Wednesday, 26 April 2017

ከኢትዮጵያ.... በስተቀር !!

ይነበብ ይግለጡ

የአፍሪካ  እድገትና መነሳት በስፋት ለሚገኘው አፍሪካዊ ወጣት ተደራሽ መሆን አብሮ ይዞት መጓዝም አልቻለም፡፡የወጣቱ የስራ አጥነት ችግር  በመላው አፍሪካ የሚታይ ችግር ሲሆን አንዲት ከአፍሪካ ውስጥ ብቸኛ ሀገር ኢትዮጵያ የወጣቱን ችግር ለመፍታት የምትችለውን ሁሉ እያደረገች ነው ሲል የኢብራሂ ሞ ፋወንዴሽንን ዘገባ መነሻ በማድረግ ኩዋርትዝ አፍሪካ ዘግቦአል፡፡

በሀገር አቅም በሀገር ገንዘብ ወጣቱን የራሱ ስራ ባለቤት ለማድረግ ሰርቶም እራሱን እንዲለውጥ በተራውም የስራና የፈጠራ ችሎታውን ተጠቅሞ አዳዲስ የስራ መስኮችን ለዜጎች እንዲፈጥር ኢትዮጵያ ለወጣቶችዋ ቅድሚያ በመስጠት የምትችለውን ሁሉ እያደረገች ነው፡፡ በመሬት ላይ ያለ ተጨባጭ እውነት ነው ዘገባው ያሰፈረው፡፡ምስክርነቱ ራሱን ችሎ መሰጠቱ የሚያበረታታ ነው፡፡ከድፍን አፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያ በምሳሌነት መጠቀስዋ ለበለጠ ውጤት የሚያነሳሳ ነው፡፡

በአለፉት አስርት አመታት ኢኮኖሚያቸው አድጎና ተንሰራፍቶ የነበሩት የአፍሪካ ሀገራት ጭምር የወጣቶቻቸውን ችግር በማጤንና በመረዳት መፍታት አልቻሉም፡፡አፍሪካ እያደገች እየተነሳች፤እያሻቀበች ነው የሚለው አባባል ለአፍሪካ ወጣቶች በተጨባጭ ያደረገው ወይም የሰራው ነገር ትንሽ ነው፡፡አህጉሪቱን በመላው ጉልበቱ ሊለውጣት የሚችለው የወጣቱ ኃይል በአፍሪካ ውስጥ እንደ አደጋ እየተቆጠረ ነው ሲል ኩዋርትዝ አፍሪካ ይገልጻል፡፡

በሞ ኢብራሂም ፋወንዴሽን የወጣው አዲስ ሪፖርት የአፍሪካን አህጉር ወጣቶች ተጨባጭ ሁኔታ በሚያሳይ ዳታ የታጨቀ ነው፡፡ሪፖርቱ መለየት የቻለው በአንድ ወቅት በአህጉሪቱ ብልጭ ብሎ የነበረው ተስፋ ወደ ተስፋ ማጣትና ጨለማነት መቀየሩን ነው፡፡ፖለቲካዊ ቅዠት፤ከችሎታ ጋር ያልተመጣጠነ ትምህርትና ከጀርባ ማምለጥ እንዲሁም አሸባሪነት የአፍሪካን አህጉር ወጣቶች ሕልም እየነጠቁ ነው ብሎአል፡፡   
በአፍሪካ ውስጥ ሀምሳ ሀገራት ሲፈተሹ የሞ ኢብራሂም ፋወንዴሽን ሪፖርት የደረሰበት ግኝት እድገቶች ቢኖሩም በአፍሪካ ስራ አጥነት በቋሚነት የቀጠለ ሲሆን አሁንም ከፍተኛ ነው፡፡ የተለያየ ብሔራዊ ገቢ ባላቸው ሀገራትም የወጣቱ ስራ አጥነት ተመሳሳይ ነው፡፡ ለምሳሌም በኬንያና በሱዳን የወጣቱ ስራ አጥነት ቁጥር  22 በመቶ ሲሆን በ2016 የኬንያ ብሔራዊ ገቢ 6 በመቶ ያደገ ሲሆን የሱዳን ደግሞ በግማሽ ወደ 3. 1 በመቶ ነበር፡፡
የወጣቱን ስራ አጥነት ችግር ለመፍታት ለረዥም ግዜ ትምህርት እንደ መፍትሄ ተወስዶ ቆይቶአል፡፡ቢሆንም ሪፖርቱ የሚጠየቀው ችሎታና የሚገኘው ስራ ያለመገጣጠማቸውን ያሰምርበታል፡፡በቱኒዚያና ግብጽ ወጣቶች እጅግ በጣም ከተማሩት ውሰጥ የሚገኙ ቢሆንም የወጣት ስራ አጥነት ቁጥር  ከ60 በመቶ በላይ ነው፡፡የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ ስራ እንደማያስገኝ አረጋግጦአል ሲል ሪፖርቱ ይገልጻል፡፡
ሪፖርቱ ይቀጥላል፡፡አሁንም ቢሆን በአህጉሪቱ ብሩህ ተስፋ ሰጪ ነጥብ አለ፡፡እንደሌሎች የተለየየ ኢኮኖሚያቸውን ለማሳደግ እንደሚታገሉት ሁሉ ኢትዮጵያ ወደመሬት በመመለስ የተለየች ሁና ብቅ ብላለች፡፡ግብርና ግዙፉ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ነው፡፡80 በመቶውን የሠራተኛ ኃይልና ከብሔራዊ ገቢውም 40 በመቶ ይሸፍናል በማለት ይገልጻል፡፡ 
ይህም ማለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ኢኮኖሚ በ2015 ከነበረው በ2016(እኤአ) ዝቅ ሲል የወጣት ስራ አጡ ቁጥር ከነበረበት ወደ ላይ አልተወነጨፈም ሲሉ ሪቻርድ ሙሬይ የፋወንዴሽኑ ተጠባባቂ የምርምር ኃላፊ ለኩዋርትዝ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ስራአጥነት በአጠቃላይና በተለይም የወጣቱ ስራ አጥነት ባለፉት አስርት አመታት አንጻራዊ በሆነ ሁኔታ አልተለወጠም፡፡የተረጋጋና በነበረበት የነበረ ነው፡፡ የኢትዮጵያ አጠቃላይ የስራ አጥ ቁጥር 5.7 ፐርሰንት ሲሆን የወጣት ስራ አጡ ቁጥር ደግሞ 8.1 ፐርሰንት ነው፡፡በቀሪው የአፍሪካ ክፍል በአህጉሪቱ እነዚህ ቁጥሮች በአማካይ ከ8 ፐርሰንት እስከ 13 ፐርሰንት ይደርሳሉ፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ችግሮች የሌሉበት አይደለም በማለት ችግሮቹን የጠቀሰው ሪፖረት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የፖለቲካ ቀውስ ራሱን ያገኘው ስር በሰደደው የመሬት ጉዳይ ላይ የገቢ ምንጭና የማንነት መለያ አድርጎ ነው ሲል ይገልጻል፡፡
ፖሊሲዎችዋ በግብርና እድገት የሚመራ ኢንደስትራላይዜሽን የሚለው ሀገሪትዋ ሀብቶችዋንና የግብርናውን ክፍል እንድታሳድግ ረድቶአታል  ይላል ሪፖርቱ፡፡የፖሊሲውን ስኬታማነት እስከአሁን በተጨባጭ ያረጋገጠው ሳይሸረሸር አነስተኛ የእርሻ ይዞታ ባለቤቶች መብታቸው ተጠብቆ እንዲቀጥሉ ማድረጉ ነው፡፡የሕዝብ እድገትን አስከትሎአል፡፡ እድሎችን በከተማና በገጠርም አስፋፍቶአል በማለት ሪፖርቱ ኢትዮጵያን ያወድሳል፡፡
በግብርና ላይ ማተኮር ማለት አፍሪካ ምናልባት በትውልዶች ውስጥ ራስዋን መቀለብ ትችላለች ማለት ነው፡፡ ከውጭ የምታስገባውንና እርዳታን ታስወግዳለች ማለት ነው፡፡ በቴክኒዮሎጂ ውስጥ ለቴክኒሎጂ ፈጠራዎች ቦታ በመስጠት አዲሱ የአርሶአደሮች ትውልድ ቀድሞ ከነበሩት በላይ አዲስ አይነት የተለያዩ ሰብሎችን በማምረት በጣም በተስፋፋ ሁኔታ በመጨረሻም ሰፊ ስራዎችን ይፈጥራል ሲል ኩዋርትዝ አፍሪካ ዊክሊ አስነብቦል፡፡
በአፍሪካ ውስጥ በከፍተኛ ፍጥነት ቁጥሩ እየጨመረ የመጣውን ወጣት ትውልድ በየሀገራቱ የኢኮኖሚ አቅም ወደስራ ለማስገባት በአብዛኛው መንግስታት ትኩረት ሰጥተው እየሰሩበት አይደለም፡፡የወጣቱ ስራ አጥነት ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነትና ደረጃ በማደጉ ለአህጉሪቱ ልማትና እድገት የሚጠቅም ኃይል ተደርጎ ሊወሰድ ሲገባው  የሚታየው  ለመንግስታቱ እንደ ስጋትና አደጋ ተደርጎ የሚቆጠርበት ደረጃ ላይ ደርሶአል፡፡
ይህ ምስክርነት በመስኩ ጥናት አድርጎ በቅርቡ ይፋ ያወጣው  የሞ ኢብራሂም ፋወንዴሽን  የጥናትና የምርምር ግኝት ሪፖርት ነው፡፡ሀገራት ኢኮኖሚያቸው ቢያድግም የወጣቱን ስራ አጥቁጥር ለመቀነስ ያደረጉት ነገር እምብዛም ነው፡፡ ቁጥሩ ከግዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ ይገኛል፡፡ኢትዮጵያ ብሔራዊ የኢኮኖሚ አቅምዋ በፈቀደ መጠን ለወጣቶችዋ የተለያየ የስራ እድሎችን በመክፈት ሰርተው አግኝተው እንዲለወጡ ለማድረግ አቅምዋ የፈቀደውን ሁሉ አድርጋለች፡፡ በማድረግም ላይ ትገኛለች፡፡
ቀደም ባሉት አመታት በብሔራዊ ደረጃ በሁሉም ክልሎች የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማትን በማደራጀት ወጣቱ በአቅሙ ብድር ወስዶ የሚሰራበትን መንገድ በማመቻቸት በርካታ ወጣት ዜጎች በአገኙት ብድር ተጠቅመው ስራም ፈጥረው በመስራት በብዙ ተጠቃሽ መስኮች ውጤታማ መሆን ችለዋል፡፡
በእንጨት ስራ፤ በብረት ስራ፤ በንብ ማነብ፤በቤት ግንባታ፤በሸክላና በጡብ ምርት፤በምግብ ቤት፤በመዝናኛ አገልግሎት መስጫ ወዘተ ስራዎች በመሰማራት ውጤት አስመዝግበዋል፡፡ ከወጣቶቹ መካከል ደረጃቸውን አሳድገው ከነበሩበት ወደተሻለ አደረጃጀት የተለወጡ ሰፊ የስራ መስክ የከፈቱም ይገኙባቸዋል፡፡
ዛሬ ደግሞ ለወጣቱ የበለጠ የስራ እድል ለመክፈትና የራሱም የስራ ባለቤት እንዲሆን መንግስት 10 ቢሊዮን ብር የወጣቶች ፈንድ በጀት መድቦ በሁሉም ክልሎች እንዲዳረስ ወደስራ እንዲገቡም በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
ወጣቱ ተደራጅቶ በመረጠው የስራ መስክ መሰማራት መስራት የፈጠራ ችሎታውን ተጠቅም አዳዲስ ስራዎችን መክፈት የበለጠም ማስፋፋት ይችላል፡፡ለወጣቱ የተሰጠው ገንዘብ ሰርቶ በሚመለስ ብድር ነው፡፡ሰርቶ አግኝቶ ራሱን እንዲለወጥ ውጤታማና ትርፋማ ሁኖ የብድር ገንዘቡን ወደ መንግስት ይመልሳል፡፡ይሀው ገንዘብ ተመልሶ ለሌላ አስፈላጊ የሀገሪቱ ልማትና እድገት ይውላል፡፡
የዚህን ስራ ሂደትና አፈጻጸም በብሄራዊ ደረጃ የሚከታተል ራሱን የቻለ አካል ያለው ሲሆን ውጤቱ የሚመዘነው በወጣቶቹ የስራ ብቃትና በሚያስገኙት ውጤት ነው፡፡ሀገርን በማልማትና በማሳደግ ረገድ የወጣቱ ድርሻ ጉልህ ነው፡፡ወጣቱን ያላሳተፈና በወጣቱ እውቀትና ትኩስ አእምሮ እንዲሁም ጉልበት መጠቀም ያልቻለ ሀገርና ሕዝብ የማደግ ተስፋው የመነመነ ነው፡፡
ይህ እውነት ስለሚታወቅ ነው በኢትዮጵያ ውስጥ ለወጣቱ የተለየ ትኩረት የተሰጠው፡፡ ወጣቱ ስራ ፈጣሪና ስራ አክባሪ በመሆን የስራ ቦታንም ሳይመርጥ ለመስራት የሚችል ሲሆን ለውጡን እራሱ በራሱ ያየዋል፡፡ ተቀምጦ ስራን ከመጠበቅ የተገኘውን ማንኛውንም አይነት ስራ መስራት ከሰው እጅ ጠባቂነት አውጥቶ በራስ መተማመንን ያዳብራል፡፡የስራ ፍቅርንም ያሳድጋል፡፡
ዛሬ በአነስተኛ ደረጃ ወጣቱ በየቦታው የጀመረውና እየሰራ ያለው ስራ ነገ በከፍተኛ ደረጃ ወደ ካምፓኒዎችን ኢንዱስትሪዎች ሊያድግና ሊሰፋ ይችላል፡፡ በርካታ ሰራተኞችን ቀጥረው መስራት የሚችሉበት አቅምና ጉልበትም ያገኛሉ፡፡ በሌላውም አለም አንድ ስራ ሲጀመር መነሻው ትንሽ ነው፡፡ እያደገና እየሰፋ የሚሄደው በሂደት ነው፡፡

Wednesday, 19 April 2017

አልላቀቀን ያለው ስደት

                                                                                          ይነበብ ይግለጡ

ድሮ ድሮ ሀገርን ለቆ መሰደድ በባሕላችን እንደ ነውር ይቆጠራል፤ ኢትዮጵያዊያንን በውጭ ሀገራት  በስደት ማግኘትም እጅግ በጣም ብርቅ ነበር፡፡ በንጉሱ ዘመን ውስን ስደተኞች ነበሩ፡፡ ስደት የባሰውና ገዝፎ የወጣው ግን በደርግ ዘመን ነው፡፡ ፖለቲካውን በመፍራት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በሱዳን፣ በኬንያ፣ በጅቡቲና የመን አድርገው ወደተለያዩ የአለም ሀገራት ተሰደዋል፡፡
ጥያቄው ከመኖርና ካለመኖር ጋር የተያያዘ ስለሆነ የስደት ሕይወትን መረጡ፡፡ ከዚያን ግዜ የጀመረው የኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን ለቀው የመሰደድ ጉዳይ በኢህአዴግ ዘመንም ብሶበት ጭራሹንም ከጣራ በላይ ወጣ፡፡ አልፎም ሄደ፡፡ ዛሬ በመላው አለም ከአፍሪካ አስከ ኤሽያ አውስትራሊያና አውሮፓ ድረስ መገመትና ማመን በማይቻልበት መልኩ ኢትዮጵያውያን የሌሉበት ሀገር የለም፡፡ እንደሚታወቀው አሜሪካ ሁለተኛ ሀገራቸው ናት፤ እስከ 1ሚሊዮን የሚጠጉ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ይኖራሉ የሚሉ ግምቶች አሉ፡፡ 
በአረቡ አለም የተለያዩ ሀገራት ብዙ ሺህ ኢትዮጵያውያን በሕገወጥ መንገድ ገብተው እየሰሩ ይኖራሉ፡፡ እነዚህ ስራ ፍለጋ የሄዱ ሰርተን አግኝተን የራሳችንንና የቤተሰባችንን ሕይወት እንለውጣለን ብለው ከፊት ለፊታቸው አፍጥጦ የመጣውን ሞት ሁሉ ተጋፍጠው በማለፍ የሰው ሀገር ድንበር አልፈው ማስረጃ ሳይኖራቸው የገቡ ናቸው፡፡ በመንገድ ላይ በአውሬ ተበልተው የቀሩትን፣ በባሕር ሰምጠው የሞቱ ዜጎቻችንን ቁጥር ቤቱ ይቁጠረው ማለቱ ይቀላል፡፡
አንዱና የሕገወት ስደት ዋናው ተዋንያን በሕገወጥ የሰው ዝውውር ስራ ላይ ተሰማርተው የከበሩና የደለቡ እንደ ባርያ ንግድ ዘመን የራሳቸውን ዜጎች ለውጭ ሰው-በላ ነጋዴዎችና አዘዋዋሪዎች እየሸጡ ያሉ ሰዎች በብዛት መንሰራፋትና መደበኛ ሕይወታቸው አድርገው የመቁጠራቸው ጉዳይ ነው፡፡
በዚህ ሕገወጥ ስራ በዘረጉት ሕገወጥ መዋቅርና ሰንሰለት ከከተማ እስከ ገጠር ወኪሎቻቸውን በመመደብ በተለይ ወጣቱን በባዶ ተስፋ በመሸንግል ከፍተኛ ገንዘብም በመቀበል ለስደት ሲያበረታቱት፤ በብዛት አገሩን ለቆ እንዲፈልስ ሲያደርጉት ኖረዋል፡፡ ቀደም ብሎ በተወሰኑት ላይ እርምጃ ቢወሰድም ዛሬም በስውር መስራታቸውን ቀጥለዋል፡፡
የኢኮኖሚ ስደተኞች ዋና አላማ የትም ሀገር ቢሆን ድንበርን በሕገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት አልፎ በመሄድ የሚመጣውንም እስከ ሞት የሚደርስ መከራ በመቀበል ሰርቶ መኖር፣ ማግኘትና መለወጥ ነው፡፡ በተቃራኒው፣ ያለሙት ቀርቶ በተለያዩ ሀገራት ዛሬም የሰውን ሀገር ድንበር በሕገወጥ መንገድ ጥሰው በመግባታቸው ተይዘው በእስርቤት ውስጥ የሚገኙ በርካቶች ናቸው፡፡
የአረቡ አለም ደግሞ የባሰ ይሁን እንጂ በሊቢያ የሚገኙም አሉ፡፡ እንዴት አድርገው እዛ ደረሱ የሚለው በራሱ በጣም አስጨናቂ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ተነስቶ ድንበር አልፎ እያቆራረጡ ሊቢያ መድረስ ተአምር ነው፡፡ በሌሎች ሀገራትም እንዲሁ፡፡ በአረቡ አለም ለስራ ፍለጋ በሕገወጥ መንገድ ከሀገራቸው ወጥተው የሚኖሩ ብዙ ሺህ ኢትዮጵያውያን አሉ፡፡ ወንዶችም ሴቶችም፡፡ አግብተው የወለዱም አሉ፡፡
በሕጋዊ መንገድ ከሀገራቸው ስላልወጡ የሚደርስባቸው ፈተናና መከራ እንግልት ሊገለጽ ከሚችለው በላይ መሆኑን እራሳቸው በተለያዩ ግዜያት በሚዲያ ተናግረውታል፡፡ ሆን ተብሎ በአሰሪዎቻቸው ከፎቅ እየተወረወሩ የሞቱ፤ አካለ ጎደሎ የሆኑ፤ ሕይወታቸው በድብደባና በስለት ያለፈ እህቶችና ወንድሞች ቁጥር ከፍተኛ ነው፡፡ ዛሬም በአረቡ አለም እስርቤቶች በርካታ ኢትጵያውያን ይገኛሉ፡፡
ጥያቄው ለዚህ አሳሳቢ ለሆነ ብሔራዊ ክብርን ለሚነካ ችግር እንዴት አይነት መፍትሔ ሊገኝለት ይችላል የሚለው ነው፡፡ መንግስት በተደጋጋሚ እንደገለጸው ዜጎች ስራ ፈልገው ከሀገር ሲወጡ በሕጋዊነት መታወቂያና ፓስፖርታቸውን ይዘው ቢወጡ ለሚደርስባቸው ኢሰብአዊ ድርጊትና ክብረ ነክ ጉዳዮች መከላከል ይቻላል፡፡ መንግስት ከመንግስት ጋር ይነጋገራል፡፡ መፍትሄም ይኖረዋል፡፡ በሕጋዊነት ተመዝግበው  ካልሄዱ ግን ምን እንደደረሰባቸው፣ የት እንዳሉ፣ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ አይቻልም፡፡ ይህ ጉዳዩን አስቸጋሪና ውስብስብ ያደርገዋል፡፡
አሁንም የሚመከረው መንግስት አውቆት ሕጋዊ ሁነው ለስራ ከሀገር ቢወጡ ነው ባሉበት ደህንነታቸውን መከታተልና ማስጠበቅ የሚቻለው፡፡ በሕገወጥ መንገድ ከሀገራቸው ከወጡ በኋላ ያለው ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ለማንኛውም አደጋ ተጋላጭ ያደርጋቸዋል፡፡ ምንም አይነት የሕይወት ዋስትና የላቸውም፡፡ አልፎ ተርፎ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ሴቶች እህቶቻችንን በሕገወጥ የሰው ዝውውር የተሰማሩት ሰዎች ለወሲብ ንግድ ይሸጡዋቸዋል፡፡ ይሄ ደግሞ ከራሳቸውም አልፎ ብሔራዊ ክብርንና ማንነትነን በእጅጉ ይጎዳል፡፡ ይሄን ቸግር በአንድ ግዜ ማስቀረት ባይቻልም በየደረጃው መፍትሄዎችን ማስቀመጥ ግን ይቻላል፡፡
አንዱና ዋነኛው ሰራ መሆን ያለበት ያለማሰለስ የስደትን አስከፊነት ስደተኞች የሚደርስባቸውን ግፍና በደል ጭቆና ኢሰብአዊ ድርጊት በሚዲያ አማካኝነት በሰፊው ለሕዝቡ ማሳወቅና ማስተማር ነው፡፡ ሌሎች ዜጎች እንዲጠነቀቁና አደጋውን አስቀድመው እንዲረዱ ያደርጋል፡፡ ሌላው በአሁኑ ሰአት ሀገራችን የተሻለ የስራ እድል ለዜጎችዋ መፍጠር የምትችልበት ሁኔታ ስላለ በየአካባቢያቸው በመረጡት የስራ መስክ ለመሰማራት የሚያስችል ፕሮጀክት ቀርጸው ከመንግስት ብድር መጠየቅ፣ ማግኘትና ወደስራ መግባትም ይችላሉ፡፡
የቢሮክሲው ውጣ ውረድ እንዳይበዛ መንግስት ይሄንን በተመለከተ ራሱን የቻለ በከፍተኛ አመራር ክትትል የሚደረግበትና ፈጣን ውሳኔ የሚሰጥበት ከስደት ተመላሽ ዜጎች የገንዘብ ብድርና ቦታ አግኝተው ወደስራ የሚገቡበትን ሁኔታ የሚመራና የሚቆጣጠር አካል መፈጠር አለበት፡፡ በአብዛኛው  ችግሩ የሚፈጠረው በላይኛው አካል አይደለም፡፡ ትልቁን ማነቆና እንግልት የሚፈጥሩት በታችኛው አመራር ውስጥ የሚገኙ  አካላት ናቸው፡፡ በተደጋጋሚ ግዜ በአሰልቺ መልኩ ታይቷል፡፡ አንዱ መፍትሔ ሊሆን የሚችለውም ይሄንን ማስወገድ ነው፡፡
ሌላው ከስደት በፊት ዜጎች እየተደራጁ ስራ መስራት የሚችሉበት ወይንም ስራ ራሳቸው የሚፈጥሩበትና በመንግስት የሚታገዙበት የንግድ ትስስር መረብ የሚፈጥሩበት ሁኔታ በሰፊው መጠናት ያለበት ጉዳይ ነው፡፡ ባለፉት አመታት ከሳኡዲ አረቢያ ተመላሽ ዜጎችን በስፋት ተቀብሎ ወደስራ ሊሰማሩ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ስልጠና ተሰጥቶ ወደ ስራ እንዲገቡ የተደረገበት ሁኔታ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ከፊሎቹ ሌላ መንገድና ዘዴ ተጠቅመው ተመልሰው ወደስደት እንደሄዱ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ሀገራቸው ሁነው ውጤታማ የሆነ ስራ በመስራት ላይ የሚገኙም እንዳሉ ይታወቃል፡፡ የሕገወጥ ስደተኞች ችግር ዳግም አገርሽቶበት ሳኡዲ አረቢያ ማስረጃና የስራ ፈቃድ የሌላቸው ሕገወጥ ስደተኞች በአስቸኳይ ተመዝግበው በ90 ቀናት ውስጥ በራሳቸው ትራንስፖርት ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዋጅ አስነግራለች፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ከፍተኛው ቁጥር የኢትዮጵያውያን እንደሚሆን ይገመታል፡፡
በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ ዜጎቻችን እንግልት ሳይደርስባቸው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ቃል አቀባዩ ለመገናኛ ብዙሀን ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ሳኡዲ ድረስ በመሄድ ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር የተነጋገሩ ሲሆን ከውይይቱ በኋላ ዜጎች በቀላሉ መውጫ ቪዛ እንዲያገኙ በሳዑዲ መንግስት በኩል ተንቀሳቃሽ ጽህፈት ቤቶች እንዲከፈቱ መደረጋቸውም ታውቆአል፡፡ በሪያድና በጂዳ የሚገኙ ሚሲዮኖች የጉዞ ሰነድ አሰጣጥ የተቀላጠፈ እንዲሆን፤ ሊያጋጥሙ በሚችሉ ቸግሮችም ዙሪያ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በሳዑዲ ከሚኖሩ የኮሚዩኒቲ ማሕበራትና የተለያዩ አደረጃጀቶች ጋር ውይይት ተደርጎአል፡፡ እስካሁን ባለው ሁኔታ 4ሺህ ሕገ ወጥ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን የጉዞ ሰነድ ወስደው 200 የሚሆኑት ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ችለዋል፡፡
ቃል አቀባዩ እንደገለፁት ይህ ቁጥር መግባት ከሚገባው አሃዝ አንጻር ሲታይ ዝቅተኛ ነው፡፡ በመሆኑም፣ መገናኛ ብዙሐን የአዋጁን ምንነት በማሳየት በዜጎች ላይ ሊደርስ የሚችለውን ችግር ለመቅረፍ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡ በሕገ ወጥ መንገድ ድንበር አቋርጠው የገቡ ስደተኞች፣ ቋሚ ቦታ ሳይኖራቸው በመዘዋወር በሕገ ወጥ መንገድ የሚሰሩ ስደተኞች፣ የስራ  የመኖሪያ ፍቃድ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ የውጭ ሐገራት ነዋሪዎች፤ የስራ ፍቃድ ኖሯቸው የመኖሪያ ፍቃድ መታወቂያ ካርድ የሌላቸው፣ ለዑምራና ሐጂ ሄደው በዚያው የቀሩ ወይም የቆይታ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ነዋሪዎች፣ ያለ ሐጂ ፍቃድ የተጓዙ አማኞች በሳዑዲ መንግስት ሕገወጥ ተብለው የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
አሁን አሳሳቢው የስደት ቸግር እንዴት ለዘለቄታው ይገታ የሚለው ነው፡፡ የመንግስት ድርሻ እንዳለ ሆኖ፣ በሰፊው ከሕብረተሰቡ ጋር መወያየት የመፍትሔ ሀሳቦችንም ማመንጨት ከሁሉም ወገን ይጠበቃል፡፡