ኢብሳ
ነመራ
የተማሪዎች ዕውቀት እየተመዘነ ከፍ ወዳለ የትምህርት
እርከን የሚሸጋገሩበትን ፈተና መስረቅ በየትኛውም መለኪያ አስነዋሪ
ድርጊት ቢሆንም “ፈተናው ተሰርቋል፣ እጃችን ገብቷል ወዘተ.” እያሉ ውዥንብር የሚነዙ ቡድኖችን ስናዳምጥ ሰንብተናል። አንዳንዶቹ
ሰርቀነዋል ያሉትን ፈተና በማህበራዊ ሚዲያዎች እስከመልቀቅ የደረሱበት ሁኔታ ነበር። ይህ ተሰረቀ ተብሎ የተነዛ ፈተና ግን ሃሰተኛ
ነበር።
በፈተናው ዋዜማ እሁድ ሃምሌ 3 ይህን ተሰረቀየተባለው ፈተና በተለይ አዲስ አበባ ውስጥ በርካታ ተማሪዎችእጅ
ገብቶ ነበር። ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች እሁድ እለት ይህን ፈተና አየተቀባበሉ፣ ፈተናውይገኝበታል ወደተባለ ቦታ እየሄዱ
ይህን በእጃቸው የገባ ሃሰተኛ የፈተና ቅጅ ሲሰሩና ለአዋቂ ሲያሰሩ ነበር። ፈተናው በማህበራዊ ሚዲያ መለቀቁን የሰሙና ማህበራዊ
ሚዲያዎችአልከፈትያሏቸው ተማሪዎች ኔትዎርክ አለ የተባለባቸው
ራቅ ያሉ አካባቢዎች ድረስ እየሄዱ ዕለቱን ያለስራ ያባከኑበትን ሁኔታም ታዘበናል። በተለይ አዲስ አበባ በተለምዶ 22 ማዞሪያ ተብሎ
የሚጠራው አካባቢ ኔት ዎርክ አለ የሚል ወሬ ተነዝቶ ከዚህ አካባቢ
ርቀው የሚገኙ ተማሪዎችበአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ የኦሮሚያ አካባቢዎች የሚኖሩ ተማሪዎች ጭምር ወደዚያ ቦታ ሲጎርፉ ውለዋል። ከማህበራዊ
ሚዲያ ላይ ፈተናውን ለማግኘት። እሁድ ሌሊት ፈተናው ይገኝበታል በተባለበትየማያውቋቸውሰዎትቤትሄደው ያደሩ ተማሪዎችምቁጥር ቀላል
አልነበረም። ተሰረቀ ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውንፈተና መልስ
ይዘው ወደፈተና አዳራሽ ሲገቡ የተያዙ ተማሪዎችም ነበሩ።
በሌላ በኩል በራሳቸው የሚተማመኑና በተሰረቀ ፈተና
ወደዩኒቨርሲቲ መግባትን የሚጸየፉ ጎበዝ ተማሪዎች የበለጠ ግራ ተጋብተው ነበር። ተሰረቀ በተባለው ፈተና ሽሚያ ውስጥ እንዳይገቡ
ህሊናቸው አለፈቅድ አላቸው። ፈተናው በሁሉም ተማሪ እጅ ገብቶ የልፋታቸውን ወጤት ሊያረክሰው የሚችል መሆኑ ደግሞ አሳሰባቸው። በዚህ
ሁኔታ በጭንቀት ውስጥ የሰነበቱ በርካታ ጎበዝ ተማሪዎች ነበሩ። የኢፌዴሪ የትምህርት ሚኒስቴር ግን ፈተናው እንዳልተሰረቀ ማስተማማኛ
ሰጥቶ ነበር። መላ ተማሪው እንዲረጋጋ፣ ወላጆችም ልጆቻቸውን እንዲያረጋጉ አሳስቦ ነበር።
ተፈታኝ ተማሪዎችከፈተናው ቀደም ባሉት ጥቂት ቀናት
የአንድ ዓመት የጥናት ዝግጅታቸውንበአእምሯቸውአደራጀተው ዘና ብለውለፈተና መዘጋጀት የነበረባቸው ቢሆንም፤የተወሰኑቱ የትምህርት ሚኒስቴርን
ማሳሰቢያ ችላ ብለው ባልተጨበጠ ነገር ባዝነዋል። ይህ በቀጣይ ውጤታቸው ላይ አሉታዊ ተፅእኖ የሚያሳድር መሆኑ የሚያጠያይቅአይደለም።
በዚህ ሁኔታ ሲባዝኑ ሰንብተው በተረበሸ ስሜት ለፈተና ቀርበው ጉዳት ለሚደርስባቸው ተማሪዎች ተጠያቂው ማን ይሆን?
ወላጆች የትምህርት ሚኒስቴርን ማሳሰቢያ አድምጠው ልጆቻቸው
እንዲረጋጉ የማድረግሃላፊነት የነበረባቸው መሆኑ ሳይዘነጋ፣ ዋናዎቹ ተጠያቂዎች ግን ፈተናውን ሰርቀናል አያሉ ሲፎክሩ የነበሩና የፈጠራ
ፈተና በማህበራዊ ሚዲያ የለቀቁ ሞራል የጎደላቸው “ዱርዬዎች” ናቸው። እነዚህ ሰዎች ፍፁም ስነምግባር የጎደላቸው፣ በተለይ ገና
በለጋ የወጣትነት እድሜ ላይ ለሚገኙና ወደላቀ የትምህርት ደረጃ መሸጋጋር ለሚያጓጓቸው ተማሪዎቸ ምንም ደንታ የሌላቸው ክፉ ሰዎች ናቸው።
ይህ ሞራለቢሰ የሆኑ ሰዎች የሰረቅነው ፈተና እያሉ በየአቅጣጫው በማህበራዊ ሚዲያ የፈጠራ ፈተና እንዲያሰራጩ
እስከመጨረሻው መረን ተለቅቀው ቢሆን ኖሮበሚፈጥሩትውዥንብርየተነሳ በርካታ ተማሪዎች ይጎዱ ነበር። መንግስት ሀላፊነት የማይሰማቸው
ሞራለ ቢስ “ዱርዬዎች” በሚፈፅሙት ተግባር ተማሪዎች ሲጎዱ ዝም ብሎ መመልከት አልነበረበትም። ተማሪዎቹን ከ“ዱርዬዎች” ጥቃት ለመከላከል
የነበረው አማራጭ ፈተናው ተሰጥቶ እስኪያልቅ ማንም እንደፈለገ የሚፈነጭባቸውንና ተጠያቂ የሌላቸውን ማህበራዊ ሚዲያዎች መዝጋት ነበር።
እናም ይህን አደረገ።
ፈተናው በተሰጠባቸው ቀናት የማህበራዊ ሚዲያዎች በተለይ
ፌስ ቡክ፣ ቲዩተር፣ ኢንስታግራም፣ ቫይበርእንዲዘጉ የማደረጉ ዓላማ ይሄ ብቻ ነው። መንግስት በወሰደው በዚህ እርምጃ የጉዳዩ ቀዳሚ
ባለቤቶች የሆኑት ተማሪዎች፣ የተማሪዎቹ ወላጆችና መምህራን ደስተኞች መሆናቸውን ገልፀዋል። እርምጃውን ተገቢ እርምጃ ብለውታል።
ማህበራዊ ሚዲያዎቹ በተወሰነ ደረጃ በተፈታኞቹ ላይ የፈጠሩትን አሉታዊ ተፅዕኖ ያስተዋሉ ቅን ዜጎችና የጉዳዩ ቀዳሚ ባለቤቶች በሙሉ
ማህበራዊ ሚዲያዎቹ ፈተናው እስኪያልቅድረስ መዘጋታቸውንበአንድ ድምፅ ተገቢ
ነው! ሲሉ ደግፈዋል።
ይሁን እንጂ፤ ማህበራዊ ሚዲያዎቹ ፈተናው እስኪጠናቀቅ
እንዲዘጉ የተቃወሙ ድምጾችም ተሰምተዋል። የተቃውሞ ድምፅ ያሰሙት ወገኖች የተለያየ አቋም ያላቸው ናቸው። በአንድ ወገን ያሉት ማንኛውንም
የመንግስት እርምጃ፣ የልማት ስራዎች ጭምር የተቃውሞ አጀንዳ ለማድረግ የሚራወጡ በጥላቻ የታወሩ ወገኖች ናቸው።የእነዚህአቋም ላይ
አስተያየት መስጠትከንቱ ድካም ነው፤ለማንኛውም አስተያየት ራሳቸውን ዝግ ያደረጉ በምርጫቸው ላይቃኑ የተጣመሙ በመሆናቸው።
በሌላ በኩልከቅንነት ከመነጨ ስጋት ተቃውሞ ያቀረቡ
አሉ። እነዚህ ወገኖች መንግስት ሃሳብንየመግለፅ ህገመንግስታዊ መብት ማረጋገጫ የሆኑትንማናቸውንም አይነት ሚዲያዎች በማንኛውም ሁኔታ
መዝጋት የለበትም ባዮች ናቸው።ለዚህ አቋማቸው የሚያቀረቡት መከራከሪያ፤ፈተናውእንዲሰረቅ ያደረገው ምክንያት የማህበራዊ ሚዲያ መኖር
አይደለም፣እናም መንግስት ማተኮር ያለበት ፈተና እንዳይሰረቅ በሚያደርጉ አሰራሮች ላይ ነው እንጂ ፈተናው ከመሰረቁ ጋር ምንም ግንኙነት
በሌላቸው ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ መሆን የለበትም፤የሚል ነው።
እርግጥ ነው የፕሬስ ወይም የሚዲያ ነፃነት ሃሳብን
የመግለፅ መሰረታዊ መብትና ነፃነት እውንየሚሆንበት በመሆኑና ኢትዮጵያም ሃሳብን የመግለፅ ነፃነት በህገመንግስት ስላረጋገጠች፤ ሚዲያ
በመንግስትም ሆነ በማንም አካል ሊታገድ አይገባም። ይሁን እንጂ ይህ ማለት ሚዲያ ምንም ዓይነት የህግና የሙያ ስነምግባር ገደብ
የለበትም፣ በማንኛውም ሁኔታ ከተጠያቂነት ውጭ ነው ማለት አይደለም።
በሚዲያ ላይ የሚጣለው ገደብና ተጠያቂነት ከሌሎች መብትና
ነፃነት የመነጨ ነው። ሚዲያ የሌሎችን ህይወት ለአደጋ የሚያጋልጥ፣ በተሳሳተ መረጃ ሰጋትና ቅሬታ የሚቀሰቅስ፣ የሰዎች ማህበራዊና
ኢኮኖሚያዊ ህይወትላይ አሉታዊ ተፅእኖ የሚያሳድር፣ሰብአዊ ክብራቸውን የሚነካ፣ ሁከትና ትርምስ የሚያነሳሳ . . . መረጃ የማሰራጨት
መብት የለውም። ህግም የሞያ ስነምግባርም ይህን እንዳያደርጉ ይከለክላቸዋል።
የሚዲያ ወይምየፕሬስ ነፃነትበሌሎች መብትና ነፃነት የተገደበ ነው።
ማህበራዊ ሚዲያ በባህሪው ተጠያቂነት የለበትም። የጥሩና
የክፉው ጎራ ተደበላልቆ የተሰለፈበት ነው። በመሆኑም አደጋ የሚስከትል ሁኔታ ሲያጋጥም የጥሩዎቹን ለቅቆ የክፉዎቹን ነጥሎ ማገድ
አይቻልም። ስለዚህ ሊያስከትሉ የሚችሉትን አደጋ ማስቀረት የሚቻለው የአደጋ ስጋት ባለባቸው ጊዜዎች ሁሉንም በመዝጋት ነው። ይህ
በማንኛውምአገር ሊደረግ የሚችል ነው። ከአራት ዓመት በፊት እንግሊዝ ውስጥ ሁከት በተቀሰቀሰ ጊዜ የእንግሊዝ መንግስት ሁከቱ ካልቆመ
በጥባጮቹ ለቅስቀሳ የሚጠቀሙበትን ፌስ ቡክ እንደሚዘጋ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ እንደነበር ልብ በሉ።
ሰሞኑን በኢትዮጵያ የማህበራዊ ሚዲያዎች ፈተናው እስኪጠናቀቅ
ድረስ ለሶስትና አራት ቀናት እንዲታገዱ የተደረገው ቀደም ሲልእንደተገለፀው ሃሰተኛ መረጃ በመንዛት ተፈታኝ ተማሪዎች ላይ ውዥንብር
በመፍጠር በተማሪዎቹ ውጤት ላይ አሉታዊ ተጽአኖ የሚፈጥር ድርጊት ማሰራጫ ሆነው በመገኘታቸው ነው።እናም ማህበራዊ ሚዲያዎቹን የመዝጋት
እርምጃው የተወሰደው ከ250 ሺህ በላይ የሚሆኑ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን ለህግና ለሞያ ስነምግባር ተገዢ ያልሆኑ “ዱርዬዎች”
በሚፈጥሩት ውዥንብር ሊደርስባቸው ከሚችል ጉዳት ለመታደግ ነው።
እርግጥ ነው ፈተናው እንዲሰረቅ የሚያደርገው የማህበራዊ
ሚዲያ መኖር አይደለም። የማህበራዊ ሚዲያዎች በሚስጢር መጠበቅያለባቸው ፈተናዎች ከተሰረቁ በኋላ የሚሰራጩበት መንገድ በመሆናቸው
ነው። በመሆኑም የፈተና ስርቆትንና የሚያስከትለውን ጉዳት መከላከል የሚያስችለው መሰረታዊ መንገድ የፈተና አዘገጃጀትና አያያዝ ላይ
ያለውን የአሰራር ስርአት በማስተካካል ነው። መንግስት የመጀመሪያው ፈተና መሰረቁን ካወቀ በኋላ በድጋሚ ፈተና ሲያዘጋጅ ምስጢራዊነቱን
መጠበቅ የሚያስችል አስተማማኝ ስርዓት ዘርግቷል። በዚህ ላይ እምነት ነበረው።
አሁን መንግስት ማህበራዊ ሚዲያዎቹን የዘጋው ፈተና
እንዲሰረቅ ያደርጋሉ፣ ወይም ፈተና ሊሰረቅ ይችላል የሚል ስጋት ስላለበት ወይም የተሰረቁ ፈተናዎች እንዳይሰራጩ በመስጋት አይደለም።መንግስት
ፈተናዎች ሊሰረቁ የማይችሉበትንአዲስ ጠንካራ የአሰራር ስርአት ስለዘረጋ ፈተናው ሊሰረቅ እንደማይችል በተደጋጋሚ ሲገልፅቆይቷል።
የመንግስት ስጋት ፈተናው ይሰረቃል ከሚል የመነጨ ሳይሆን ይልቁንም ፈተናው ሳይሰረቅ ተሰርቋል በሚልበሚሰራጩ ሃሰተኛ የፈተና ሰነዶችና
መልሶችበተማሪዎች ላይ የሚፈጠረውን ውዥንብርና ውዥንብሩ ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ለመከላከል ነው።
No comments:
Post a Comment