በደቡብ ሱዳን የተቀሰቀሰውን ግጭት እንዲቆም የተመድ ጥሪ አቀረበ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች በአዲስ መልክ የተቀሰቀሰውን ግጭት እንዲያቆሙ ጥሪ አቀረበ፡፡ምክር ቤቱ የተቀሰቀሰውን ግጭት እና በድርጅቱ ንብረቶች ላይ የደረሰውን ጥቃት አውግዟል፡፡
ከአርብ ጀምሮ በተቀሰቀሰው ግጭት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር ደጋፊዎቸ በፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ደጋፊዎች ጥቃት እንደደረሰባቸው አስታውቀዋል፡፡
በጁባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ ሻንታል ፔርሳውድ እንዳሉት ግጭቱን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎች በድርጅቱ ውስጥ ተጠልለዋል፡፡
ሁለቱ ወገኖቸ ለደረሱት የሠላም ስምምነት መከበር ሃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የሀገሪቱ ኢንፎርሜሽን ሚንስትር ማይክል ማኩይ እንዳሉት በጁባ ያለው ሁኔታ በቁጥጥር ስር በመዋሉ ነዋሪዎች ወደ ቤታቸው መመለስ ጀምረዋል፡፡
No comments:
Post a Comment