ስለእናቱ
ጉዳት ሲነገር የማይራራልብያለውየአዳም ዘር፤ስለ እህቱ መጠቃት ሲወሣ ውስጡ የማይብሰለሰል የሄዋን ልጅ፤ ስለ ሴት ልጅ መበደል በሰማ ጊዜ ለምን? ብሎ የማይጠይቅ ትውልድ፤ስለ ሴት ልጁ መብት መነጠቅ
ከቁብ የማይቆጥር ሰው ቀጣይ ለሚተካው የሰው ዘር ግድ የሌለው ወደ ፊት ለሚመጣው ትውልድ የማይጨንቀው መሆኑ ግልጽ ነው፡፡አዎ ትውልድን
የምታንጸዋ ሴት፤ ፍሬን ሰጥታ ትውልድን የምትቀጥለዋ ሄዋን፤የሰውን
ልጅ ገና ከመነሻውእንደ እርሳስ ከስር የምትቀርጸው ስብዕናውን ከማንም ቀድማ የምታንጸውእናት ህመም እና ጉዳትየማይሰማው ግድ የለሽ
ነው፡፡በዚህ ሰልጥኗል የሰው ልጅ ትልቅ ደረጃ ደርሷል በሚባልበት ዘመን ስለ ሴት ልጅ መብት መነጠቅ፣መበደል፣አካላዊና ስነ ልቦናዊ
ጥቃት መባባስ ተደጋግሞ ከአለም የተለያዩ ማዕዘናት በየዕለቱ ይደመጣል፡፡አለም ለዘመናት ከተኛችበት እንቅልፍ መንቃትዋን ብታውጅም
አንገትዋን የሚያሰብራት የሄዋን ሰቆቃ ግን አሁንም አልራቃትም፡፡አለም ለሴት ልጅን ዘርፈ ብዙ ችግሮችንአሁንም ማስቆም ወደ ኋላ
አቀበት የመውጣትን ያህል ሆኖባት ትግል ላይ ትገኛለች፡፡የመጪው ትውልድ ፍሬ አብቃይ ለሆኑት ሴቶችዛሬም አለም ምቹ አይደለችም፡፡
በስልጣኔ
ወደ ፊት ተራምደዋል አድገዋል የሚባሉት ሀገራት እንኳን የሴት ልጅን መብት በማስከበሩ ሂደት ከታዳጊ ሀገራት የተሻሉ ቢሆኑም ለወንዶች
የሰጡትን እድል ለሴቶች በማድረሱ በኩል አሁንም ችግሮች ይስተዋልባቸዋል፡፡ድምፃቸውን ከፍ አድርው የሴት ልጅ መብት ማክበራቸውን
ቢለፍፉም እውነታውን ሲታይ ግን ሌላ ነው፡፡የሴትን ልጅ ክብር በዘመነና በማይታይ መልኩ ይከሰክሱታል፡፡ መብትዋ እንዳታይ አድርገው
ይነጥቁዋታል፡፡ሴትዋን አስጊጠው የወንዱ
አጃቢ ከማድረግ ባለፈ እራስዋን ችላ በጎ ተጽዕኖ መፍጠር እንድትችል ሁኔታዎች ምቹ እዳይሆኑላት ይደረጋል፡፡ በምዕራቡ አለም አሁንም
ሴት ልጅ ለእኩል ስራ አኩል ደሞዝ የማታገኝበት ሁኔታ ይታያል፡፡ በአንድም በሌላም መልክ አሁን ድረስ ወሲባዊ ትንኮሳዎችና ጥቃቶች
ይደርሱባታል፡፡ በማታለያዎች የሰውነቷን ክብር ዝቅ ያደርጉባታል፡፡ማታለያዎችን እንደ ጭንብል አጥልቀው መጠቀሚያ ያደርጉዋታል፡፡ሰለጠንኩ
የሚለው የአለም ክፍል የሰለጠኑ ግፎችን በሴቶች ላይ ማድረሱን ቀጥሏል፡፡
በሌላው
የአለም ክፍሎችምሴቶች በሚፈጠሩ የስራ እድሎች ከወንዶች እኩል ተሳትፎ እንዳይኖራቸው፣ትምህርት እንዳያገኙ ተደርገው፣ስለ እራሳቸው
የመወያየት፣ስለመብታቸው የመጠየቅና በውሳኔ ሰጪነት የመሳተፍ መብታቸው ተጥሶ፣በማህበራዊ ኢኮኖሚውና በፖለቲካው ሁኔታዎች ሊኖራቸው
የሚገባውን ተሳትፎናመፍጠር የሚችሉት በጎ ተጽዕኖ መወጣት እንዳይችሉ መብትተነፍገው፣ለአካላዊና ስነ- ልቦናዊጥቃት ሰለባሆነው ይገኛሉ፡፡
እነዚህ ጫናዎችሴቶች በተለያዩ መስኮች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ከወንዶች ጋር ሲነጻጸር በጣም ዝቅተኛ እንዲሆንአድርጎታል፡፡
የአለምን ህዝብ ግማሽ ያህል ቁጥር የሚሸፍኑት ሴቶች በተነፈጋቸው እድል ምክንያት ውጤታማ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡ያላቸውን አቅም ተጠቅመው
ለማህበረሰቡ ሊፈጥሩት የሚችሉት ትልቅ ለውጥ እንዳይታይ አድርጎታል፡፡
ለሴት
ልጅ ክብር መስጠት ገና ያለመደ፤ለአለም ያበረከቱትን የላቀ አስተዋፅዖ አምኖ ያልተቀበለበት ማህበረሰብ ባለበት አለም የሴት ልጅን
በደል ማስቆምናተጠቃሚነትዋ ማረጋገጥ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ትግል መጠየቁ የማይቀር ነው፡፡በሴቶች ዙሪያ የሚሰሩ ተቋማት ቢበራከቱም
የሚፈለገው ለውጥ ማምጣት አልቻሉም፡፡ስለ ሴቶች መብት ተሟጋቾች ቢበረክቱም ትግላቸው በሚፈለገው ልክ በውጤት አልታጀበም፡፡ በማህበረሰቡ፣በአስፈጻሚ አካላት እና በራሳቸው ሴቶች ስለ ሴት ልጅ መብት
ያለው ግንዛቤ አሁንም በሚፈለገው ልክአለመሆን፣ከኢኮኖሚ ጥገኝነት ጋር በተያያዘ የሴቶች ስራ አጥነት ቁጥር ከፍተኛ መሆንና በአብዛኛው
የህግ ጥበቃና ማዕቀፍ በሌላቸው ስራዎች ላይ መሰማራታቸው፣በተለያዩ ቦታዎች ላይ ጾታዊ/ወሲባዊ/ትንኮሳዎች ለመከላከልና ለማስቆም
የሚያስችሉ የህግ ማዕቀፎችቢወጡም በአግባቡአለመተግበራቸውናበሴቶች መብት ላይ የወጡ አለም አቀፍ ህጎች በትክክል አለመተግበርየሴቶችን
መብት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ትግል ስኬታማ እንዳይሆን ያደረጉት
ተጠቃሽ ምክንያቶችናቸው፡፡
እነዚህ ከላይ የተቀመጡ ተግዳሮቶች የሴት ልጅን መብት በተገቢው ሁኔታ ላለመከበሩ
ምክንያት ተደርገው ቢታዩም ዋንኛው የመፍትሄ ቁልፍ ግን ማህበረሰቡ የሴቶችን መብት በማስከበሩ በኩል ተገቢው ተሳትፎ ማድረግ እንዲችል
ስለ ሴቶች መብት የሚያሳውቁና ግንዛቤውን ሊያሳድጉለት የሚችሉ የተጠናከሩ ስራዎች መስራት ወሳኙ ጉዳይ ነው፡፡የአንዲት ሴት የተሻለ
ቦታ መድረስ የቤተሰብዋ አጠቃላይ ለውጥ መሰረት መሆኑን ማሳወቅ ተገቢ ነው፡፡ያኔ አለም ይለወጣል፤ ማህበረሰቡ የሚሰጣት ቦታ ከፍ ይላል፤ተገቢውን
ቦታም ታገኛለች፡፡ማህበረሰቡ ስለ ሴት ልጅ ያለው እሳቤ ገና የሚቀረው መሆኑ ማሳያ ነጥቦች የበዙ ቢሆኑም በአንዲት ማሳያ ነጥብ
የሴቶችን ማህበረሰባዊ እይታ መለካት ይቻላል፡፡
አንድ ባለትዳርና ከሶስት ልጆቹጋር የሚኖርን አባወራ ስለ ስራው ብንጠይቀው የሚሰራውን በዝርዝር ያስረዳናል፡፡ቢሮ
ውስጥ ገብቶ ከመቀመጫው ሳይነቃነቅ የሚሰራው በየእለቱ ከሚተገብረው ከፍ ባለ መልኩ አጉልቶ ስራውን ያሳየናል፡፡የሱን ስራ አድካሚነት
በተከሸኑ ቃላት ሳይሰለቸው ይደረድርልናል፡፡ ፍቃደኛ ከሆነ የሱን ስራ መዘርዝርአስቁመን ወደ ቤቱመልሰነው የባለቤቱን ሁኔታ ብንጠይቀው
ስራ የላትም የሚል አጭር ምላሽ ይሠጠናል፡፡ ስራ የላትም የሚለውን ቃል እንደሱ በቀላሉ ሳናልፈው ቃሉ እኛ ጆሮ ጋር ሲደርስ አጉልተነው ስለ ባለቤቱ የማወቅ ፍላጎት ቢያድርብንና
የባለቱን ውሎ ማጥናት ብንጀምር የምናገኘው ውጤት ፈጽሞ ተቃራኒነው፡፡
ባለቤቱንጋት 12 ሰዓት ከመኝታዋ ተነስታ ለቤተሰቡ ቁርስ ማሰናዳት እና ለልጆችዋ ምሳቋጥራየትምህርት ቤት የደንብ
ልብሳቸውን ተኩሳ አልብሳ ወደ ትምህርት ቤት እስክትልክ ለአፍታ ቆም ብላ ትንፋሽዋን መሰብሰቢያ ጊዜ የላትም፡፡ከልጆችዋ ት/ቤት
ሁለቱን ሸኝታ አንዱን አድርሳ ወደ ቤትዋ መመለስዋን ተከትሎ ቤት ማጽዳት፣ እቃና የቤተሰቡን ልብስ ማጠብ፣ባለቤትዋ ከስራ ከመመለሱ
በፊት ምሳ ማዘጋጀት፣ የልጆችዋ መመለሻ ሲቃረብ መክሰስ አዘጋጅቶ ማብላት፣መሸትሸት ሲል ለቤተሰቡ እራት ማሰናዳትየእራት ሰዓት ሲደርስ
አብልታ የተበላበት እቃ አጥባ በንጋታው ለልጆችዋ ምግብ ለማዘጋጃ የሚረዱ ነገሮችን አሰናድታ ከምሽቱ 6 ሰዓት ላይ ወደ መኝታዋ
በስራ የዛለ ሰውነትዋ ለማሳረፍ ትሄዳለች፡፡ይህየሰርክ ስራዋ ነው፡፡ ከላይ በባለቤትዋ ስራ የላትም የተባለችው እናት ስትማስን የምትውለው
የቤተሰብዋን ውሎና አዳር ቀጥ አድርጋ የያዘችው እረፍት የለሽዋ እናት እውቅና ከባለቤትዋ አላገኘችም፡፡ እስዋ ለእሱ ስራ ፈት ናት፡፡
አስፍቶ ማየት ተስኖት የቤቱ መሪ እስዋ መሆንዋን መመልከት እንዳይችል አድርጎ ማህበረሰቡ ቀርጾታል፡፡ ይህ ነው ማህበረሰቡ ሴት
ልጅ የምታበረክተውን ትልቅ አስተዋጽዖ መመልከት ያልቻለበት ማሳያ ነው፡፡
ማህበረሰባችን ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ማህበረሰባዊ ልማዳችን በሴት ልጅ ላይ ያለው አተያይ ገና አልተስተካከለም፡፡ሴት
ልጅ እያበረከተችው ያለውን ትልቅ ጠቀሜታ ገና አልገባውም፡፡ ቤተሰብ የማነጽ እና ጎጆን የማቃናት ተግባርዋን የማህበረሰቡ አይን
እስካሁን አልተመለከተውም፡፡ እንደ እድል ኢኮኖሚውን በበላይነት ተቆጣጥሮ ዱቄት መግዣ የሚሆን ሳንቲም የሰጠ አባት ውሀ ቀድታ አቡክታ
ቅምም መጥና አብስላና ለምግብነት አጣፍጣ የምታቀርበዋን ሚስቱ እጆችበእርሱ የሚተዳደሩ ስራ ፈት አድርጎ ይቆጥራቸዋል፡፡ ምናልባትም
ለልጆቹ የትምህርት ወጪያቸወን ስለሸፈነ በየእለቱ ለለውጣቸው እየተጋች ለምቾታቸው የምትጨነቀዋን እናት ለውጣቸውን እየተከታተለች
የምታንጸዋ ሴት በሱ አይን ምንም አይደለችም፡፡
ለሴት ልጅ መብት መከበር ደጀን የሚሆን ማህበረሰብለመፍጠር ስለ ሴት ልጅመብት ግንዛቤውን ማስፋትና ለሴት ልጅ ትልቅ
ክብርና ቦታ መስጠት ተገቢነቱንማስረዳትና የመብታቸው መከበር ያለውን ጠቀሜታ አጉልቶ ማሳየት ተገቢ የሚሆነው ለዚህ ነው፡፡ለማህበረሰቡም
ስለ ሴትልጅ መብት በማሳወቁ በኩል ትልቅ ጥረት ሊደረግ ይገባል፡፡ከራስዋ አልፋ ማህበረሰቡን ብሎም አለምን መለወጥ እንድትችል መርዳት
ይገባል፡፡በተለያየ መልኩ መብትዋን የሚጋፉ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ሊከላከልላት አብሯት ሊቆም ግድ ይላል፡፡ሴት ልጅ ለትምህርት ልኮ ነገ
የተሻለ ህይወት እንዲገጥማት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ የወደፊት ማህበራዊ ለውጥ ወሳኝ እና ትልቅ አቅም መፍጠር መሆኑን መረዳትና
ቤተሰቡን በተገቢው መሰረት እያነጸ መሆኑን ማመን አለበት፡፡ለሴት ልጅ ተገቢውን ትኩረት መስጠት መብትዋን ማረጋገጥ የነገን አለም
በተሻለ ሁኔታ መገኘት ዋንኛ ጉዳይ መሆኑ ሊታመንበት የሚገባ እውነታ ነው፡፡
የሴት ልጅን መብት በማረጋገጡ በኩል የተለያዩ ሀገራት የችግሩ መፍትሄ ይሆነናል
የሚሉዋቸውን እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛሉ፡፡ በሚወስዱት ዘርፈ ብዙ የሴቶችን መብት የማስከበር ስራዎች ለውጦችን ካመጡ ሀገራት
ኢትዮጵያ ተጠቃሽዋ ናት፡፡የሴት ልጅ ግርዛት፣ጠለፋ፣ያለ
እድሜ ጋብቻ እና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን የመሳሰሉት በኢትዮጵያ ሴቶች ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ የሚያሳድሩ የመብት ጥሰቶች በተሰራው
ስራ ከፍተኛ ለውጥ ታይቷል፡፡ በዚህም የሴቶች ማህበራዊ ፖለቲካዊ ተሳትፎ ማደግና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከጊዜ ወደ ጊዜ ለውጥ እያሳየ
ይገኛል፡፡
ለሴቶችንተገቢው ቦታ
መስጠትና መብታቸው ማክበር ተገቢ መሆኑን የተረዳችውኢትዮጵያ የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመፍጠር የሴቶችን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለመፍታት
ጥረት በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡ይህ ጥረትዋ ያመጣወን ለውጥ መመልከት ይቻላል፡፡
በዚህም የሴቶች፣
ሕፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር በፌደራል ደረጃ የሴቶችን ጉዳይ ቀጣይነት ባለውና አሳታፊ በሆነ መዋቅር እንዲመራ በአዋጅ ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡ሌሎች
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችም በሥራቸው መስክ በሚያዘጋጇቸው ፖሊሲዎች፣ ህጎች፣ የልማት ኘሮግራሞች እና ኘሮጀክቶች ውስጥ የሴቶችን ጉዳይ
ማካተት እንዳለባቸውም ተደንግጓል፡፡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ደረጃም ሴቶች በሕገ-መንግስቱ የተረጋገጡላቸው መብቶች መተግበራቸውን
የሚከታተል የሴቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡ በክልሎችና በከተማ መስተዳድሮች የሴቶችን ጉዳይ የሚከታተሉቢሮዎች ተቋቁመዋል፡፡እነዚህ
አደረጃጀቶች ለሴቶች መብት መከበር ትልቅ አስተዋጽዖ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡
በኢትዮጵያ ህገ መንግስት የሴቶች
መብት ማረጋገጥ የሚያስችሉ ከአለም አቀፍ ህጎችጋር የተጣጣሙ ህጎችተደንግገው በመተግበራቸው ሴቶች በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ
ተሳፎዋቸውን የሚያሳድጉበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮላቸዋል፡፡ በተለያዩ አደረጃጀቶች በመሳተፍ የራሳቸው እድል በራሳቸው መወሰን እንዲችሉ
ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮላቸው እድሎችን በመጠቀም ፖለቲካዊ ተሳትፎዋቸው ያሳደጉ ሲሆን የሴቶችንየፖለቲካተሳትፎከማጎልበትአኳያበፌዴራልደረጃበፓርላማ
27.8 በመቶ፣በህግተርጓሚ 20.6 በመቶናበአስፈጻሚአካላትየፖለቲካአመራር
9.2 በመቶማድረስተችሏል፡፡ይህ ካለፉት ጊዜያት ጋር ሲነጻጸር ትልቅ ለውጥመኖሩን ያመለክታል፡፡
በሌላ በኩል በአንደኛው የእድገትና
ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈጻጸም ወቅት የሴቶችን የመሬት ተጠቃሚነት መብት ከማረጋገጥ አንፃር
11.11 ሚሊዮን (2 ሚሊዮን እማወራ እና 9.11 ሚሊዮን በጥምር ሴቶች) መሬት
ተጠቃሚነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት አግኝተዋል፡፡ እንዲሁም የሥራ ጫና ለመቀነስ 3.4 ሚሊዮን ሴቶችን በአማራጭ ኢነርጂና በሌሎች የተለያዩ ተስማሚ ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
በኢንዱስትሪ ዘርፍ የሴቶች ተሳትፎ እያደገ በመምጣቱ ስራአጥነት እየቀነሰ፣ ገቢያቸው እያደገ መጥቷል፡፡ በጥቃቅንና አነስተኛ ልማት
ዘርፍ በንግድ ሥራ አመራር 1.13 ሚሊዮን፣
በየደረጃው በተካሄዱ የግንዛቤና ንቅናቄ ስራዎች 2.2 ሚሊዮን ሴቶች በጥቃቅንና አነስተኛ እና 1.8 ሚሊዮን
በራስአገዝ ማህበራት ተደራጅተው ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
የሴቶችን ገቢ ለማሳደግና ከኢኮኖሚያዊ
ጥገኝነት ተላቀው እራሳቸውን ብሎም ማህበረሰቡን መለወጥ እንዲችሉ ስራ በመፍጠርና የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ከማድረግና የቁጠባ
ባህላቸውን ከማዳበር አንፃር ከአበዳሪ ድርጅቶች ጋር በተፈጠረው ቅንጅታዊ አሰራር
6.62 ሚሊዮንሴቶችና 80,148 የሴት አደረጃጀቶች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ በዚህም በአጠቃላይ ብር 2 ቢሊዮን ብድር በመውሰድ ሥራ ላይ ያዋሉ ሲሆን የቁጠባ ባህልን እንዲያዳብሩ በተፈጠረው
ምቹ ሁኔታ ብር 2.82 ቢሊዮን መቆጠብ ችለዋል፡፡
ከላይ የተጠቀሱት ለውጦች አበረታች
ቢሆኑም በሴቶች ላይ የሚስተዋሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮችና የመብት ጥሰቶች ዛሬም ላይ የበዛ በመሆኑ ማስተባበል የማይቻል ሀቅ ነው፡፡በመሆኑም
የሴቶችን መብት በማስከበሩ እና ተጠቃሚነታቸው በማረጋገጡ በኩል ከዚህ በላይ መስራትና ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግራቸውን
መቅረፍ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ያለባቸውን ጫና ለመቀነስ ከዚህ በላይ መስራት፣ ችግራቸውን ለመቅረፍ ይበልጥ መትጋት ወሳኙ
ጉዳይ ነው። ምክንያቱም ብዙ እናቶች አሁንም የሚገባቸውን ክብር እና ጥቅምእያገኙ አይደለም።ብዙ እህቶች ዛሬም ከስቀያቸው አልተገላገሉም፡፡ይህን
ለመለወጥ ደግሞ ጠንካራ ስራወሳኝ ነው፡፡
በመንግስት በኩል እስካሁን የተደረገው
ጥረት ሴቶችን በማሳተፍና ተጠቃሚነታቸው በማሳደግ ረገድወደፊትም የተሻለ ለውጥ መፍጠር እንደሚቻል ያሳየ ነው፡፡ ለሴቶች እየተደረገ
ያለው ድጋፍና መብታቸው እንዲከበር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ይበልጥ ተጠናክረውመቀጠልይኖርባቸዋል፡፡ እናቶች ክብር ማግኘት ይገባቸዋል፤እህቶች
እንክብካቤና ድጋፍ ያሻቸዋል፤ሚስቶች ዘውድነታቸውን አምኖ መቀበል ግድ ይላል፡፡ ያኔ ቤተሰብ ይለወጣል፤ይህ ሲሆን የማህበረሰብ ንቃት
ከፍ ይላል፤የሴት ልጅ መብት ሲከበር ሀገር ትቀናለች፤ የሄዋን በደል
ሲቆም የእናቶች ስቃይ ሲያበቃ አለም ትደምቃለች ፤ያን ጊዜ ምድር ለሁሉትመቻለች፡፡የተቃና ትውልድ ለመፍጠር የሴቶችን መብት ሳንሸራርፍ
አክብረን እናክብር መልዕክቴ ነው፡፡
No comments:
Post a Comment