ኢብሳ
ነመራ
በርካታ
ሃገራት እንደየታሪካዊ ሁኔታቸው በተለያየ መነሻ የሰንደቅ ዓላማ ቀን
ያከብራሉ። ገሚሶቹ የነጻነት ቀናቸውን መነሻ ሲያደርጉ፣ ሌሎች ደግሞ ሰንደቃላማቸው ለመጀመሪያ ግዜ የተውለበለበበትን ወይም ሰንደቃላማቸው
በህግ የጸደቀበትን እለት መነሻ በማድረግ ያከብራሉ። ለአብነት ያህል አሜሪካውያን በየአመቱ ጁን 14 ላይ የሰንደቃላማ ቀናቸውን
ያከብራሉ። ጁን 15፣ 1777 ዓ/ም የአሜሪካ ሰንደቅ ዓላማ ህጋዊ እውቅና ያገኘበት እለት ነው። ሩሲያውያን ኦገስት 22 የሰንደቃላማ
ቀናቸውን ያከብራሉ። አሁን በአገልግሎት ላይ ያለው የሩሲያ ሰንደቅ ዓላማ ኦገስት 22፣ 1991 ዓ/ም ተሞክሮ ከከሸፈው መፈንቅለ መንግስት በኋላ በታላቁ የሶቪየት ህንጻ ላይ የተውለበለበበትን
እለት ነው። ጣሊያናውያን የበለሶስት ቀለማት በዓል እያሉ የሚጠሩትን የሰንደቅ ዓላማ ቀናቸውን ጃኑዋሪይ 7 ላይ ያከብራሉ። ጃኑዋሪይ
7፣ 1797 በቁመት የተደረደሩ አረንጓዴ፣ ነጭ እና ቀይ ቀለማት ያለው ሰንደቃላማቸው ህጋዊ እውቅና ያገኘበት እለት ነው።
ሃገራችን
ኢትዮጵያም በየዓመቱ ብሄራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ታከብራለች፤ ጥቅምት ወር በገባ የመጀመሪያ ሰኞ ዕለት። ይህ ዕለት የብሄራዊ ሰንደቅ
ዓላማ ቀን ሆኖ እንዲከበር የተወሰነው የሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ቁጥር 654/2001ን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 863/2006
ነው። ይህ አዋጅ በአንቀጽ 4 የሰንደቅ ዓላማ ቀን በሚል ርዕስ
ስር፣ ብሄራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በየዓመቱ ጥቅምት ወር በገባ የመጀመሪያ
ሰኞ በአገር አቀፍ ደረጃ ይከበራል ይላል። በዚህ መሰረት የ2009 ዓ/ም የሰንደቅ ዓላማ ቀን ለ9ኛ ግዜ ሰኞ ጥቅምት 7
በሃገር አቀፍ ደረጃ ተከብሯል።
የዘንድሮው
የሰንደቅ ዓላማ ቀን እንደወትሮው በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣ የመከላከያና የፖሊስ ሰራዊት አባላት፣ እናትና
አባት አርበኞች ወዘተ በሚሳተፉበት፣ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት በበታው ተገኝተው የሰንደቅ ዓላማ መስቀል ስነስርአት በሚያከናውኑበት ሁኔታ
ሁኔታ አልተካሄደም። ይህ የሆነው በተለያያ የሃገሪቱ አካባቢዎች የተቀሰቀሱ በተለይ ያሀገር ሃብት ማወደም ላይ ያነጣጠሩ ሁከቶች
በሃገሪቱ ላይ የጋረጠውን አደጋ ለመከላከል በታወጀው የአስቸኳይ ገዜ አዋጅ ምክንያት ነው። ይህ ሁኔታ ለእለቱ ቀደም ሲል ከነበሩት
ዓመታት ለየት ያለ ድባብ የሰጠው ቢሆንም በአሉ በመንግስት መስሪያ ቤቶችና በትምህርት ቤቶች እንደወትሮው ተከብሯል። በተለይ ከ1ኛ
እሰከ 2ኛ ደረጃ ባሉ ትምህርት ቤቶች በአሉ በደማቅ ሁኔታ ነበር የተከበረው።
የዘንድሮውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን መነሻ በማድረግ ይህን አጭር ጽሁፍ እንዳዘጋጅ ያነሳሰኝ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ
ተሾመ በሰንደቅ ዓላማ ቀን ዋዜማ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ያደረጉት
የእንኳን አደረሳችሁ ንግግር ነው። ፕሬዝዳንት ሙላቱ በንግግራቸው ያነሱት ሃሳብ የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ
ለኢትዮጵያውያን ያለውንና ሊኖረው የሚገባውን ትርጉም በአጭሩ በግልጽ አስቀምጠዋል። ፕሬዚዳንት
ሙላቱ
ተሾመ
በሰንደቅ ዓላማ ቀን ዋዜማ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ
ባስተላለፉት
የእንኳን
አደረሳችሁ
መልዕክት፤ ሰንደቅ
አላማ የየሀገሮች
መለያ
ምልክት
ተደርጎ ሊወስድ
ይችላል።
ለኛ
ኢትዮጵያውያን
ግን
ከዚህ
በላይ
የጠለቀና
የረቀቀ
ትርጉም አለው።
ከታሪካችን
አንፃር የነፃነታችን
ጉልህ
አርማ
ነው።
ከብዝሃነታችን
አንፃር
ደግሞ
በመፈቃቀድ
ላይ
የተመሰረተው የዲሞክራሲያዊ
አንድነታችን
መገለጫ
ምልክታችን
ነው።
በአጠቃላይ
የኢትዮጵያ
ሰንደቅ
አላማ
የመላው
የሀገራችን
ብሔሮች፣
ብሔረሰቦችና
ሕዝቦች
ዘመን
ተሻጋሪ
ትግልና
ድል
የዘላቂ
ሰላም
የብሔራዊ
እኩልነት፣
የዲሞክራሲያዊ
እኩልነትና
በራሳችን
ትጋትና
ጥረት
ዳግም
የስልጣኔ
ማማ
ላይ
ለመውጣት
የምናደርግው
ትግልና
የውጤቱም
አርማ
ነው ብለዋል።
ይህንን ሃሳብ ፈታ አድርገን እንመልከተው።
የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ለኢትዮጵያውያን የነጻነታቸው ጉልህ ዓርማ ነው።
ኢትዮጵያ በአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች ሳትያዝ ነጻነቷንና ሉዓላዊነቷን ያለማንም ድጋፍ በራሷ ልጆች መስዋዕትነት ጠብቃ የኖረች ብቸኛ
የአፍሪካ ሃገር ነች። በ1888 ዓ/ም በአድዋ ጦርነት የጣያሊንን ወራሪ ሃይል ድል በመንሳት ነጭ አውሮፓውያን ወራሪዎች በጥቁሮች
ሊሸነፉ እንደሚችሉ ለመላው የአፍሪካ፣ የካረቢያን፣ የኢሲያ ህዝቦች በማሳየት ነጻነቷን አጽንታለች። በአውሮፓውያን ቅኝ ግዛት ስር
ለነበሩ ህዝቦች በሙሉ የነጻነት ተነሳሽነት ከፈጠረው የአድዋ ድል በኋላ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ ብሩህ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት
ያለውን ሰንደቅ ዓላማ ህጋዊ ሰንደቅ ዓላማዋ አድርጋ ማውለብለቧን የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። በዚህ ምክንያት እነዚህን ሶስት ህብረቀለማት
የያዘው ሰንደቅ ዓላማ የፓንአፈሪካኒዝም መለያ ለመሆን እስከመብቃት ደርሷል። የተለያዩ የአፈሪካ ሃገራት ከነጻነታቸው በኋላ በተለያየ
አደራደር ባለአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት ያሉት ሰንደቃላማ እንዲኖራቸው ያደረጉት በዚህ ምክንያት መሆኑንም ታሪክ ያስረዳል።
ኢትዮጵያውያን በ1928 ዓ/ም ይህን አረንጓዴ
ቢጫና ቀይ ቀለማት ያሉት ሰንደቃላማቸውን አንግበው ከአድዋ ድል አርባ ዓመታት በኋላ የሽንፈት ቂሙን ለመበቀል ዳግም ወረራ የሞከረውን
የጣሊያን ሃይል በአምስት ዓመት የአርበኝነት ትግል መመከት ችለዋል። ከዚያ በኋላ በሩቅ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ድጋፍ በሶማሊያ የሲአድ
ባሬ መንግስት የፈጸመውን ወረራም ይህንኑ ሰንደቃላማ አንገበው ነበር የቀለበሱት። የቅርብ ግዜ ታሪካችን አካል የሆነው በኤርትራ
መንግስት የተፈጸመውን ወረራ ስንመክትም አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት ያለውን ሰንደቃላማ አንግበን ነበር። ኢትዮጵያውያን ከጠላት
ነጻ የሆነ መሬታቸው ላይ ይህን ሰንደቅ ዓላማ ያውለበልባሉ። በመሆኑም ሰንደቃላማው ለኢትዮጵያውያን የነጻነታቸው ጉልህ አርማ ነው።
ኢትዮጵያውያን ሰንደቅ ዓላማቸው ሲውለበለብ ሲመለከቱ ነጻነታቸውን ያስታውሳሉ።
እነዚህ ነጻነታቸውን ከባእድ ወረራ ጠብቀው
የኖሩ ኢትዮጵያውያን የተለያየ ብሄር፣ ብሄረሰብና ህዝብ ማንነት ያላቸው ናቸው። እነዚህ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የሚጋሩት
ታሪክ ያላቸውን ያህል የየራሳቸው ታሪክ፣ ባህል፣ ቋንቋ፣ . . . አላቸው። ሁሉም የኢትዮጵያ ብሄሮችና ብሄረሰቦች የሚኖሩበት መልከዓምድራዊ
ወሰን ዓላቸው። እነዚህ ኢትዮጵያ በምትባለው ምድር የሚኖሩ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ለነጻነት ያደረጉት ተጋድሎና ጠብቀውት
የቆዩት ነጻነታቸው በበጎነት ከሚነሱ አኩሪ የጋራ ታሪካቸው መሃከል ቀዳሚው ነው።
ይሁን እንጂ በዘውዳዊውና በወታደራዊው ደርግ
ስርአት በብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች መሃከል የነበረው ግንኙነት የተዛባ ነበር። የዘውዳዊውም ይሁን የወታደራዊው ደርግ የመንግስትተ
ስርአቶች የተለያዩ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የማንነትት መገለጫዎችን
በማቅለጥ በአንድ ብሄራዊ ማንነት የምትወከል ሃገር ለመፍጠር በተከተሉት ስትራቴጂ በብሄሮችና ብሄረሰቦች ላይ አስከፊ ጭቆና ጭነዋል።
በእነዚህ ስርአቶች የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ማንነታቸው በህግ እውቅና ተነፍጎት ቆይቷል። በወኪሎቻቸው አማካኝነት
ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር፣ በቋንቋቸው የመንግስት አገልግሎት የማግኘት፣ ልጆቻቸውን በቋንቋቸው የማስተማር፣ ባህላቸውን የማጎለበትና
የማስተዋወቅ፣ ታሪካቸውን የመንከባከብ ወዘተ መብቶቻቸውን በህግ ተነፍገው ቆይተዋል።
ታዲያ ይህን ጭቆና በጸጋ አልተቀበሉም። በጀመሪያ
ባልተደራጀና በተበታታነ የአርሶ አደር አመጽ በአካባቢያቸው ያገኟቸውን ሹማምንት በመቃወም ሲታገሉ ቆይተዋል። በኋላ ከመሃከላቸው
በተፈጠሩ ልሂቃን የተጫነባቸውን ጭቆና ምንጭ የሚተነትን የተደራጀ የትጥቅ ትግል ወደማድረግ ተሸጋግረዋል። በዚህ ለዓመታት በተካሄደና
መስዋዕትነት በጠየቀ መራራ የነጻነት ትግል የመጨረሻውን ጨቋኝ አሃዳዊ ስርአት ከሃያ አምስት ዓመታት በፊት ለመገርሰስ በቅተዋል።
የኢትዮጵያ በሄሮች፣ ብሄረሰቦች ባካሄዱት የነጻነት
ትግል የወታደራዊውን ደርግ ስርአት እንዳስወገዱ ሁለት ቀጣይ አማራጮች ከፊታቸው ተደቀኑ። አንደኛው የየራሳቸውን ነጻ መንግስት በመመስረት
ኢትዮጵያ ትባል የነበረችውን ሃገር መበታተን ሲሆን፣ ሌላኛው አማራጭ አብረው በኖሩበት የአንድ ክፍለ ዘመን እድሜ ያፈሩት በጎ የጋራ
ታሪክ ላይ በመመስረት፣ የቀደሙት ስርአቶች ጭነውባቸው የነበረውን አስከፊ ጭቆና በማስወገድ በፍቃዳቸው፣ በመከባበርና በእኩልነት
ላይ የተመሰረተ የህዝቦች አንድነት ያላት አዲስ ኢትዮጵየን መመስረት ነበር። የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ከእነዚህ
ሁለት አማራጮች ሁለተኛውን መረጡ፤ ያለምንም ጣልቃ ገብነት በተወካዮቻቸው አማካኝነት በአንድ አዳራሽ ታድመው መክረውና ዘክረው ነው
እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት። በዚህ ውሳኔ መሰረት በእኩልነት የሚኖሩበትን መንግስት የሚመሰርት የሽግግር መንግስት አዋቀሩ። ሁሉም
የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች፣ እንዲሁም አመለካከቶች የተወከሉበት የሽግግር መንግስት በፍቃዳቸው የሚመሰርቱት መንግስት የቃል
ኪዳን ሰነድ የሆነውን ህገመንግስት አዘጋጁ፤ የኢፌዴሪን ህገመንግስት።
ታዲያ የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች
በመሃከላቸው የነበረውን የተዛባ ግንኙነት ሽረው ሁሉም የሉዓላዊ ስልጣን ባለቤት የሚሆኑባትን፣ በፌደራላዊ ስርአት ራሳቸውን በራሳቸው
እያስተዳደሩ፤ በመከባበርና በእኩልነት፣ የወሰን ሳይሆን በፍቃድ ላይ የተመሰረተ የህዝቦች አንድነት ያላትን ኢትዮጵያ ለመመስረት
በህገመንግስት የታሰረ ቃል ሲግባቡ፣ በዚህ የቃል ኪዳን ሰነዳቸው ላይ አዲስ የመሰረቱት ግንኙነት የሚወከልበት ሰንደቅ ዓላማ እንደሚያስፈልጋቸው
ደንግገዋል። ይህ ሰንደቅ ዓላማ በመስዋዕትነት ነጻነታቸውን ጠብቀው የኖሩበትን አኩሪ የጋራ ታሪክ መሰረት በማድረግ ቀድሞ የነበረባቸው
ጭቆና ተሽሮ በእኩልነት መኖር የጀመሩበትን አዲስ ግንኙነት የሚያንጸባርቅ እንዲሆን ነበር የተስማሙት።
በዚህ መሰረት የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና
ህዝቦች የቃል ኪዳን ሰነድደ በሆነው የኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀጽ 3 የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በሚል ርዕስ ስር፤
·
የኢትዮጵያ ሰንደቅ
ዓላማ ከላይ አረንጓዴ፣ ከመሃል ቢጫ፣ ከታች ቀይ ሆኖ በመሃሉ ዓርማ የኖረዋል። ሶስቱም ቀለማት እኩል ሆነው አግድም ይቀመጣሉ።
·
ከሰንደቃላማው
ላይ የሚቀመጠው ዓርማ የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች፣ ህዝቦችና ሃይማኖቶች በእኩልነትና በአንድነት ለመኖር ያላቸውን ተሰፋ የሚያንጸባርቅ
ነው።
የሚል
ድንጋጌ ሰፍሯል።
ይህ የአንድ ፓርቲ ወይም የጥቂት ፓርቲዎች
ወሳኔ አይደለም። የሁሉም የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ተወካዮች መክረውና ዘክረው የተስማሙበት በኋላም ለእያንዳንዱ
ለአካለ መጠን የደረሱ የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች አባላትን ይሁንታ አግኝቶ በወኪሎቻቻው አማካኝነት የጸደቀ ነው።
በዚህ መሰረት በህገመንግስቱ ላይ የተቀመጠውን
መንፈስ የሚወክል ዓርማ ለማዘጋጀት ችሎታ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዲወዳደሩ በይፋ ጥያቄ ቀረበ። በርካታ ኢትዮጵያውያን ያለምንም
ገደብ በዚህ የሰንደቅ ዓላማ አርማ የማዘጋጀት ውድድር ላይ ተካፍለዋል። በተወዳዳሪዎች ከቀረቡት በርካታ ዓርማዎች መሃከል በ1993
ዓ/ም በወረሃ ጥቅምት በሞት የተለየን ታዋቂው አርቲስት መስፍን ወልደማርያም የቀረበው ዓርማ አሸናፊ ሆኖ ተመረጠ። በሰንደቅ ዓላማው ላይ ያረፈው ዓርማ በዚሀ አኳኋን የተዘጋጀ ነው። ይህ በየትኛውም
ሃገር ያለና ተገቢ አሰራር ነው።
በሰንደቅ ዓላማው ላይ ያረፈው ዓርማ ክብ በሆነ
ሰማያዊ መደብ ላይ ከየአቅጣጫው መጥተው በመገናኘት ኮከብ የሚሰሩ ቢጫ ቀጥታና እኩል መስመሮች አሉት። ኮከብ ከሰሩት እኩል መስመሮች
መተላላፊያዎች ላይ ቢጫ ጨረሮች ይፈነጥቃሉ።
የዓርማው ትረጓሜም የሚከተለው ነው። ክብ የሆነው
ሰማያዊ መደብ ሰላምን ያመለክታል። ቀጥታ እኩል የሆኑት መስመሮች፤ የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች እንዲሁም የሃይማኖቶችን እኩልነት
ያመለክታሉ። ቀጥታና እኩል ከሆኑት መስመሮች የተዋቀረው ኮከብ፤ የኢትዮጵያ የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በመፈቃቀድ የመረቱትን
አንድነት ያመለክታል። ቢጫው ጨረር በመፈቃቀድ አንድነት ለመሰረቱት ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የፈነጠቀውን ብሩህ ተስፋ ያመለክታል።
እናም ከቅርብ ግዜ ወዲህ የምንመለከተው ባለዓርማወን የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ እውቅና መንፈግና ማዋረድ ለኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና
ህዝቦች ዕውቅና ከመንፈግና ከማዋረድ የተለየ ድርጊት አይደለም።
ያም ሆነ ይህ አርማው መመረጡን ተከተሉ የሰንደቃላማ
አርማ አዋጅ ጸደቀ፤ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት። የመጀመሪያው የአርማ
አዋጅ በ1988 ዓ/ም የጸደቀ ሲሆን ከአንድ ዓመተ በኋላ በ1989 ዓ/ም በአዋጅ ቁጥር 48/1989 ማሻሻያ ተደርጎበታል። ይህ
ማሻሻያ የአርማውን መሰረታዊ ይዘት ሳይለቅ አቀማመጡ ላይ ያተኮረ ነበር። በዚህ መሰረት ዓርማው በሰንደቅ ዓላማው መሃከል ላይ የሚሰፍረው የክብ ዙሪያ የአረንጓዴውንና የቀዩን ቀለማት ቁመት አጋማሽ አካሎ
ይሆናል ተብሎ ተደንግጓል።
ፕሬዝዳንት ሙላቱ በእንኳን ለሰንደቅ ዓላማ ቀን አደረሳችሁ መልዕክታቸው ያስተላለፉት ሰንደቅ ዓላማችን ከብዝሃነታችን
አንፃር
በመፈቃቀድ
ላይ
የተመሰረተው የዲሞክራሲያዊ
አንድነታችን
መገለጫ
ምልክታችን
ነው።
ባጠቃላይ
የኢትዮጵያ
ሰንደቅ
አላማ
የመላው
የሀገራችን
ብሔሮች፣
ብሔረሰቦችና
ሕዝቦች
ዘመን
ተሻጋሪ
ትግልና
ድል
የዘላቂ
ሰላም
የብሔራዊ
እኩልነት፣
የዲሞክራሲያዊ
እኩልነትና
የውጤቱም
አርማ
ነው የሚል መልዕክት በተለይ ከአርማው ፍቺ ጋር ተያይዞ ያለውን የሰንደቃላማ ምንነት
በግልጽ ያመለክታል።
እንግዲህ በኢፌዴሪ ህገመንግስት የኢትዮጵያ
ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው እያስተዳደሩ በእኩልነት በኖሩባቸው የባለፉ ሁለት አስርት ዓመታት ከዚያ ቀደም
በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ሲካሄዱ የቆዩ የህዝብ ድጋፍ ያላቸው የነጻነት የትጥቅ ትግሎችን በማስቀረት በሃገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን
አድርጓል። ይህ ሰላም የእድገትና የልማት መሰረት ሆኗል። ባለፉት አንድ ተኩል አስርት ዓመታት የተመዘገበው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ
ልማት የዚህ ሰላም ውጤት ነው። ይህ እድገትና ልማት፣ ሃገሪቱ ሰላም ካላት የበለጸጉ ሃገራት የደረሱበት ደረጃ መደረስ እንደምትችል
ለኢትዮጵያውያን ሁሉ አሳውቋል።
በኢፌዴሪ ሰንደቅ ዓላማ ላይ የተወከለው የብሄሮች፣
ብሄረሰቦችና ህዝቦች እኩልነት ያረጋጋጠው ሰላም የእድገትና የልማታችን መሰረት ነው። እናም ፕሬዝዳንት ሙላቱ እንዳሉት፣ ሰንደቃላማችን
በራሳችን
ትጋትና
ጥረት
ዳግም
የስልጣኔ
ማማ
ላይ
ለመውጣት
የምናደርግው
ትግልና
የተገኘውን ወጤት የሚወክል አርማችን ነው።
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና
ህዝቦች የተወሰነውን የሃገሪቱን ሰንደቅ ዓላማ አለመቀበል በአዲሲቱ ኢትዮጵያ የተረጋገጠውንና ሰንደቃላማው የሚያወክለውን የብሄሮች፣
ብሄረሰቦችና ህዝቦች እኩልነትና በእኩልነት ላይ የተመሰረተ አንድነት አለመቀበል ነው። ይህን አለመቀበል እኩልነቱና በእኩልነት ላይ
የተመሰረተ አንድነት ያረጋገጠውን ሰላምና ሰላሙ ያረጋገጠውን ልማት እንዲሁም በቀጣይነት የሚገኘው የብልዕግና ተስፋ ከመግፋት አይለይም።
ሰንደቅ ዓላማችን የነጻነታችን፣ የእኩልነታችን እና የብልጽግና ተስፋችን ዓርማ ነው።
No comments:
Post a Comment