተ መረጃ ይቆማል ብሎ ማሰብ አይቻልም። ይሁንና ወጣቱ የዚህ ተራ ፕሮፓጋንዳ ሰለባ እንዳይሆን ያለፈው ክስተት ጥሩ ትምህርት ነው።
የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች በሚኖሩባት ኢትዮጵያ ጠባብነትና ጎሰኝነት እንደማይጠቅምና እርስ በርስ ተደጋግፎና ተረዳድቶ የመኖር ባህልን ማሳደግ ይኖርብናል። ማንም የፈለገውን አስተሳሰብ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማራመድ ይችላል። የአገራችን  ዴሞክራሲ ስርዓት ታዳጊ በመሆኑ የእያንዳንዳችንን  እንክብካቤ ይሻል። በመሆኑም ጽንፈኛ አካሎች  ይህን ጅምር የዴሞክራሲ ስርዓታችንን ወደኋላ እንዳይመልሱት፣ አገራችንን ወደብጥብጥና ሁከት እንዳያመሯት ሁላችንም ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል። በአገራችን ህገመንግስታዊ ስርዓት የተዘረጋባት ናት። ማንም ወደ ስልጣን መምጣት የሚፈልግ አካል ምላሹን ከምርጫ ኮሮጆ ሊፈልግ ይገባል።  


No comments:

Post a Comment