Sunday, 1 January 2017

የእምነት ነፃነት ከህገ መንግስቱ አኳያ ሲቃኝ




                                                         ቶሎሳ ኡርጌሳ
የኢፌዴሪ ህገ መንግስት ሶስት አራተኛው የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን የሚያረጋግጡ ድንጋጌዎች ስብስብ ነው፡፡ በእነዚህ ድንጋጌዎች ውስጥ የግልና የቡድን መብቶች ተካትተዋል፡፡ በተለይም በህገ መንግስቱ ሰፍረው የሚገኙት ሶስቱ መርሆዎች የእምነት ነፃነት፣ የሃይማኖት እኩልነትና የመንግስትና የሃይማኖት መለያየት ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓቱ ማደግና ማበብ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ እንደሚገኙ በእርግጠኝነት መናገር የሚቻል ይመስለኛል፡፡
በሀገራችን ታሪክ ውስጥ ረጅም ዓመታትን ያሰቆጠረው ይህ የእምነት ነፃነትንና የሃይማኖት እኩልነትን የማስፈን ትግል፤ በእኩልነትና በመቻቻል የመኖርን ራዕይ ሰንቆ ትክክለኛው አቅጣጫን በመከተል ለፍሬ ከበቃም 22 ዓመታትን ተሻግሯል፡፡ መላው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ሃይማኖታቸውና እምነታቸው ተከብሮ በእኩልነትና በመቻቻል መርህ የተመሰረተች አዲሲቷን ኢትዮጵያን ዕውን ማድረግ በመቻላቸው መብቶቹ ዕውን መሆን ችለዋል፡፡ በመሆኑም ህዝቦች ከዘመናት የሃይማኖትና የእምነት ጭቆና ተላቀው ሃይማኖትና መንግስት የተለያዩበትን፣ መንግስታዊ ሃይማኖት የሌለባትን ብሎም የማይታሰብባትን ሀገርን እየገነቡ ነው፡፡
የቃል ኪዳናቸው ሰነድ በሆነው የኢፈዴሪ ህገ- መንግስት የሃይማኖት እኩልነትንና የእምነት ነፃነትን በማስፈርና በተግባር በመተርጎምም የሃይማኖት እኩልነትን ያስከበረ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መገንባት በመቻላቸው፤ የሃይማኖት ብዝሃነት የምታስተናግድ ሀገርን ፈጥረዋል፡፡
ይህ ሁኔታ የዛሬዋ ኢትዮጵያ ከትናንትዋ የተሻለችና የሃይማኖት ብዝሃነት የሚስተናገድባት ሀገር፣ ማንኛውም ዜጋ የመረጠውን ሃይማኖትና እምነት የመያዝና የመቀበል፣ ሃይማኖቱንና እምነቱንም ያለአንዳች ቅድሚያ ሁኔታ የማምለክ ብሎም የመከተልና የማስፋፋት መብቱን እንዲያጣጥም አድርጓል። በሃይማኖቱና በእምነቱ ጣልቃ የሚገባ የትኛውንም አካል የማስቆም መብቱን መጠቀም የመቻሉ ጉዳይንም በተግባር እያረጋገጠ ነው፡፡ እናም የሀገራችን ህዝቦች የሃይማኖት እኩልነት አጀንዳ በማይሆንበት ዘመን ላይ ይገኛሉ፡፡ የሀገራችን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ባህል ግንባታ ሂደት የግልና የቡድን መብቶችን የሚያስከብር በመሆኑ የሃይማኖት ጉዳይ በዚሁ አግባብ ምላሽ ማግኘት ችሏል፡፡ እናም  በህገ-መንግስቱ ስፍረው የሚገኙትና ቀደም ሲል የጠቀስኳቸው 3ቱ መርሆዎች (የእምነት ነፃነት፣ የሃይማኖት እኩልነትና የመንግስትና የሃይማኖት መለያየት) ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓቱ ማደግና ማበብ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ እንደሚገኙ በእርግጠኝነት መናገር የሚቻል ይመስለኛል፡፡
ዛሬ በሀገራችን መንግስታዊ ሃይማኖት የለም። መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ፣ ሃይማኖትም በመንግስት ጉዳይ ጣልቃ መግባት የሚታሰብ አይደለም፡፡ ማንኛውም ግለሰብ የመረጠውን ሃይማኖትና እምነት የመያዝና የመቀበል፣ ሃይማኖቱንና እምነቱንም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የማምለክ፣ የመከተል፣ የማስፋፋት መብቱም በይፋ ተረጋግጧል፡፡
በዚህም ሃይማኖትና መንግስት የተለያዩበት፣ የመንግስታዊ ሃይማኖት አመለካከት የከሰመበት ሁኔታን ዜጎች የቃል ኪዳናቸው ሰነድ በሆነው ህገ - መንግስታቸው አማካኝነት የሃይማኖት እኩልነትን ያስከበረ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መገንባት በመቻላቸው፤ የሃይማኖት ብዝሃነትን ማስተናገድ የምትችል አዲሲቷ ኢትዮጵያን ማየት ተችሏል፡፡  እናም ሀገራችን በእኩልነትና በመቻቻል ባህል የሃይማኖት ብዝሃነት የሚስተናገድባት ሀገር በመሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ አድናቆትን ማትረፍ ችላለች፡፡
ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ማንኛውም ዜጋ የመሰለውን እምነት የመከተል መብት ያለባት እንዲሁም የሃይማኖቶች እኩልነት የተረጋገጠባት ሀገር መሆኗና ለተግባራዊነትም በኢፌዴሪ ህገ- መንግስት በተለያዩ አንቀፆች ተደንግጎ ወደ ተግባር በመሸጋገር ለሀገራዊው ሠላም፣ ልማት፣ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታው መፋጠን ከፍተኛ ድርሻ እያበረከተ ይገኛል፡፡ ይህም አሁን ሀገራችን ባለችበት ተጨባጭ ሁኔታ ሃይማኖት የመቻቻልና የመከባበር እንጂ የግጭት መንስኤ ሊሆን እንደማይችል የሚያስገነዝበን ነው።
እርግጥም የሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ሃይማኖት የግጭት መንስዔ ሊሆን እንደማይችል ከማንም የሚሰወር አይመስለኝም፡፡ የሃይማኖት እኩልነት በተረጋገጠባት ኢትዮጵያ ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የሚካሄድ ማናቸውም እንቅስቃሴ ቦታ የለውም። ሊኖረውም አይችልም። ‘ለምን?’ ካሉ ህዝቦች ከዘመናት የሃይማኖትና የእምነት ጭቆና ተላቀው ሃይማኖትና መንግስት የተለያዩበትን፣ መንግስታዊ ሃይማኖት የሌለባትን ብሎም የማይታሰብባትን ሀገርን በመገንባት ላይ በመሆናቸው ነው፡፡
የሀገራችን ህዝቦች የቃል ኪዳናቸው ሰነድ በሆነው የኢፈዴሪ ህገ መንግስት የሃይማኖት እኩልነትንና የእምነት ነፃነትን በማስፈርና በተግባር በመተርጎምም የሃይማኖት እኩልነትን ያስከበረ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መገንባት በመቻላቸው፤ የሃይማኖት ብዝሃነት የምታስተናግድ ሀገርን ፈጥረዋል፡፡
በመሆኑም ዛሬ ከትናንቱ የተለየ የሃይማኖት ብዝሃነት በሚስተናገድባት ኢትዮጵያ ማንኛውም ዜጋ የመረጠውን ሃይማኖትና እምነት የመያዝና የመቀበል፣ ሃይማኖቱንና እምነቱንም ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ የማምለክ ብሎም የመከተልና የማስፋፋት መብቱን ማጣጣም ችሏል፡፡ በዚህም የሀገራችን ህዝቦች የሃይማኖት እኩልነት አጀንዳ በማይሆንበት ዘመን ላይ ይገኛሉ፡፡
ያም ሆኖ ግን ይህን ያህል የጎላ ባይሆንም ከዚህ የሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር በሚፃረር መልኩ የሃይማኖት አክራሪነትን ለማራመድ የተካሄደው ጥረት እንደነበር አይዘነጋም፡፡ በሁሉም የእምነት ተከታዮች አማካኝነት በእንጭጩ እንዲቀር ተደረገ እንጂ። በእኔ እምነት ሀገራችን ውስጥ ከአክራሪነት ይልቅ መቻቻልና መከባባር ከፍ ያለው ለዘመናት የዘለቀው ሃይማኖታዊ ጭቆናና በደልን ጠንቅቆ የሚገነዘበው መላው ኢትዮጵያዊ፤ ትናንትን የሚጠላ እንጂ የሚያማትር አለመሆኑን እንዲሁም ለዘመናት ባካሄደው ትግልና ባስመዘገበው ውጤትም የሚረካና ሁሌም ለሰላም ቀናዒ እንጂ የሚማረር ባለመሆኑ ነው፡፡
እንደሚታወቀው የሀገራችንን ዴሞክራሲያዊና ልማታዊ ስርዓት ለየት የሚያደርገው አንድ ወሳኝ ነጥብ ቢኖር፤ በህገ -መንግስቱ ላይ የሰፈሩ መሰረታዊ መብቶችና ነጻነቶች ይበልጥ ተግባራዊ እንዲሆኑ ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ መሆኑ ነው፡፡ በህገ -መንግስቱ ውስጥ ህጋዊ ከላላ ከተሰጣቸው ጉዳዮች መካከል የእምነት ነጻነትና የሃይማኖት እኩልነት በመሆናቸው፤ እነዚህን መብቶች ሳይሸራረፉ ገቢራዊ ለማድረግ መንግስት ያልተቆጠበ ጥረት አድርጓል፡፡
የማንኛውም እምነት ተከታይ ያለማንም አስገዳጅነት በመረጠው ሃይማኖት እንዲመራ፣ ሃይማኖታዊ ግዴታውን ያለማንም ጣልቃ ገብነት እንዲፈጸም እንዲሁም መንግስትና ሃይማኖት ብሎም ሃይማኖትና የትምህርት ተቋማት ተነጣጥለው ተግባራቸውን እንዲከውኑ በማድረግ ረገድ ህገ መንግስታዊ ድንጋጌው ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ በተግባር እንዲተረጎም አድርጓል፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ ባለፉት 22 ህገ መንግስታዊ ዓመታት ሁሉም ሃይማኖቶች አምልኮአቸውን የሚፈጽሙባቸው የእምነት ቦታዎች ከመስፋፋታቸው በተጨማሪ፤ የመቻቻል ባህላችን ማሳያ የሆኑት የሃይማኖት በዓላት ክብደት በሚሰጣቸው ሁኔታ እንዲከበሩ አስፈላጊ የሚባሉ ጉዳዮች ተመቻችተዋል፡፡ እነዚህ የሃይማኖትት እኩልነትን በተግባር ለመተርጎም የተከናወኑ ሃቆች ሀገራችን ውስጥ በማንኛውም እምነት ተከታይ ዘንድ ነባሩን የመቻቻል ባህል ይበልጥ ያሰፉና ያረጋገጡ ናቸው፡፡
በመሆኑም የእያንዳንዱ እምነት ተከታይ ለዘመናት የዘለቀውን መቻቻላችንን ለማቆርፈድ የተሰለፉ ፖለቲከኞችን ከውስጡ ለይቶ በማጋለጥና ሴራቸውን ይፋ በማድረግ ለሰላሙ መትጋት ይኖርበታል፡፡ ለነገሩ እኔን ጨምሮ የማንኛውም እምነት አስተምህሮት ተከታታይ ምዕመን የሃይማኖት ልዩነት መኖሩ በማይታወቅበት ሁኔታ ውስጥ ተቻችሎ የመኖር ትውፊቱን ለጥቂት ፅንፈኞች አሳልፎ ይሰጣል ማለት የዋህነት ነው፡፡ ምክንያቱም በአሁኑ ወቅት የተፈጠረውንና መቻቻልና በመፈቃቀሩ ያተረፋቸው በሰላም ወጥቶ የመግባት እንዲሁም በየደረጃው ከሚገኝ ልማታዊ ዕድገት ተጠቃሚ የመሆን… ወዘተ. ትሩፋቶችን ማጣት የሚፈልግ ዜጋ ሊኖር ስለማይችል ነው፡፡
በህዝቡ የጋራ ፍላጎት ዕውን የሆነው የኢፌዴሪ ህገ መንግስት መሰረቱ ዴሞክራሲ ነው፡፡ የህዝቡም በዴሞክራሲ ውስጥ የመኖር ፍላጎት ሁነኛ መገለጫ ነው። እናም በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ውስጥ የሚገኝ ህብረተሰብ ፀረ ዴሞክራሲያዊነት ሊያማልለው አይችልም፡፡ በህገ መንግስቱ ውስጥ የሰፈሩትን የእምነት ነፃነትና የሃይማኖት እኩልነትን ያውቃል—ታግሎ ያመጣቸው መብቶች ናቸውና፡፡ እናም ህገ መንግስቱ ለሃይማኖት የሰጠውን መብቶች አውቆ ህገ መንግሰቱ የመብቶቹ ሁሉ ምንጭ መሆኑን በመገንዘብ ተግባራቶቹን ሁሉ ከዚህ አኳያ መቃኘት የሚኖርበት ይመስለኛል፡፡ 


No comments:

Post a Comment