ይነበብ ይግለጡ
የወጣቶቻችን በስራ መስክ መሰማራት አምራችና ብቁ ሀገራዊ
ዜጋ ሁኖ መገኘት የሚጠበቅባቸውን ሀገራዊ ድርሻ በብቃት እንዲወጡ ያስችላቸዋል፡፡የአንድ ሀገር ትልቁ ሀብት ሀገር ተረካቢው
ወጣት ትውልድ ነው፡፡ወጣቱ ሰፊና እምቅ ጉልበት ያለው ሲሆን
እውቀትና ክሕሎት እየተላበሰ ሲሄድ የበለጠ ሀገርን የማገልገል አቅም ይገነባል፡፡ነገን የተሻለ ለማድረግ ዛሬ በሁሉም
መስክ ለመብቃት መዘጋጀትን ይጠይቃል፡፡
በየትኛውም የአለማችን ሀገሮች ታሪክ ሀገራዊ ለውጥንና
ግንባታን የሚያከናውነው ግዙፍ ራእዮችና ትልሞች ሕይወት እንዲዘሩ የሚያደርገው ሀገርን ከድሕነት በማውጣትና በማላቀቁ ሂደት
ቁልፉን ሚና የሚጫወተው ወጣቱ ነው፡፡ ወጣቱ ያልተነካ ጉልበት ገና ብዙ ሊሰራ የሚችል ኃይል ያለው የሕብረተሰብ ክፍል ነው፡፡ለውጥ
ፈላጊና የለውጥ ሠራዊትም ነው፡፡
ይህንን ትኩስ የሕብረተሰብ ክፍል ገንቢ በሆኑ ሀገራዊ
የልማትና የእድገት ሂደቶች ውስጥ በዋነኛነት ማሳተፍ ሀገርንም ሕዝብንም ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡በሀገራችን ወጣቱ የለውጥ ኃይል ሁኖ
ቆይቶአል፡፡አዲስ ስርአት ለማምጣት በተደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል ወስጥ በዋነኛነት ታላቅ መስዋእትነት ከፍሎአል፡፡በእውቀትና
በትምሕርት የተገነባ ወጣት ትውልድ ሀገር ተረካቢ ብቻ ሳይሆን ሀገርን ወደተሻለ ምእራፍ የሚያሸጋግር ያደገና የበለጸገ
ሕብረተሰብ ለመፍጠር ቁልፍ ሚና የሚጫወት ነው፡፡
በሀገራችን የወጣቱ ቁጥር በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ
70 በመቶ የሆነውን የሕብረተሰቡን ክፍል የሸፈነበት ሁኔታ ነው የተፈጠረው፡፡ይህን ኃይል ወደ ስራ ለማሰማራት ሰፊ ሀገራዊ
የኢኮኖሚ አቅምን ይጠይቃል፡፡መንግስት በዘንድሮው አመት ለወጣቶች ፈንድ የመደበው 10 ቢሊዮን ብር ወጣቶች ራሳቸውን ችለው
አቅማቸው በሚፈቅደው የስራ መስክ እንዲሰማሩ ውጤታማና ምርታማ እንዲሆኑ ከራሳቸውም አልፈው ስራ ፈጣሪ በመሆን ሌላውን የሕብረተሰብ
ክፍል እንዲጠቅሙ በማሰብ የተደረገ ነው፡፡
ይህ ገንዘብ መንግስት የወጣቱን ችግር ለመቅረፍ አስቦ የመደበው
የሕዝብ ገንዘብ ሲሆን ወጣቱ በስራው ውጤታማ ሆኖ መልሶ ብድሩን የሚከፍለው ነው፡፡ገንዘቡ የተሻለ የስራ ውጤት ለማምጣት
እንዲችል ውጤታማ በሆነ የስራ መስክ መዋል ያለበት ሲሆን ክልሎች ገንዘቡን ለወጣቶች በማከፋፍል ወደ ስራ ገብተዋል፡፡
በዚህ አመት ባለፉት
10 ወራት
ከ886
ሺህ
በላይ
ለሚሆኑ
ወጣቶች
ቋሚና
ጊዚያዊ
የሥራ
እድል
መፈጠሩን
የኦሮሚያ
ብሔራዊ ክልል በቅርቡ አስታውቆአል፡፡በኦሮሚያ
ክልል
ባለፉት
10 ወራት
በአጠቃላይ
987 ሺህ
የሚሆኑ
ሥራ
አጥ
ወጣቶች
በገጠርና
ከተማ
የሚገኙ
መሆናቸው ተረጋግጦ 886ሺህ 274 ለሚሆኑት
ቋሚና
ጊዚያዊ
የሥራ
እድል
ለመፍጠር
ተችሎአል፡፡
ባለፉት 10 ወራት
የኦሮሚያ
ክልልና
የፌደራል
መንግሥት
በመደቡት
የወጣቶች
የተንቀሳቃሽ
ፈንድ
አማካኝነት በክልሉ የሚገኙት ሥራ
አጥ ወጣቶች በማኒፋክቸሪንግ
፤በኮንስትራክሽን፤በአገልግሎት
ዘርፍ፤ንግድ፤በግብርና
በከብት
እርባታና
ማእድን
ዘርፎች እንዲሠማሩ
መደረጉን
በክልሉ
የሥራ
እድል
ፈጠራ
ምክትል
ዳይሬክተር
አቶ
ዳንኤል
ኢላኖ
ለመገናኛ ብዙሀን ገልጸዋል፡፡
ሥራአጥ ወጣቶች
ተደራጅተው
በተለያዩ
የሥራ
ዘርፎች
እንዲሠማሩ
ለማድረግ
ሰፊ ስልጠናዎች ተሰጥተዋል፡፡የብድርና የቴክኒክ
ሙያዊ ድጋፍ
ተደርጎላቸዋል፡፡በሥራ እድል
ፈጠራው
ተጠቃሚ
ከሆኑት
ውስጥ የዩኒቨርስቲና
የቴክኒክና
ሙያ
ተመራቂ
ወጣቶች
ይገኙበታል፡፡ለሥራ
እድል
ፈጠራው
1 ነጥብ
5 ቢሊዮን
ብር
ጥቅም
ላይ
የዋለ ሲሆን ከፍተኛ ውጤት እንደሚያስመዘግብ ይጠበቃል፡፡
በተለያዩ ዘርፎች
ተደራጅተው
ለተሠማሩት
ወጣቶች አይነታቸው
የተለያየ
የድጋፍ
ማእቀፎች ተዘርግተው በከተማ
ውስጥ ለመስሪያ
ለመሸጫ
የሚሆኑ ከ4ሺ
ሔክታር
በላይ
በሆነ መሬት ላይ ቦታዎችን አዘጋጅቶአል፡፡በገጠር
112ሺ
ሔክታር
መሬት
በግብርና
ለተሠማሩ
ወጣቶች በነጻ እንዲሠጥ
መደረጉ ወጣቱ የበለጠ ስራ በአዲስ ተስፋ እንዲሰራ የሚያበረታታ ነው፡፡
በኦሮሚያ ክልል
ሥራአጥ ወጣቶች በተለያዩ
የሥራ ዘርፎች
እንዲሠማሩ
ለማድረግ
የፌደራል መንግሥት ከተንቀሳቃሽ ፈንድ
3 ነጥብ
4 ቢሊዮን ብር
፤የክልሉ
መንግሥት 1 ቢሊዮን
ብር
የመደበ
ሲሆን
የኦሮሚያ
ብድርና
ቁጠባ
ተቋም
1 ነጥብ
5 ቢሊዮን ብር
ለወጣቶቹ
የብድር
አገልግሎት
ለዋማል ማዘጋጀቱ ለወጣቶች የሰጠውን
ልዩ ትኩረት ያሳያል፡፡
ለወጣቶች
የስራ እድል ፈጠራ ትኩረት መሰጠቱ በሀገር ደረጃ የሚበረታታ የሚደገፍ ትልቅ ተግባር ነው፡፡ሕዝቡ ልጆቹን በስራው
እንዲበረቱ እንዲጠነክሩ የማድረግ ቤተሰባዊና ሀገራዊ ግዴታ አለበት፡፡በገጠርና በከተማ የሚገኙ ወጣቶች በየደረጃው የየራሳቸውን የፈጠራ ስራ ተጠቅመው ውጤታማ ለመሆን ሰፊ ጥረት ማድረግ ለስራ የተመደበላቸውን
ገንዘብ በከፍተኛ የኃላፊነት መንፈስ መያዝ ትርፋማ በሚሆንበት መልኩ መጠቀም ይጠበቅባቸዋል፡፡
ቀደም ባሉ አመታት
በአነስተኛና ጥቃቅን የተደራጁ ወጣቶች አብዛኛዎቹ ውጤታማ መሆን ሲችሉ አንዳንዶች ገንዘቡን በብድር ወስደው አልባሌ ቦታ
ያዋሉበት እየተደራጁ በመምጣትም ገንዘብ ወስደው ያለአንዳች ስራ ያባከኑበት ሁኔታም ታይቶአል፡፡ዛሬም የተለየ ስሌት በማስላት
ገንዘቡን እጃቸው አስገብተው ሊጫወቱበት የሚያስቡ አይኖሩም ለማለት አይቻልም፡፡
ገንዘቡ ከድሀ ሀገር ካዝና
የወጣ ወጣቱ ሰርቶ ተለውጦ አግኝቶ ራሱንና ቤተሰቡን በአጠቃላይም ሕይወቱን እንዲለውጥ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ የመደበው መሆኑን
ማሰብም ተገቢ ነው፡፡ወጣቱ ያገኘው እድል ትልቅ ነው፡፡እራሱን የስራ ባለቤት ሊያደርግበት ሊለውጥበት አዳዲስ ስራዎች ሊፈጥርበት
ይችላል፡፡
እያደገ ከመጣው የሀገሪቱ
የወጣት ቁጥር አንጻር መንግስት ችግሩን አቅም በፈቀደ መጠን ለመቅረፍ የተቻለውን ሁሉ በሚያደርግበት ወቅት ወጣቱ በበኩሉ
በበለጠ ሀገራዊ ኃላፊነት የድርሻውን መወጣት ይጠበቅበታል፡፡የተመደበው ገንዘብ ተጨማሪ የስራ እድሎችን ለሌሎችም ዜጎች እንዲከፈት
የሚያበረታታ ነው፡፡
የሕዝብ ቁጥር በስፋት መጨመሩ አሳሳቢ ተደርጎ ሊወሰድ የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡ይህን
በተመለከት ከበለጸጉት ሀገራት ልምድና ተሞክሮ መማር ወሳኝነት አለው፡፡ልጅ ይወለድ በእድሉ ያድጋል የሚባልበት ዘመን አልፎአል፡፡ሲወለድ
የሚበላውን የሚጠጣውን የሚታከምበትን የተሻለ ትምህርት የሚያገኝበትን ብቁና ሀገራዊ ሀላፊነት የሚሰማው ዜጋ ሁኖ ተኮትኩቶ
የሚያድግበትን መንገድ ሁሉ ማስላትን ይጠይቃል፡፡የወጣቶችን የስራ አጥነት ችግር መቅረፍ የሚቻለው ሀገራዊ የኢኮኖሚ አቅማችን በሚፈቅደው
መሰረት ነው፡፡ይሄን ችግር ዛሬ በአለማችን አድገዋል በልጽገዋል የተባሉትም ሀገሮች መሉ በሙሉ አልፈቱትም፡፡ሊፈቱትም
አይችሉም፡፡
በአሜሪካ በእንግሊዝ በፈረንሳይ በኢጣሊያና ሌሎችም ሀገራት ካፒታሊዝም ከሚከተለው
የኢኮኖሚ ስርአት በመነሳት የወጣቱ የስራ አጥነት ቁጥር ተባብሶ ቀጥሎ ነው የሚገኘው፡፡ ይህንን የወጣቶች የስራ አጥነት ቁጥር
ያውም በአለም ላይ ግዙፍ ሕዝብ ያላት ቻይና ብቻ ናት በተለያየ መንገድ ወደስራ በማሰማራት በተወሰነ ደረጃ ለመቅረፍ
የቻለችው፡፡
የእኛ ኢኮኖሚ አሁን ካለውም በላይ አቅማችን እያደገ ሲሄድ የበለጠ የስራ እድሎችን
ለመፍጠር የሚችል ቢሆንም በየግዜው ባልተጠበቀ ሁኔታ የሕዝቡ ቁጥር የሚጨምር ከሆነ ኢኮኖሚው ሊሸከመው አይችልም፡፡የተመጣጠነ የሕዝብና
የኢኮኖሚ እድገት ተሸካክሞ ሊሄድ የሚችል ሁኔታ ነው መፍጠር ያለብን፡፡ለዛሬው ግዜያዊ መፍትሄ ብቻ ሳይሆን እንደ ሀገር ዘላቂ
መፍትሄ ማስቀመጥም ይጠበቃል፡፡የኢኮኖሚ እድገታችን እያደገ የመጣውን የሕዝብ ብዛት የሚሸከም አቅም በመፍጠሩ ረገድ ሊታሰብበት
ይገባል፡፡የሕዝብ ቁጥር መጨመር ራሱን ችሎ እድገት አይደለም፡፡ሊሆንም አይችልም፡፡
ዛሬ 70 በመቶ የሚሆነውን ወጣት ሙሉ በሙሉ ስራ ማስያዝ ይቻላል የሚል ካለ ጤነኛ
አእምሮ ያለው ሊሆን አይችልም፡፡ይሄንን የመንግስት ችግር አድርገው የሚወስዱትም ካሉ ተራ የፖለቲካ ትርፍ ማግኘት የሚሹ
አልባሌዎች ናቸው የሚሆኑት፡፡ማድረግ ያለብን ሰፊ ሀገራዊ አማራጮችን ማስላት ነው፡፡ወጣቱ ስራን አክብሮ ምርጫ ውስጥ ሳይገባ
እንዲሰራ ማበረታታት ማስተማር ስራንም በራሱ በኩል እንዲፈጥር ማትጋት ነው መፍትሄው፡፡
ስራ ክቡር
ነው፤ሰውን ሰው ያደረገው ስራ ነው፤ስራ አለምን የለወጠ አለምን ያሳደገ በመሆኑ የስራን ታላቅነት መረዳት ሀገርን ያሳድጋል ሕብረተሰብን
ይለውጣል የሚለው ሰፊ ግንዛቤ እንዲፈጠር መሰራት አለበት፡፡የውጭ ስደት ሀገርን ለቆ የተሻለ ስራና ሕይወት ፍለጋ የሚደረገው አደገኛ
ፈተና መከራ እንግልት የሕይወት መስዋእትነት የሚጠይቅ በመሆኑ ከሚያስከትለው ውርደት የበለጠም ሰብአዊ ክብርን የሚገፍ የጉልበትና
የወሲብ ባሪያ የሚያደርግ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡
ከዚህ
ይልቅ በሀገር ሰርቶ ማደግ መለወጥ ይቻላል ብሎ ወጣቱ እንዲያስብ ሰፊ ስራዎች በየመስኩ መስራት አዋጪ ይሆናል፡፡ወጣቱ በስደት ያውም
በሕገወጥ መንገድ ከሀገሩ ወጥቶ ጉልበቱን በማፍሰስ የሰው ሀገርን ከሚያለማ ከሚገነባ የጉልበት ባርነት ውስጥም ከሚገባ ሀገሬን ባገለግል
ባለማ የበለጠ ተጠቃሚ እሆናለሁ ብሎ የሚያስብበትን ሁኔታ መፍጠር ሁሉንም ወገን ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡
ስደትን
እንደ ክብር የሚወስዱት ወገኖች ከነጻነትና ከባርነት የቱ ይሻላል የሚለውን ምርጫ ማሰብ አለባቸው፡፡ምንም ሆነ ምን ሀገር ትሻላለች፡፡በሀገር
ላይ ሰርቶ ማደግ ሰርቶ መለወጥ ይቻላል፡፡ዛሬ በሀገራችን ጠንክረንና ተግተን ከሰራን ነገ የተሻለ ቀን ነው፤የለማች ያደገች የበለጸገች
የተከበረች ለዜጎችዋም የተመቸች ኢትዮጵያን እንፈጥራለን እንገነባለን የሚለው ታላቅ መንፈስ በወጣቶቻችን ውስጥ ሊሰርጽ ይገባል፡፡ኢትዮጵያ
ታላቅ የነገ ተስፋ ያላት ሀገር ነች፡፡
ማጠቃለያ
ወጣቱ
ተተኪና ሀገር ተረካቢ ትውልድ ነው፡፡የተሰጡትን የስራ እድሎች አስፋፍቶና አሳድጎ መጠቀም ይኖርበታል፡፡ስራ ክቡር ነው፡፡ስራ ሀገርን
ይለውጣል፡፡ስራ ያሳድጋል፡፡ ያለስራ ለውጥና እድገት የለም፡፡ሀገር የሚለማው የሚያድገው በስራና በስራ ብቻ ነው፡፡ወጣቶቻችን ይህንን
መርሕ አጥብቀው ሊከተሉት ይገባል፡፡
No comments:
Post a Comment