Wednesday, 13 July 2016

ገዝግዞ ገዳዩ



 

ስሜነህ


የማህፀን በር ካንሰርን ከአገር ብሎም ከአፍሪካ ለማጥፋት ብዙ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ። “የማህፀን በር፣ የጡት እና የፕሮስቴት ካንሰርን ከአፍሪካ እናጥፋ” ጉባኤ ከፊታችን ሐምሌ 17 እስከ 20 ቀን 2008 ዓ.ም “የአስር ዓመታት ስኬቶቻችንና ትሩፋቶቻችን” በሚል መሪ ሀሳብ ይካሄዳል። ይህንኑ ጉባኤ መሰረት በማድረግም ስለማህጸን ካንሰር አንዳንድ መረጃዎች መለዋወጥ የዘመቻው አንድ አካል ነውና ወጋችንም እርሱው ይሆናል።
 
የማህፀን በር ካንሰር መንስኤው ሂማንፓፒለማ የተባለ ቫይረስ ነው። በዚህ ቫይረስ ምክንያት የተከሰተ ኢንፌክሽን በሰውነት ውስጥ ለረጅም ጊዜ በሚቆይበት ጊዜ የማህፀን በር ካንሰር እንደሚከሰት በዘርፉ ምርምር ያደረጉ ልሂቃን ይገልጻሉ። ይህ ቫይረስ በሰውነት ውስጥ ከገባ በኋላ የቅድመ ካንሰር ምልክቶች ማሳየት የሚጀምረው በአማካይ ከ10 እስከ 15 ዓመታት ባሉት ጊዜያት ውስጥ ነው። ይህ ማለት ደግሞ አንዲት ሴት በ15 ዓመቷ የግብረ-ስጋ ግንኙነት ማድረግ ብትጀምር እና ቫይረሱ ሰውነቷ ውስጥ ቢገባ እንኳን እነዚህን የቅድመ ካንሰር ምልክቶች እስከ 30 እና 35 ዓመቷ ድረስ ላታሳይ ትችላለች ማለት ስለሚሆን ጉዳቱን ያከብደዋል። እነዚህ የቅድመ ካንሰር ምልክቶች በማህፀን በር ሊይ ከተስተዋሉ በኋላም ወደ ካንሰርነት ለመለወጥ ከ10 እስከ 15 ዓመታት የሚፈጅበት መሆኑን ነው ጠበብቱ በምርምራቸው ያረጋገጡት። ከዚህ እድሜ ጀምሮ ግን ወይም ወደ ካንሰር ከተለወጠ በኋሏ ቫይረሱ በማህፀን የውስጥ ክፍልች ላይ ለውጥ ያመጣል። የማህፀንን ግድግዳ በመበከል ቁስለት ይፈጥራል።እንደጠበብቱ መረጃ ቁስለቱ ከማህፀን ግድግዳ አልፎ በደም ውስጥ በመግባት መላ ሰውነትን ያዳርሳል።

የማህፀን በር ካንሰር ዋነኛ ቫይረስ በግብረስጋ ግንኙነት የሚተላለፍ ሲሆን፣ ሰባ ከመቶ በላይ የሚሆኑት ታማሚዎችም የቫይረሱ ተሸካሚዎች ናቸው። በተጨማሪም በግልፅ የማይታወቁ መንስኤዎች እንደሚኖሩም ባለሙያዎቹ ይገልጻሉ። ለማህፀን በር ካንሰር አጋላጭ የሆኑ በርካታ ነገሮችም አሉ ከእነዚህም የመጀመሪያው፤ ሴቷ የመጀመሪያ የግብረ ስጋ ግንኙነት የጀመረችበት የእድሜ ክልል እንደሆነ ያወሳሉ። አንዲት ሴት የግብረ ስጋ ግንኙነት የጀመረችው በአስራዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ከሆነ ለማህፀን በር ካንሰር የመጋለጥ እድሏ ከፍተኛ ይሆናል። ለአባላዘር በሽታዎች አልያም ለኤች አይ ቪ/ ኤዴስ የተጋለጠች ከሆነች እንዲሁም ከአንድ በላይ የወሲብ ጓደኛ ካላት አሊያም ከአንድ በላይ የወሲብ ጓደኛ ያለው ጓደኛ ካላት ለዚሁ የካንሰር አይነት የመጋለጥ እድሏ ይጨምራል። የሰውነት በሽታን የመከላከል አቅም የሚቀንሱ መድሃኒቶችን የሚወስዱ ሰዎችም ለማህፀን በር ካንሰር የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው ሲሉ ባለሙያዎቹ ያስጠነቅቃሉ።

ማህፀን በር ካንሰር አጋላጭ የሆኑት ነገሮች በአብዛኛው ከዝቅተኛ ኢኮኖሚ እና የአኗኗር ዘይቤ ጋር የተያያዙ ስለመሆናቸውም ልሂቃኑ ሳይጠቅሱ አያልፉም። በጋ እድሜ ጋብቻ በመመስረት ግብረ-ስጋ ግንኙነት መጀመር፣ ልጆችን በላይ በላዩ መውዚህ በሽታ አጋላጭ ከሚባል የአኗኗር ዘይቤ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ናቸው። የማህፀን በር ካንሰር ከበፀጉት አገራት ይልቅ በማግ ላይ ባሉት አገራት ላይ ስርጭቱ ከፍተኛ የሚሆነውም ስለዚህ ነው። ከዚህ ውጪ ግሞ ሲጋራ የሚያጨሱ ሴቶች ከሌሎቹ በበማህፀን በር ካንሰር ያላቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ ነው። የማህፀን በር ካንሰር ሊካለከሉት የሚቻል በሽታ ሆኖ ሳ መከላከል የማይቻውም ከላይ ከተመለከተው ዝቅተኛ የአኗኗር ሁኔታ ጋር በተያያዘ ነው። ሴቶች ጤናቸው ቅድሚያ በመስጠት በየጊዜው የቅድመ ካንሰር ምርመራ ስማያርጉ ዚህ በሽታ የመጋጥ እድላቸው ይጨምራል።

ሌላውና ከዚሁ ዝቅተኛ ኢኮኖሚ ጋር የሚያያዘው ጉዳይ፤ የማህፀን በር ህክምና በሚፈገው መጠን አመስፋፋቱ ነው። ኅብረተሰቡ ስበሽታው ግንዛቤ ኖሮት መታከም ቢፈልግ እንኳን የህክምና አገልግሎቱ ሰፊ እና በሁሉም ቦታ የሚሰጥ ባመሆኑ በሽታውን መከላከል ከባድ ያደርገዋል

የማህፀን በር ካንሰር በሽታው ሲጀመር ምንም አይነት ምልክት አያሳይም። ቫይረሱ በሰውነት ውስጥ ገብቶ ምልክቶች ማሳየት በርካታ ዓመታት ስሚፈጅበትም ምልክቶቹን በቶሎ መገንዘብ አይቻልም። ነገር ግን ህክምና ሳያገኝ ሲቆይና ቫይረሱ በሰውነት ውስጥ የሚኖረው ስርጭት እየበዛና እየሰፋ ሲሄድ ምልክቶቹ መታየት ይጀምራሉ። ምልክቶቹ መታየት የሚጀምሩትም  በሽታው ከቅድመ ካንሰርነት ወ ካንሰርነት በሚሸጋገርበት ወቅት ነው። ምልክቶቹንም ባለሙያዎቹ የቅድመ ካንሰር እና የካንሰር ብ  ይከፍሏቸዋል። ነገር ግን፤ በቅድመ የማህፀን በር ካንሰር ወቅት ብዙም ምልክቶች አይታዩም። በአጠቃላይ ስንመከተው ግን የማህፀን በር ካንሰር መኖሩን ከሚጠቁሙት ምልክቶች መካከል  ህመም አልባ የሆነ ም ከማህፀን መውጣት የመጀመሪያው ነው። ይህ ክስተት የሚከሰተውም መበኛ ባሆኑ ጊዜያት ነው። እነዚህ ጊዜያትም ከመበኛ የወር አበባ ጊዜ ውጪ፣ ከግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ፣ ከማረጥ በኋላ፣ ብልትን ከታጠቡ በኋላ ሊሆን ይችላል። ከዚህ በተጨማሪም የሚታየው ምልክት መጥፎ ጠረን ያው እና ውሃማ ቀም ያው የማህፀን ፈሳሽ መውጣት፣ የን፣ የወገብ እና የእግር ህመም ስሜት መሰማት፣ የሽንት ቧንቧ ወይም የፊንጢጣ መድማት፣ የእግር እብጠት፣ እንዲሁም የሽንት ወይም የሰገራ ማምጥ (fistula) ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

የማህፀን በር ካንሰርን አስቀድሞ በሚረግ ጥንቃቄ እና ምርመራ መከላከል የሚቻል መሆኑንም ከላይ ስለተመለከቱት መንስኤዎችና ምልክቶች አስረጅ የሆኑን ምርምሮች ይገልጻሉ። በሽታው መንስኤ የሆኑትን ነገሮች በማስወገድ በሽታው ያውን ተጋላጭነት መቀነስ ይቻላል። ባልታወቀ ምክንያት የሚመጣውን መከላከል ግሞ ቅድመ ካንሰር ምርመራ በማድረግ ሁኔታውን ማወቅ ይቻላል። ዋና ዋና የመከላከያ መንገዶቹም፤ ሂውማን ፓፒልማ ቫይረስ የሚተላለፈው በግብረ ስጋ ግንኙነት ስሆነ ዚህ ቫይረስ በማያጋልጥ መልኩ ጥንቃቄ የተሞላበት የወሲብ ግንኙነት ማድረግ ያስፈልጋል ። ነገር ግን ይሄንን ቫይረስ ኮንም በመጠቀም መከላከል የማይቻል እንደሆነ ጠበብቱ ያሰምራሉ። ሁተኛው ሊወሰድ የሚገባው ጥንቃቄ ግሞ፤ ሲጋራ የሚያጨሱ ሴቶች ሲጋራ ማጨሳቸውን ወዲያው ማቆም ይኖርባቸዋል። ዋናውና የበሽታው መከላከያ ግን ቅድመ ካንሰር ምርመራ በተገቢው ጊዜ ማድረግ ነው። ለቅድመ ካንሰር ምርመራ የሚረጉት ምርመራዎች ሁት አይነት ናቸው። የመጀመሪያው ቪ አይ ኤ የሚባው ምርመራ ነው። ይህ ምርመራ በሴቷ ማህፀን ላይ ኬሚካል በመቀባት እና አምስት ቂቃ ያህል በማቆየት የሚሰራ ምርመራ ነው። በዚህ የቆይታ ጊዜ ውስጥ በሚታየው ውጥም ካንሰር መኖር አመኖሩን ማረጋገጥ ይቻላል። ይኸኛው ምርመራ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚሰራና ውጤቱም በዓይን በማየት ብቻ ለማወቅ የሚቻል ነው። በዚህ የምርመራ ዘዴ የተመረመሩ ሴቶች በየሦስት ዓመቱ ተመሳሳይ ምርመራ እንዲያደርጉ ይመከራል። ሁተኛው የቅድመ ካንሰር ምርመራ ፓፕ ስሚር የሚባው ዓይነት ነው። በዚህኛው የምርመራ ዘዴ ከማህፀን ላይ የፈሳሽ ናሙና በመውሰድ ምርመራ ይረጋል።ይህ የምርመራ ዓይነት ከበድ የሚል እና ረዘም ያ ጊዜም የሚወስድ ነው። ይሄንን አይነቱን ምርመራ ማድረግ የሚቻውም በተወሰኑ የህክምና ማዕከላት ነው። በዚህ ዓይነቱ መንገድ የተመረመረች ሴት የካንሰር ቫይረስ በሰውነቷ ውስጥ አመኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ በየአምስት ዓመቱ ምርመራ እንድታርግ ይመከራል።

የቅድመ ካንሰር ምርመራ በማድረግ የማህፀን በር ካንሰር ከመከሰቱ ከአስር ዓመት በፊት አስቀድሞ ማወቅ ይቻላል። የቅድመ ካንሰር መርመራ እድሜያቸው 21 ዓመት በላይ የሆኑ  የግብረስጋ ግንኙነት ለጀመሩ እና ከኤች አይ ቫይረስ ጋርሚኖሩ ሴቶች መሰጠት ይኖርበታል። ምርመራው በዚህ መልኩ በመቀጠል እድሜያቸው 65 ዓመት በላይ ሲሆን፣ አልያም ለተከታታይ ሦስት ምርመራዎች የተመዘገበው ውጤት ነፃ ከሆነ ምርመራውን ማቆም እንደሚቻል ተመራማሪዎቹ ይገልጻሉ። እናም ይህንን ገዳይ የሆነ በሽታ እንደዋዛ ማየት ተገቢ አይሆንም።

No comments:

Post a Comment