በቤተልሔም
በድሉ
ኢትዮåያ በሕዝብ ብዛት ከአፍሪካ የሁለተኛነት ደረጃ ይዛለች። ከሕዝብ ቁጥሯም ከፍተኛውን
ቁጥር የሚይዘው ወጣቱ ነው። በመሆኑም ይህን የኅብረተሰብ ክፍል ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ዕድገት ለማዋል መንግሥት በ2004 ዓ.ም ላይ
ሀገራዊ የወጣቶች ፖሊሲ ቀርፆ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።
በመሆኑም በኢትዮåያ ሀገር አቀፋዊ የወጣቶች ፖሊሲ ሥራ ላይ ከዋለ ጊዜ ጀምሮ ለወጣቶች መብት ከመቼውም ጊዜ በላይ ዕውቅና ተሰጥቶት እየተሠራ ይገኛል፡፡
ፖሊሲው በዋናነት ግብ ያደረገው በወጣቶች ንቁ የሆነ ተሳትፎ ዴሞክራሲያዊ የሆነች እና መልካም አስተዳደር የሰፈነባት ሀገር መገንባትን
ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የፖሊሲው ግብ የሚያተኩረው
ወጣቶች በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ባህል ነክ ጉዳዮች ላይ እንዲሳተፉ እና ከውጤቱም እኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ላይ
ነው፡፡ ትምህርት እና ጤና፣ ዴሞክራሲ እና መልካም አስተዳደር እንዲሁም ባህል፣ ስፖርት እና መዝናኛ የፖሊሲው ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች
ናቸው፡፡
ወጣቶች በአንድ ሀገር ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ
ገጽታ ላይ ሚና ለመጫወት የሚያስችል ከፍተኛ ብቃት አላቸው። በቅርቡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለሕዝብ ተወካዮች
ምክር ቤት እንደገለጹት ከጠቅላላ ከሀገሪቱ የሕዝብ ብዛት 70 በመቶ የሚሆኑት ወጣቶች ናቸው። እነዚህ ወጣቶች ሀገሪቱ በተለያዩ
የሕይወት መንገዶች ባለፈችባቸው የኢኮኖሚ ደረጃዎች ውሰጥ ተፈትነው ያለፉ ናቸው፡፡ ይህም የተለያዩ የመዝናኛ ቦታዎች፣ የሕዝብ ላይበራሪዎች እንዲሁም
የሥልጠና ቦታዎች እንደልባቸው ማግኘት ይከብዳቸው የነበረ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
አምራች ለሆነው ወጣት ትኩረት በመስጠትም
የኢፌዴሪ መንግሥት በ2001 ዓ.ም የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴርን እንዲቋቋም አድርጓል። ይህም መንግሥት ኢትዮåያን ከኋላቀርነት ወደ ብልጽግና ለማሸጋገር የሚችሉ እና የተሟላ ሰብዕና ያላቸው
ወጣቶችን ለመፍጠር አሰቦ እየሠራ መሆኑን ያሳያል። በመሆኑም ወጣቶች ሥራ ፈጣሪ፣ ምርታማ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እና በልማታዊ
እና በዴሞክራሲያዊ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ እያበረታታ ይገኛል፡፡
እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ በፈጠራ ችሎታቸው
የላቁ እና ምርታማ የሆኑ ወጣቶችን ለማፍራት የሚያስችል በቂ የሆነ ማበረታቻ አለ ወይ ነው? ምክንያቱም የሚጠበቀውን ያህል የዳበረ አዕምሮ ያለው ወጣት በአንድ ጀንበር ማግኘት የሚቻል አይደለም።አንድ
ሰው በተፈጥሮው ወይም ከልምድ እና ከትምህርት በሚያገኛቸው ነገሮች (በጊዜ ሂደት ) ውጤታማ በመሆን ሥራ ፈጠሪ ሊባል ይችላል፡፡
ነገር ግን ይህ ተግባር እንደ ሀገራችን ባሉ ታዳጊ ሀገራት በምዕራቡ ዓለም ከልጅነት ጀምሮ ፍላጎቱ ታውቆ ድጋፍ እየተደረገለት እንደሚያድግ
ልጅ ቀላል አይደለም፡፡ ምክንያቱም እንደ ኢትዮåያ ባሉ ታዳጊ ሀገራት ወላጆች ከተለያዩ
የሕይወት ሩጫዎቻቸው የተረፈ የልጆቻቸውን ችሎታ /ክህሎት/ የሚለዩበት ምናልባት ለይተውም ከሆነ ድጋፍ የሚያደርጉበት ጊዜም ሆነ
ገንዘብ ሊያጥራቸው የሚችልበት አጋጣሚ ከፍተኛ ነው።
ትምህርት ቤቶች በተለያየ የትምህርት ዘርፍ
ብቁ የሆኑ ዜጎች የሚፈሩባቸዉ ቦታዎች ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ እንደ ሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የትምህርት
ዕድል ባላገኙ ሕዝቦች ብዛት ቀሚጠቀሱት የዓለም ሀገራት ኢትዮåያ አንዷ ነች። ስለዚህ በገጠሩ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያላቸው ማኅበረሰቦች
የሚገኙ ሕፃናት ወጣቶች እና ሴቶች መሠረታዊ ትምህርት የማግኘት ዕድላቸው ዝቅተኛ ነው ማለት ነው፡፡ እዚህ ላይ ሊነሳ የሚችለው
ጥያቄ ታዲያ መንግሥት መሠረታዊ ትምህርት ማግኘት የማይችሉ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ይዞ የወጣቶችን የፈጠራ ክህሎት ማዳበር እና ራስን
የመቻል ፍላጎታቸውን ዕውን ማድረግ የሚችለው እንዴት ነው? የሚለው ነው።
የኢፌዴሪ ወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር
በያዝነው ዓመት ባወጣው ጽሑፍ ላይ እንደገለፀው ዓለማቀፋዊ እና ሀገራዊ ሁኔታዎች ሰዎች የግላቸውን ሥራ እንዲፈጥሩ እያስገደዱ ነው።
በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ እጅግ ግዙፍ እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞችን የሚቀጥሩ ኢንዱስትሪዎች እና የግብርና ልማት ሥራዎች
ቁጥር እየቀነሱ በመሆናቸው የዓለም የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በመቀዝቀዙ
ከፍተኛ የሆነ የሰው ኃይል ቅነሳን አስከትሏል። በመሆኑም የሥራ ፈላጊዎች ቁጥር እየተበራከተ መምጣቱን ያሳያል። ስለዚህ ድህነት
እና ሥራ አጥነት የወጣቶች ዋነኛ ችግሮች እንደመሆናቸው መጠን ወጣቶች የራሳቸውን ሥራ እንዲፈጥሩ ለማስቻል እና የጥቃቅን እና አነስተኛ
ልማት ዘርፎችን ማጎልበት ልንከተለው የሚገባ ስልት መሆኑን በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የተዘጋጀው ጽሑፍ አውስቷል፡፡
ወጣቶች በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ተሠማረተው
ራሳቸውን ከመቻል አልፈው ድህነትን በመቀነስ እና በሥራ ፈጠራ በኩል ቀላል የማይባል ሚና መጫወት እየጀመሩ ቢሆኑም የተለያዩ መሰናክሎች እየገጠሟቸው ይገኛሉ፡፡ ከነዚህ ውስጥ የትምህርት
እና የሥልጠና ሥርዓቱ በሀገሪቱ የሚፈለገውን ያህል አለመሆኑ ወጣቶች በሥራ ፈጠራ እንዳይሠማሩ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩ በዋናነት
ይጠቀሳል።
ሌላው የሚያጋጥማቸው እንቅፋት የፋይናንስ
ችግር ሲሆን፤ ወጣቶች ሊያሳኳቸው የሚመኟቸውን የፈጠራ ሀሳቦች ቢይዙም ወደተግባር ለመለወጥ የሚፈለገውን ያህል ሀገራዊ የፋይናንስ
አቅርቦት አለመኖሩ ካሰቡበት የስኬት ደረጃ እንዳይደረሱ ፈተና ሆኖባቸዋል ለዚህም ድህነት፣ የብድር ተቋማት አለመስፋፋት እና የቁጠባ ባህል አለመዳበር
በዋናነት የሚጠቀሱት ምክንያቶች ናቸው፡፡
ሌላው የወጣቶች ችግር በጥቃቅን እና አነስተኛ
የሥራ ዘርፎች ተደራጁ ወጣቶች የገበያ እና የመረጃ እጥረት አስፈላጊው መሠረተ ልማቶች የተሟሉላቸው የማምረቻ እና የመሸጫ ቦታዎች
በበቂ ሁኔታ አለመኖራቸው ምክንያት ምርቶቻቸውን ለፈላጊው ለማድረስ የሚቸገሩበት ሁኔታ ሲሆን፤ ገበያ ተኮር መረጃዎችን የማግኘት
አጋጣሚያቸውም በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡
ከሥራ ፈጠራ ጋር ተያይዘው ከሚነሱ ዋነኛ
ችግሮች መካከል የሚጠቀሰው ሌላኛው ነገር የተስማሚ ቴክኖሎጂዎች እጦት ነው፡፡ ወጣቶች በየሚኖሩበት አካባቢ ተስማሚ ቴክኖሎጂዎች
ባለመኖራቸው ምርታቸውን ለማሳደግ እና ጥሬ ዕቃዎችን ወደ ተሻሉ ምርቶች ለመለወጥ የሚያስችሉ ሁኔታዎች አለመፈጠራቸው ችግር እየፈጠረ
ይገኛል፡፡
ይህንን ችግር ለመቅረፍ መንግሥት እና
የሚመለከታቸው አካላት ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም እና ከቴክኒክ እና ሙያ ማሠልጠኛ ተመርቀው የሚወጡ ወጣቶችን በተመረቁባቸው
የሙያ ዘርፎች ከሚያገኙዋቸው ሥራዎች በተጓዳኝ የየራሳቸውን ሥራ እንዲፈጥሩ ወይንም በጥቃቅን እና አነስተኛ ተደራጅተው ራሳቸውን
እንዲችሉ የበኩላቸውን ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
ከፍ ብሎ ለመግለጽ እንደተሞከረው ወጣቶችን
በስፋት ከሚያጋጥማቸው ችግር አንዱ የመነሻ ወይንም የሥራ ማስኬጃ የሚሆን ገንዘብን ማግኘት አለመቻል ነው፡፡ በመሆኑም ወጣቶች የፈጠራ
ሥራዎቻቸውን ወደ ተግባር ለመለወጥ፣ ለማሻሻል እንዲሁም በብዛት ወደ ማምረት ደረጃ ለመግባት የሚያስችል ገንዘብ ይቸገራሉ፡፡ ይህ
ችግር በከተማም ሆነ በገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍል የሚኖሩ ወጣቶች በተመሳሳይ የሚያነሱት ችግር ይሄ ነው፡፡ በመሆኑም ይህን ወሳኝ ማነቆ
ለመቅረፍ የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት የብድር እና ቁጠባ ተቋማት በገጠር እና በከተሞች በማቋቋም፣ የወጣቶች የቁጠባ ባህላቸውን
እንዲያዳብሩ በማድረግ የተለያዩ ብድሮችን ያመቻቻሉ፡፡
አንድን የፈጠራ ሥራ ለመሥራት፣ ከተሠራም
በኋላ ለተጠቃሚው ኅብረተሰብ ለማሳየት ቦታ ማግኘት ወሳኝ በመሆኑ መንግሥት በየአካባቢው የተደራጁ ወጣቶች የማምረቻ፣ የምርት ማሳያ
እና የመሸጫ ቦታዎችን እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ይገኛል። ይሁን እንጂ መንግሥት የወጣቶችን የሥራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ የሚያደርገው
ጥረት የሚፈለገውን ያህል እንዳይሆን ያደረገው በአንዳንድ አስፈጻሚዎች እና ተጠቃሚዎች ባላስፈላጊ ጥቅም ትሥሥር የሚስተዋሉ የኪራይ
ሰብሳቢነት አመለካከቶች ናቸው፡፡ ይህን ችግር ለመቅረፍ መንግሥት አሠራሩን ማጥራት፣ በውስጡ የተሰገሰጉ ኪራይ ሰብሳቢዎችን ማስወገድ
እና የመሥሪያ እና የመሸጫ ቦታ እጥረቱን የሚያቃልሉ መሠረተ ልማቶችን ማስፋፋት ይኖርበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሥራን እና ሥራ
ፈጣሪዎችን የሚያበረታቱ ዘዴዎችን በመቀየስ በተቻለ መጠን መሥራት ይጠበቅበታል፡፡
ሀገሪቱ የምትከተለው ገበያ መር የኢኮኖሚ
ፖሊሲ ሥራ ፈጣሪዎች አቅማቸውን እና ሙያቸውን እንዲጠቀሙ አመቺ ሁኔታን ቢፈጥርም፤ ሥራ ፈጣሪዎችን ያማከለ በቂ የዓቅም ግንባታ
ሥልጠና የሚፈለገውን ያህል ባለማግኘታቸው ሥራ ፈጣሪዎች የተለያዩ
የቢሮክራሲ፣ የፋይናንስ፣ የማምረቻ እና መሸጫ ቦታ ዕጦት እና ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸው መሰናክሎች በሚገጥሟቸው ጊዜ ተስፋ የመቁረጥ እና ገፍቶ ያለመሄድ
ችግር ይስተዋሉባቸዋል፡፡ ስለዚህ የወጣቶቹን ዕውቀት እና ክህሎት የሚያሳድግ በሥራቸው ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል ተከታታይ እና ለውጥ
ተኮር የሆነ የዓቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን እንዲያገኙ ማድረግ ተገቢ ነው። በመሆኑም መንግሥትም ሆነ የሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን
ትኩረት መስጠት አለባቸው። ሌላው ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ዋና ነጥብ የሥራ ፈጠራ እንደማንኛውም የትምህርት ዓይነት ራሱን ችሎ
ወይም ኬሎች የትምህርት ዓይነቶች ጋር ተጣምሮ በመደበኛ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ እንዲካተት ቢደረግ በችግሩ ላይ ሥር ነቀል የሆነ
ለውጥ እንዳሚመጣ ዕሙን ነው፡፡
መንግሥት ወጣቶችን በፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ
እና ኢኮኖማያዊ ተሣትፎ እና ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት ያደረጉ የወጣቶች ፖሊሲ እና ፓኬጅ ቀርፆ በትኩረት እየሠራ መሆኑ ለወጣቶች
መልካም አጋጣሚ የፈጠረ ነው፡፡ ይሄ ብቻውን የወጣቱን ችግሮች ስለማይቀርፍ ክፍተቶችን በማጥናት መፍትሔ መፈለግ እና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
ይህን ግምት ውስጥ በማስገባትም መንግሥት እና የሚመለከታቸው አካላት
ሥራ ፈጣሪዎች የሚያመርቱት፣ ምርት ከፈላጊዎች ጋር እንዲገናኙ፣ ትሥሥር እንዲፈጥሩ፣ ምርቶቻቸውን እንዲያስተዋውቁ እና የገበያ ፍላጎቶችን
በተመለከተ መረጃዎችን እንዲያገኙ እንዲሁም እርስ በእርስ እንዲተዋወቁ እና እንዲደጋገፉ አመቺ ሁኔታዎች በማመቻቸት ላይ ይገኛሉ።
በሀገሪቱ ያለው የኢንቭስትመንት ፖሊሲ
የሥራ ፈጠራን የሚያበረታታ እና ወጣቱን ወደ ኢንቨስትመንት የሚጋብዝ መሆኑን እና ለጥቃቅን እና አነስተኛ ልማት ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት
የሚሰጥ ነው። ከዚህ በተጨማሪ የሀገሪቱ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ለሥራ ፈጣሪዎች የሚሰጠው ማበረታቻ እና ሌሎች የተፈጠሩላቸውን መልካም
አጋጣሚዎች በመጠቀም ወጣቶች በሥራ ፈጠራ ራሳቸውን መለወጥ የራሳቸው ኃላፊነትቢሆንም፤ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች እንዲበራከቱ እና የሚያጋጥሟቸውን
ችግሮች ለመቅረፍ መንግሥትም ሆነ የሚመለከታቸው አካላት ከፍተኛ ኃላፊነት አለባቸው። ለዚህም ችግሩን ለዘለቄታው ለመፍታት ክፍተቱን
መለየት ቅዲሚያ የሚሰጠው ተግባር ነውና! ችግሩን ማወቅ የመፍትሔው ግማሽ ነውና!!
No comments:
Post a Comment