ደቡብ ሱዳን ተፋላሚዎች ግጭት ከሚያባብሱ እንቅስቃሴዎች እንዲቆጠቡ የኢጋድ ሊቀመንበር አሳሰቡ
ግጭቱን በተመለከተም ኢጋድ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
በደቡብ ሱዳን ከሁለት ዓመት በላይ የዘለቀውን የእርስ በእርስ ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታተ በኢጋድ፣ በአፍሪካ ህብረትና በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ያላሰለሰ ጥረት ሁለቱን ተፋላሚ ሀይሎች የሸግግር መንግስት ለማቋቋም ከአራት ወራት በፊት ስምምነት ተደርሶ ነበር፡
ይሁንና ከሰሞኑ በሁለቱ ተፋላሚ ሀይሎች በተቀሰቀሰው ግጭት በትንሹ 239 ታጣቂዎችና 33 ነጹሀን ዜጎች ህይወታቸው አልፏል፡፡
ይህን ተከትሎም የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የወቅቱ ሊቀመንበርና ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በላኩት መግለጫ ሁላቱ ተፋላሚ ሀይሎች ግጭቱን ሊያባብሱ ከሚችሉ ድርጊቶች ሊቆጣቡ እንደሚገባ አሳስበዋል፡
ተፋላሚ ሀይሎቹ ሰላማዊ አማራጮችን መከተል ካልቻሉ ግጭቱ ለበርካታ ዜጎች እልቂት ምክንያት ከመሆኑም በላይ አገሪቱን ማለቂያ ወደ ሌለው ቀውስ ውስጥ ሊከታት እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡
የተፈጸመው ድርጊት የኢጋድን የቀጣናውን አገራት ብሎም የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በአገሪቱ ሰላም የማስፈን ጥረትን ዋጋ ቢስ ያደረገ ተግባር ሲሉም በመግለጫው አውግዘውታል፡፡
የሊቀመንበሩ መግለጫ እንደሚያመለክተው አሁን የተፈጠረውን ሁኔታ የኢጋድ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በቀጣይ የሚመለከተው ይሆናል።

No comments:
Post a Comment