Tuesday, 27 December 2016

...ስለ ዴሞክራሲ ሞተ



     
ተፊሪ መኮንን

ሐይማኖት እና እምነት ዋና የህይወት ጎዳና ባለሆኑበት ምዕራባውያን ዘንድ የገና በዓል በልዩ ስሜት እና ትኩረት ይከበራል፡፡  የገና ዛፍ ይዘጋጃል፡፡ ከቤተሰብ ራቅ ብሎ የሚኖረው ሁሉ ከያለበት የዓለም ክፍል ሻንጣውን ቀርቅቦ፣ ውቂያኖስ አቋርጦ ይጓዛል፡፡ የገና ሸመታ ሰፊ ነው፡፡ ስጦታው ብዙ ነው፡፡ የገና ዛፍ በብርሃን ይደምቃል፡፡ በዓሉ እንጂ የበዓሉ ምክንያት አይታሰብም፡፡ በቃ ወግ ነው፡፡
ይህን ግርምቢጥ የሆነ ነገር የሚጠቅሰው አለን ብሉም የተባለ አሜሪካዊ ፀሐፊ፤ ‹‹እኛ አሜሪካውያን ፍቅር ምን እንደሆነ እንኳን ጠፍቶብናል›› ይላል፡፡ የአሜሪካ ወጣቶች ከፍቅረኛቸው ጋር ተጣልተው ሲለያዩ፤ ‹‹I love you ይባባሉ›› ይላል፡፡ በዚህ የወጣቶቹ ነገር የተገረመው ብሉም፤ ‹‹I love you ማለት፤ አልወድሽም የሚል መልዕክት ያለው ይመስላል›› ይላል፡፡ አክሎ፤ ‹‹አሜሪካውያን ወጣቶች አንድ የማይታሙበት ነገር አለ፡፡ የሰዎችን ነጻነት በማክበር በኩል አይታሙም፡፡ ‹‹መብቱ ነው፡፡ መብቷ ነው ይላሉ፡፡ የመብታቸው እና የነጻነታቸው መሠረት ምን እንደሆነ በውል አያውቁትም›› ሲል ይተቻል፡፡

ፀሐፊው የዩኒቨርሲቲ መምህር ነው፡፡ ከዚሁ ካነሳው ችግር ጋር የተያያዘ አንድ አስገራሚ ይጠቅሳል፡፡ በክፍል ውስጥ ለሚያስተምራቸው ተማሪዎቹ አንድ ጥያቄ አቀረበላቸው፡፡ በእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ በተያዘችው ህንድ አንድ ልማድ አለ፡፡ ባል ሲሞት፤ ሚስቲቱ ከነህይወቷ ከባሏ ጋር ትቀበራለች፡፡ በእንግሊዝ የቅኝ አገዛዝ መስተዳድር፤ አንድን የህንድ ግዛት የሚያስተዳድረው እና ‹‹ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር  የማይገሰስ መብት አለው›› በሚል የፖለቲካ መርህ ተወልዶ ያደገው እንግሊዛዊ አስተዳደሪ ይህን የህንድ ልማድ ለመቀበል ተቸገረ፡፡ ሰው ከነ ህይወቱ ሲቀበር ዝም ብሎ ለማየት አልቻለም፡፡ ሆኖም ‹‹እንዲህ ልታደርጉ አትችሉም›› ብሎ መከልከል፤ የህንድን ባህል ካለማክበር የሚቆጠርብት ስለሆነ በሥጋት ተወጠረ፡፡

ይህን ታሪክ ለተማሪዎቹ የተረከላቸው መምህሩ አለን ብሉም፤ በማያያዝ ለአሜሪካውያን ተማሪዎቹ አንድ ጥያቄ አቀረበላቸው፡፡ ‹‹ለመሆኑ እናንተ የህንድ አስተዳዳሪ ብትሆኑ ምን ታደርጋላችሁ?›› ሲል ጠየቃቸው፡፡ የሰዎችን ነጻነት በማክበር የማይታሙት ተማሪዎቹ በጥያቄው ተቸገሩ፡፡ በነገሩ ብዙ ካሰቡበት በኋላ በመጨረሻ የሰጡት መልስ፤ በሽሽት ጎዳና የሄደ መልስ ነበር፡፡ ‹‹የሟቹ ባለቤት አብራ ልትቀበር አይገባም›› የሚል መልስ ሣይሆን፤ ‹‹እንግሊዝ ወደ ህንድ መሄድ አልነበረባትም›› የሚል መልስ ነበር የሰጡት፡፡ ምላሻቸው አስገራሚ ነው፡፡ መብት እና ነጻነት ከመሠረታዊ የፍልስፍና መነሻቸው ተነጥለው ሲያዙ የሚፈጠረው ችግር እንዲህ ያለ ነው፡፡ የገና በዓልን ከክርስቶስ ልደት እና ከሞራላዊ አንድምታው ለይተው እንደያዙት፤ መብት እና ነጻነትን ለሁሉም መብቶች እና ነጻነቶች (የባህል መብት) መሠረት ከሆነው በህይወት የመኖር መብት ነጥለው ይዘውታል፡፡

የአሜሪካ ዴሞክራሲ እንደ ዶናልድ ትራምፕ ዓይነት ሰው ለመቀበል እና ረጅም ርቀት ይዞት ለመሄድ ፈቃደኛ ሆኗል፡፡ ይህ አጋጣሚ የዴሞክራሲን ሞራላዊ ዳራ ለመቃኘት ያስገድዳል፡፡ የዴሞክራሲ እናት በሆነችው ግሪክ በሶቅራጥስ ዘመን ዴሞክራሲ ወይም የህግ የበላይነት፤ እንደ እምነት ወይም ሐይማኖት የተያዘ ጉዳይ ይመስላል፡፡ በዓለ ገናን ከክርቶስ እና ከኢየሱስ አስተምህሮ መነጠል እንደማይቻል፤ ዴሞክራሲ ከሞራላዊ ዳራው ተለይቶ ሊቆም አይገባም፡፡ የሶቅራጠስ ህይወት ለዚህ ማስረጃ ነው፡፡

አውደ-ሐሳብ
ሠረቀ ብርሃን ገብረ እግዚእ የተባሉ የሀገሬ ሰው ‹‹ክሪቶን›› በሚል ርዕስ (በ1947 ዓ.ም) ባሳተሙት አንድ መጽሐፍ፤ ስለ ሶቅራጥስ ሐገር ስለ አቴና ሰዎች ሲናገሩ፤ ‹‹ከፍጥረቱ ስጉ፣ ንቁ፣ ጠያቂ እና ተመራማሪ የሆነው የአቴና ሕዝብ በአምልኮ፣ በባህል እና በሐሳብ ልዩ ልዩ ከሆኑ ሕዝቦች ጋር ግንኙነት በማድረጉ፤ በመጠያየቅ፣ በመወያየት፣ በመነጋገር እና በመከራከር ይበልጥ ነቃ›› ይላሉ፡፡ የዴሞክራሲ ማህጸን በሆነችው አቴና የነበረው ‹‹ማህበራዊ ዓውድ፤ ፍቱን የሚሆን የአዕምሮ ምርመራ ለመከተል ዝግጁ የሆነ አስተሳሰብ እንዲፈጠር የሚያደርግ መሆኑን›› ገልጸው፤ ‹‹በዕውቀት ወይም በህሊና ለመመራት እና ለመረዳት ችሎታ ያለው መሆኑን የተገነዘበው የሰው ልጅ፤ በምናብ ከሐሳቡ የፈጠራቸውን አማልክት በዕውቀት ሊሽራቸው ደፈረ፡፡››

ሠረቀ ብርሃን አክለው፤ ‹‹ይህም የስህተት መጋረጃ መቀደዱ የሰውን ልጅ ከክህደት የጣለው መሰለ፡፡ ፍልስፍና ፍቱን ማስረጃ በሚሰጥ ጎዳና እየተመራች የጣዖትን መቅደሶች ግርማ ካጠወለገች በኋላ፤ ሥነ ፍጥረትን፣ ረቂቅ የሓሳብ ሁኔታን፤ በተለይም በስነ ፍጥረት ላይ የማሰብ ችሎታ የተሰጠውን የሰው ልጅ ትክ ብላ ተመለክታ፤ የሰውን ልጅ ሥነ ፍጥረት ብቻ ሳይሆን የማህበራዊ አኗኗሩን ስሜቱን ሐሳቡን፣ መንፈሱን፣ የአዕምሮ እና የህሊናውን ሁኔታ መርምራ የማወቅን ነገርን ሥራዬ ብላ ያዘች›› ይላሉ፡፡

ሠረቀ ብርሃን፤ ‹‹በአጎራ አደባባይ ከሚናገሩት ፈላስፎች አንዳንዶቹ እጅግ ረቂቅ መንፈሳዊነት የሚሰማቸው ነበሩ፡፡ ሁኔታቸው ወደ ነቢይነት ወይም ወደ መናኝነት ያዘነበለ ነበረ›› ይላሉ፡፡ ታዲያ ከእነዚህ ፈላስፎች አንዱ ሶቅራጥስ ነበር፡፡ ሶቅራጥስ የድሀ ወገን ነው፡፡ አባቱ ሐውልት የሚያንጽ ባለሙያ ነበር፡፡ እናቱም ምጥ የያዛትን ሴት የምትረዳ አዋላጅ ነበረች፡፡ ሶቅራጥስ ከዓይኑ በስተቀር ሌላው መልኩ ሁሉ ጅል የሚመስል ሰው ነበረ፡፡ ‹‹ይህ ሰው የት ተማረ ሳይባል፤ እንዲሁ አልባሌ መስሎ የአቴናን አደባባይ ሲመለከተው ቆይቶ ጊዜው ሲደርስ ወይም የደረሰ መስሎ በተሰማው ጊዜ ተጠጋው፡፡››

እርሱም የተራ ሰው መሰል ጥያቄዎች እያነሳ በተጠየቅ ሥርዓተ-ሐሳብ ነገር ብሎ ያነሳውን ጉዳይ ማበራየት የሚችል ፈላስፋ ነበር፡፡ ርትዕ፣ እኩይ ወይም ሠናይ ምንድነው? ምንስ ይመስላችኋል? እያለ ይጠይቅና፤ ተጠያቂው ሰው በሚሰጠው ምላሽ ላይ ተመስርቶ፤ ለተነገረው ነገር ተቃራኒ የሚሆነውን ወይም የሚዛመደውን፣ ተመሳሳዩን፣ ተወራራሹን፣ ወይም በፍጹም ጋፊኛ የሚሆነውን ሐሳብ እያስከተለ የሰውን ሥጋዊ እና መንፈሳዊ ህላዌ በሚመለከት መመራመር እና መከራከር ሲጀምር መነሻው ‹‹ራስህን ዕወቅ›› የሚል ነበር፡፡ ሶቅራጥስ ሁሉን ሥነ ፍጥረት ያደንቃል፡፡ ነገር ግን የሰውን ልጅ ከሁሉ አብልጦ ይመከት ነበር፡፡

‹‹ማወቄ ምንም የማላውቅ መሆኔን መገንዘቤ ነው››  ብሎ የተነሳው ሶቅራጥስ፤ ጥያቄ ሲያነሳ ራሱ ለመማር የሚሻ እየመሰለ ነው፡፡ ሆኖም እንዲያ ባለ ሁኔታ የጀመረው ነገር፤ ‹‹ቀጥ ባለ፣ በማያላውስ፣ የመጨረሻውን እውነት እንጂ አስተያየትን በማይቀበል ሥርዓተ -ሐሳብ የዕውቀትን፣ በጠቅላላው የህላዌን ነገር፤ ህላዌ-ሥጋን፣ ህላዌ-ነፍስን ምንነት ይመረምር ያዘ፡፡ ሠናይ ወይም እኩይ የሚባለው ምንድነው? ርትዕ፣ ጽድቅ ምንድነው? መንግስት፣ ህግ፣ አስተዳደር፣ ሥርዓት፣ ምግባር፣ ዳኝነት፣ ፍርድ፣ መብት ግዴታ ፍቅር መውደድ እና ወዳጅነት ሐሴት ኀዘን፣ ተድላ፣ ችሎታ፣ ሐኬት፣ ሙያ፣ እንከን፣ ጥበብ፣
ብልኃት……ምንድናቸው እያለ ይጠያይቅ ነበር፡፡
ተፍጻሜተ ነገረ
ስፓርታ እና አቴና ለሰላሳ ዓመታት ያካሄዱት ጦርነት ሲያበቃ፤ በእርሱ ሰላማዊ አካሄድ ሥልጣን ለመጨበጥ ተከራካሪ በነበሩት ተማሮቹ ሲመራ የነበረው የኦሊጋርኪያ አስተዳደር ወገን በዴሞክራሲያውያኑ ወገን ሲቸነፍ በሽማግሌው ፈላስፋ ላይ ክስ ለመመስረት ተመከረበት፡፡

በወቅቱ የ‹‹ዴሞክራቶች›› እና የ‹‹ኦሊጋርኪ›› ሐሳብ አራማጅ የሆኑ አቴናውያን ነበሩ፡፡ ታዲያ አኒቶስ የተባለ ሰው የዲሞክራቶቹ ደጋፊ ነበር፡፡ ጥቅሙን ከዲሞክራቶቹ ጋር አዛምዶ የነበረ ሰው በመሆኑ ኦሊጋረኪያዎቹን ጠምዶ ይዟቸው ነበር፡፡ ስለዚህ የሶቅራጥስ ዋና ከሳሹ ሆኖ የተነሳው አኒቶስ የሚሉት ሰው ሆነ፡፡  

የሶቅራጥስ ጠላት ሆኖ የተነሳው አኒቶስ፤ በአንድ ወቅት በጦር አዝማችነት ታዝዞ የተሰጠውን ግዳጅ እና ግዴታ በሚገባ ሳያከናውን ቀርቶ በክስ ፍርድ ቀርቦ በገንዘብ እርዳታ ከቅጣት የዳነ ሰው ነበር፡፡ ይህ ሰው ሶቅራጥስ የሚያስተምረው ትምህርት የእርሱን እንከን የሚያጎላባት ስለሚመሰለው ጠልቶታል፡፡ ሶቅራጥስ ስለ አስተዳዳሪዎች የሚያሰማው ሐተታ በቀጥታ የሚነካው ይመስለው ስለነበረ ሽማግሌውን ፈላስፋ ይጠላዋል፡፡ ከዚህም በላይ የገዛ ልጁ የሶቅራጥስ አስተሳሰብ አራማጅ በመሆኑ ይናደድ ነበር፡፡

ስለዚህ የእርሱ ከሳሽ ሆኖ ከእርሱ ጋር ከፍርድ ቤት ለመቋቋም በመቻሉ እጅግ ደስ አለው፡፡  እናም እንደ እርሱ ከተከፉ ሌሎች ጓደኞቹ ጋር ሆኖ በሶቅራጥስ ላይ ክስ አቀረበ፡፡ ክሱም፤ ‹‹ሶቅራጥስ ሐገሩ በሚያምንባቸው አማልክት ባለማመኑ እና እንግዳ መናፍስትን በመስበኩ ዓመጸኛ ነው፡፡ የወጣቶችንም ጠባይ የሚያጠፋ ወይም የሚያበላሽ በመሆኑ ያምጻል፡፡ ስለዚህ ሞት ይገባዋል›› የሚል ነበር፡፡
ይህ ክስ፤ ከዘመኑ ባህል እና መንፈስ አንጻር ከባድ ክስ ነበር የሚሉት ሠረቀ ብርሃን ገብረ እግዚእ ‹‹የክሱ መንፈስ፤ የሶቅራጥስ ነገር የሚታወቅ ነው፡፡ መንግስቱ እና ህዝቡ መስሏችሁ ታግሳችሁ ባቆያችሁት ነገር ሐተታ ማብዛት አያስፈልግም፤ ከማለት የሚቆጠር ክስ›› እንደ ነበር ይጠቅሳሉ፡፡ እውነትም ነገሩ በቋፍ የቆየ ስለነበር፤ የፈላስፋው መከሰስ  ከአስቸጋሪ ሰው የሚገላግል ሁነኛ ዘዴ ሆኖ ታየ፡፡ ስለዚህ ከሳሹ አኒቶስ ፓሊክራቲስ በተባለ የመናገር እና የመጻፍ ልዩ ችሎታ በነበረው ሰው የተነዘጋጀ የክስ ዝርዝር ይዞ ችሎት ቀረበ፡፡ ችሎቱም የአቴና ህዝብ በሙሉ የተገኘበት ይመስል ነበር፡፡

ለባለስልጣናቱ ብቻ ቀርቦ የነበረው ክስ በአደባባይ ተገልጦ ታወቀ፡፡ የክሱ ማብራሪያ የሆነው መርዘኛ ንግግር ከተሰማ በኋላ ተከሳሹ ሽማግሌ እንዲከላከል ተፈቀደለት፡፡ ነገር ግን ከፍ ያለ መንፈስ የሚሰማው ሶቅራጥስ፤ ከፍ ባለ የመንፈስ የሚመራ ስለሆነ፤ ከተራ ዝርዝር ሳይገባ በጠቅላላው በደለኛ አለመሆኑን ከተናገረ በኋላ ‹‹ለመከላከል የተፈቀደለትን ጊዜ ለመገሰጽ የተጠቀመበት መስሎት ሥጋዊ ህላዌውን ለማቆየት ሳያስብ በነቢይ የመንፈስ አለንጋ ተጋረፈበት፡፡ ሆኖም ቁጥራቸው 501 ከነበሩት አቴናውያን ዳኞች ውስጥ 220ው ነጻ ሲያወጡት 281 ጥፋተኛ ብለውት በ61 የድምጽ ብልጫ ይሙት በቃ ተፈረደበት፡፡››

ፈላስፋው የተወሰነበትን ፍርድ በእርጋታ ሰምቶ ብዙ እጅግ ኃይለኛ እና ጥልቅ ሐሳብን አሰምቶ፤ ‹‹………..እንግዲህ እኔ እንድሞት እናንተም ለመኖር መለያየታችን ነው………›› ብሎ ከተናገረ በኋላ የችሎት መልስ ሆኖ ወደ እስር ቤት ሲያመራ ፍርድ ቤቱ በመጥበቡ በውጭ ቆይተው የነበሩ ወዳጆቹ ተስፋ ቆርጠው ሲያለቅሱ፤ ‹‹…….ገና ስወለድ እንድሞት ከፍጥረት የተወሰነ እንደነበረ አታውቁምን……? ለምን ……ታለቅሳላችሁ ?›› በማለት ሊያጽናናቸው ተናገረ፡፡

ሶቅራጥስ በእስር ቤት ከገባ በኋላ፤ እንደቆየው ልማዱ፣ ሐሳቡ ሳይደክምና ከጥንት ንቃቱ ምንም ሳይቀነስበት ከወዳጆቹ እና ከተማሪዎቹ ጋር በመከራከር ማስተማሩን ሳያቋርጥ የፍርዱን ፍጻሜ ይጠብቅ ነበር፡፡ በመጨረሻም ወዳጆቹ እና ተማሮቹ ክሪቶን በተባለ ጥብቅ ወዳጁ አማላጅነት ከእስር እንዲጠፋ እና ከአቴና ርቆ እስከተወሰነለት ጊዜ ሥጋዊ መኖሩን እንዲያቆይ ሊረዱት በብዙ ደከሙ፡፡

ሶቅራጥስ የተጣለበት ፍርድ ያልተቀበለው እና ፍርዱም የተፈረደበት ሲነቅፈው በነበረ መንግስት ቢሆንም፤ በህግ የተወሰነበትን ፍርድ በአመጽ ለመሻር አልፈለገም፡፡ ህግ እና ስርዓት በኃይል ወይም በአመጽ እንዲደፈር እና እንዲፈርስ አልፈለገም፡፡

ህግን በአመጽ ለማፍረስ ህሊናው የማይፈቅድለት ሆኖ፤ በደልን በበደል ለመሻር መሞከር  ተገቢ አይደለም ብሎ ጸና፡፡ ህግን በኃይል (ህገ ወጥ በሆነ አካሄድ) በመጣስ መንቀሳቀስ እና የሐገርን ሥልጣን መጋፋት ከርኩሰት የሚቆጠር ተግባር መሆኑን ተቀብሎ ለፍርዱ መፈጸም ታመነ፡፡ ሶቅራጥስ ረቂቅ በሆነ እምነት ተመርቶ፤ የወዳጆቹን ሐዘን ወደ አመጽ የሚመራ እንጂ ትክክለኛ ሓሳብ የለበትም ሲል ነቅፎ ውድቅ አደረገው፡፡ ይህን ሲያደርግ ሐሳቡን በእምነት ጠብቆ ለመዝለቅ ሲል እንጂ ኑሮን በመሰልቸት ወይም በፈላስፋ ትዕቢት ተመርቶ እና ከሌሎቹ ሰዎች ተለይቶ ለመታወቅ አልነበረም፡፡

ሶቅራጥስ መንፈሳዊነትን እና የኅሊና ቅንንነትን፣ የጽድቅ እና የርትእን፤ እንዲሁም ሰናይ ምግባርን በተግባር ገንዘቡ ያደረገ ሰው ስለነበር፤ መንፈሱ የአመጻን ሐሳብ ሊቀበል የሚችል አልነበረም፡፡ ራሱ ‹‹የኃይል እና የአመጻ ሥራ›› የሚለውን ነገር አድርጎ ከማቸነፍ ይልቅ ግፍን መቀበልን ፈቀደ፡፡

በእርሱ እምነት የአንድ ማህበረሰብ ስርዓት እና ህግ፤ በውይይት በክርክር እና በመግባባት ሊሻሻሉ ይችላሉ እንጂ በኃይል እንዲፈርሱ ማሰብ አይገባም ባይ ነው፡፡ በዚህ መንገድ የሚሻር እና የሚለወጥ ህግ፤ በሰላም እና በስምምነት የሚደረግ  በመሆኑ ስልጣኔ ነው፡፡ ህዝብን ያስተባብራል፡፡ ያስማማል፣ ያሳድጋል፡፡ በኃይል የተለወጠ ነገር ግን ምንጩ አመጽ ነው፡፡ ስለዚህ በህዝብ ህሊና ፍርኃትን ያሳድራል፡፡ ተጠራጣሪ ያደርጋል፡፡ በምንም ነገር እምነት የሌላቸው እና ለማመንም የማይችሉ ያደርጋቸዋል፡፡ ጸጥታን ይነሳቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ህሊናቸው ስለሚደክም፤ ከዕለት ጉዳይ የሚበልጥ ነገር ለማሰብ ወይም ለመመኘት እንኳን የማይችሉ ያደርጋቸዋል፡፡ ሶቅራጥስ በእንዲህ ያለ እምነት የአዕምሮ ፍርድ ሓሳቡን ከስህተት የሚጠብቅ ሰው ነበር፡፡

ስለዚህ ቅር ሳይለው በሚነቅፈው መንግስት ፍርድ ቤት በተንኮል በተነሳሱ ሰዎች በተመሰረተበት ክስ የተጣለበትን ፍርድ ፍጻሜ እንዲሆን የሞትን መንገድ ተከተለ፡፡ ከክርስቶስ በፊት የኖረ ክርስቲያን የሚል ስም ያተረፈው ሶቅራጥስ በአዕምሮ ብርሃን ወደተለመከተው መንፈሳዊ ዓለም አለፈ፡፡ እንዲህ ባለ አሟሟት ፍጹም እምነትን እና እውነትን ገለጠ፡፡ የተከሰሰባቸውን ኃጢአቶች በአንደበት ሳይሆን በግብር አስተባበለ፡፡ ትክክለኛ ህግ አክባሪነቱ እስከ መጨረሻው ፍጹም እና ለወጣቶች ከፍ ያለ አብነት የሚሆን ሰው በመሆኑ፤ህግ ከመጣስ ይልቅ ልሙት በሚል አቋሙ ታየ፡፡ ‹‹ከጥቂት ዓመታት በኋላ አቴናውያን በሶቅራጥስ ላይ የተፈጸመውን ግፍ አወቁ፡፡ አዘኑ፡፡ የሰው ዘር በእውነት እንዲያምን ደም እና ሬሳን ማየት ይፈልጋል፡፡ ጸጸቱን ለመርሳት፣ ኅሊናውን ለማባበል የቻለ ሲመስለው ደግሞ ለበደላቸው ሰዎች ግፍ ላደረገባቸው ሰዎች ከድንጋይ ሐውልት አንጾ  ያቆምላቸዋል፡፡…… ይህም በየዘመናቱ የሚደጋገም፤ የእውነት መልዕክተኞች እና ምስክሮች እና የክፋት ባሮችም ታሪክ ነው፡፡›› ታዲያ የሐተታዬ የሞራል ታሪክ፤ ዴሞክራሲ እንዲህ ያለ እምነት የሚፈልግ ሆኖ ሳለ፤ አሁን በፖለቲካ ነጋዴዎች፣ በአሜሪካ በሚኖሩ አንዳንድ ግብረ ገብ እንኳን ያጡ ኢትዮጵያውያን ዋጋዋ ጠፍቷል የሚል ነው፡፡

Ethiopia is Burning the Midnight Oil




Amen Teferi
Whether western think-tanks or activists (like the Survival International, Oakland Institute and Rights Groups) like it or not, all the dams we plan to build on our rivers in the coming five years will, as expected, be materialized as per the schedule we have devised. Some international organizations like the Survival International who vowed and tread to suppress Africa’s development have adamantly been against the construction of the Gilgel Gibe III hydroelectric dam which the PM, Hailemariam Desalegn, had inaugurated on December 17, 2016. Now, Gibe III is a fact of life. However unpalatable it may be for some activists and think-tanks it may be, it must willy-nilly be accepted as a fact of life.
In point of fact, some western scholars and countries do want Africa to remain unchanged to serve them as a museum of backwardness. They have zealously barraged the Gilgel Gibe III project with wild and woolly accusations or nonsensical criticisms.
These Ill-devised tantrums or hypes were orchestrated to designedly misinform promising financers and consequently promote “their own” skewed self/business interests. Those pseudoscientific exercises and gibberish criticisms pertaining to the construction of the Gibe III dam were designedly aimed at instigating animosity between the two sisterly countries, Ethiopia and Kenya. Luckily, these notorious and beaten-up campaigns have finally turned out to be a futile venture and bore no fruit whatsoever. Instead, the pompous crusades have utterly failed to antagonize Ethiopia with its trustworthy neighbor -Kenya.
To our dismay, they have succeeded in concocting stories that had forced some financial organizations to shun from granting loan to the billion dollar mega project inaugurated on December 17, fortnight ago. Financial oligarchs like the African Development Bank (ADB), the European Investment Bank and other international financial institutions might have received the signals sent by these think-tanks and activists and lost interest in providing the necessary fund for the construction of the dam. Apparently, they did not appraise the project and got convinced that the construction of the Gilgel Gibe III dam would disrupt the livelihood local communities or significantly impact the environment. That was not the case at all, for Ethiopia usually unequivocally demonstrates its staunch commitment for environment. It had adopted a green economic policy and as the CNN has recently confirmed, “Ethiopia was among the most daring signatories to the Paris Agreement on climate change, committing to cut carbon emissions by 64% by 2030.” Truly that is the reason why, “the Ethiopian government has ploughed billions of dollars into hydropower megaprojects such as Grand Renaissance Dam which will be the largest dam in Africa ---and the freshly-inaugurated Gibe II Dam,” as the CNN had rightly noted this week.
As Ethiopia has unwaveringly committed itself to the cause of environment and has clearly demonstrated the justness of its position in the utilization of trans-boundary water, it would be very difficult to drive a wedge between the two countries, Kenya and Ethiopia and accuse Ethiopia on account of promoting its selfish without considering the rational and best interest of neighboring people of Kenya. However, some groups have tried to project their sinister motives by negatively representing Ethiopia’s motives in harnessing the Omo River. As an immediate reaction to these baseless allegations Ethiopia had invited Kenya to visit the project and thus removes the logjams and outmaneuvered its “arch-enemies.”   
Now, Ethiopia is burning the mid night oil to realize its renaissance. It is really working hard to accomplish the daunting task of removing the ugliest impacts and the adverse effects of extreme poverty. Poverty reduction, for Ethiopia, is a ground zero of all its projects. It is impatient to see the realization of this noble goal and is working well beyond the limits of its poor financial and implementing capacities witnessed by the daring undertakings of the mega projects like Renaissance Dam and Gilgel Gibe III.   
Therefore, we would be blown away on hearing news about the completion of a flagship dam project that has been listed in the black books of market fundamentalists and right groups who barraged and disparaged the Gibe III project and also as the late PM Meles Zenawi once said, “who want us to remain under developed and backward to serve their tourists as museum.”
Disgusted with these criticisms the Ethiopian government has shut the uproars of “the guards of poverty” with an unequivocal and succinct statement: “it would be finished at any cost.”
At any rate, it is as nice as pie and even uplifting, if you like, to hear bits of news about the superlative performance of Ethiopia in the economic sector. The unprecedented economic achievement in the last two decades has put Ethiopia on the map, as various international organizations are praising its progress. Economic reports from major media organization are now telling us that the bags and baggage of the Ethiopian economy replenished with blank checks of opportunities. It is, therefore, attracting giant foreign investors from all corners of the globe.
Following the inauguration of the Gilgel Gibe III dam, we had heard incredible news about the economic boom in Ethiopia. The Economist, on its Dec 21st 2016 issue, has commended the Gibe III dam for having “a capacity to double the country’s electricity output at the flick of a switch.”
In its latest report of Dec 21st, The Economist chose to be very laconic in the opening paragraph that tries to list some prominent accomplishments of the ruling party. The report rendered Ethiopian government as one that “likes to deal in superlatives” and goes on listing the superlatives as, “largest mass-housing program in Sub-Saharan Africa; its first metro; its biggest army and last week the ruling party Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) added another to the list: the tallest dam, i.e. Gibe III”
Ethiopia wishes to be a renewable-energy exporter in region and beyond. The Gibe III alone is expected to generate as much electricity as currently produced by the whole of neighboring Kenya, which has already signed up to buy some power from Gibe III. According to The Economist, “the export earnings will help to plug Ethiopia’s gaping current-account deficit   The export earnings will help to plug Ethiopia’s gaping current-account deficit, power will provide a timely fillip to its nascent manufacturing sector.” It is, therefore, attracting giant foreign investors from all corners of the globe.
On the other hand, the CNN in its latest report has said, “After a decade of rapid growth, Ethiopia’s bubble is not bursting.” I liked that statement. That is really a poetic – a riposte of metaphoric. It is a work of an ingenious writer whose figurative rendition is as new as foam and as old as a rock. It is a fantastic representation of the fanatic economic performance of Ethiopia for over a decade. One more quote from the CNN:

Dubbed the 'African Lion’ by economists, Ethiopia is the home of booming industry, new infrastructure, and showpiece summits. It has become a powerful force in the region and beyond. To maintain this golden age, the East African state is pressing ahead with ambitious development plans, and renewable energy is core to the mission.

In my view Ethiopia must also be dubbed as “shipwright for humanity and its civilization” for it vowed to pursue green economic policy that would be a safeguard to the mother earth that is being threatened by the outpouring of the sea water caused by the rising of the sea level. The melting sheets of the ice in the Antarctic region would inundate the major coastal cities of the world due to the global warming triggered by the greenhouse gas emission.
In fact, Ethiopia has virtually contributed nothing the global warming. However, it is among the most daring signatories to the Paris Agreement on climate change, committing to cut carbon emissions by 64% by 2030.  The government has pumped billions of dollars into hydropower megaprojects such as the Grand Renaissance Hydroelectric Dam which will be the largest dam in Africa. The freshly-inaugurated Gibe III Dam is one among the billions dollars project the country has undertaken.
The CNN has also regaled its reader with yet another lavish praise on Ethiopia with an admiring comment like Ethiopia’s “next target is to become the wind power capital of Africa.” Ethiopia has enormous potential for hydropower and geothermal energy generation. Several studies have so far been carried out to identify Ethiopia's energy potential and to develop short, medium and long-term investment plans for the power sector. The country's hydropower potential is estimated at 45,000 MW and the potential for generating electricity from geothermal is about 5,000 MW. The country is also endowed with enormous potentials of other renewable energy sources like solar and wind, particularly in rural areas. Despite such huge resources, the country has so far managed to utilize merely 2,000 MW of its power generating potential and only about 33 percent of the population has access to electricity, but it has planned to boost the electricity coverage of the country to 75 percent in the coming few years. Since the formulation of the last comprehensive power system expansion master plan, there is fundamental and unprecedented structural change that have taken place and Ethiopia’s economy is finding its driving force in the power sector.

Wednesday, 14 December 2016

‹‹የአክሱም ጫፍ አቁማዳ››




አሜን ተፈሪ
ገጣሚው ደበበ ሰይፉ፤ ‹‹ከአክሱም ጫፍ አቁማዳ›› ብሎ የሚጠራው አንድ ግጥም አለው፡፡ ይህ ግጥም እንደሚከተለው ይነበባል፤
እኔ እና ወንድሞቼ …. ሁላችን ሁላችን፤
ከባዶ አቁማዳ ነው እሚዛቅ ፍቅራችን፡፡
‹‹ከአክሱም ጫፍ አቁማዳ›› ከተሰኘው ግጥም የተወሰዱት፤ ከላይ የጠቀስኳቸው ሁለቱ የደበበ ስንኞች፤ የግጥሙ ዘውድ ወይም ኃይለ ቃል የሆኑ ስንኞች ናቸው፡፡ ግጥሙ ተራኪ ነው፡፡ የአንድ ወቅት ኢትዮጵያውያንን ፈተናኝ ይተርካል፡፡  በሐገሩ ረሃብ ገብቷል፡፡ በሐበሻ ጓዳ ሸረሪት አድርቶበታል፡፡ በአውድማው አይጥ ይፈነጭበታል፡፡ መሶብ እና ሌማቱ ግትቻ ሆኗል፡፡ ከጓዳ አንዲት ቅንጣት ጥሬ ጠፍቶ፤ የሐበሻ ቱቢት ተገምዶ፤ ቅስሙም አንገቱም ተሰብሮ፤ አንጀቱ በረሃብ ተፈርፍሮ፤ የሐበሻ የኑሮ መልካ ተናግቶ፤ ‹‹እባክህ አንድ ቁና ጤፍ አበድረኝ?›› ከሚል መልዕክት ጋር አንዲት አቁማዳ በምድረ ኢትዮጵያ ትዞራለች፡፡ ይህችን አቁማዳ ትግራይ - ለወሎ ላካት፤ ወሎ - ለሸዋ፤ ሸዋ - ለሐረር፤ ሐረር - ለባሌ ይልካታል፡፡
‹‹እባክህ አንድ ቁና ጤፍ አበድረኝ›› ብሎ አንዱ ለሌላው ይልክበታል፡፡ ሁሉም ‹‹የለኝም›› ማለት እያፈረ፤ ወገኑ ሲቸገር ለመርዳት አለመቻል ‹‹ባህሉን መንቀፍ›› ሆኖበት እየተቸገረ፤ ለተራበ ወገኑ እህል ለመላክ ያን አቁማዳ ‹‹እህል አበድረኝ›› እያለ፤ ችግሩን ውጦ ዝም ወዳለው ጎረቤቱ ይልከዋል፡፡ የራሱን ችግር ቻል - ዋጥ አድርጎ፤ ለወዳጁ ለዘመዱ ለወገኑ ሊደርስለት ይመኛል፡፡ ‹‹ኧረ በሞቴ … ይቺን ብቻ›› እያለ ያጎርሰው የነበረ ወገኑ፤ በልቶ የጠገበ ሳይመስለው ያስተናግደው የነበረ ያ ደግ ዘመዱ፤ ወዳጁ ክፉኛ መቸገሩን ሲሰማ በጣም አዝኖ፤ ከጎረቤቱ እህል ቢያገኝ፤ ተለቅቶ ሊልክለት አስቦ፤ በብቅ አቁማዳውን ይልካል፡፡
‹‹እባክህ አንድ ቁና ጤፍ አበድረኝ?›› ብሎ ትግራይ ለወሎ አቁማዳ ሲልክ፤ ወሎ ወደ ሸዋ ላከ፡፡ ሸዋ ለሐረር- ሐረር - ለባሌ፤ ባሌ- ለአርሲ፤ አርሲ - ለሲዳማ፤ ሲዳማም - ለጋሞ፤ ጋሞ - ለከፋ፤ ከፋ - ለኤሊባቡር፤ ሁሉም ኩራቱን ዘቅዝቆ፤ ሐፍረቱን ደብቆ በስውር አቁማዳውን ይልካል፡፡ ኢሉአባቦርም -ለወለጋ፤ ወለጋም -ለጎጃም፤ ጎጃምም - ለጎንደር፤ ለጎንደርም መልሶ ለትግራይ ላከለት ያች ባዶ አቁማዳ ድፍን ኢትዮጵያን ዞረች፡፡ ሁሉም ለጎረቤቱ፤ ‹‹እባክህ ላክልኝ አንድ ቁና ስንዴ፤ ልሞት ነው ተርቤ›› እያሉ የላኳት ያች አቁማዳ፤ ተመልሳ ትግራይ ገባች፡፡ ትግራይም አቁማዳውን አይቶ፤ የእርሱ አቁማዳ መሆኑን ተረድቶ፤ ለዚህ ድንቅ ፍቅር መታሰቢያ እንዲሆን፤ የፍቅራቸው አብነት አፈር እንዳይነካው፤ ክፋት እንዳያረክሰው፤ ለትውልድ መዘክር ይሆን ዘንድ ከአክሱም ሐውልት ጫፍ ሰቀለው፡፡   
እኔ እና ወንድሞቼ …. ሁላችን ሁላችን፤
ከባዶ አቁማዳ ነው እሚዛቅ ፍቅራችን፤ አለ፡፡
የኢትዮጵያ ህዝቦች እንዲህ ናቸው፡፡ ዛሬ ያች ባዶ አቁማዳ መሙላት ጀምራለች፡፡ በተስፋዋም ታጠግባለች፡፡ ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝቦች ‹‹ባዶ አቁማዳ›› ይዘው አይዞሩም፡፡ ዛሬ ‹‹የፍቅር ጽዋ›› መሥርተው፤ የህብረት ጀማ አበጅተው፤ በዓመት አንድ ቀን ህዳር 29 ከባለ ‹‹ወር ተራው›› ወይም ‹‹ከባለ ዓመቱ›› ቤት ይገናኛሉ፡፡ ‹‹እኛ የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በሐገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ዘላቂ ሰላም፤ ዋስትና ያለው ዴሞክራሲ እንዲሰፍን፤ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ዕድገታችን እንዲፋጠን፤ የራሳችንን ዕድል፤ በራሳችን የመወሰን መብታችንን፤ ተጠቅመን በነጻ ፍላጎታችን፤ በህግ የበላይነት እና በራሳችን ፈቃድ ላይ የተመሠረተ፤ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ በጋራ ለመገንባት፤ ቆርጠን በመነሳት፤ ኢትዮጵያ ሐገራችን….በተለያዩ መስኮችና የግንኙነት ደረጃዎች ተሳስረን አብረን የኖርንባት እና የምንኖርባት ሐገር በመሆኗ፤ ያፈራነው የጋራ ጥቅም እና አመለካከት አለን ብለን ስለምናምን፤ …አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ የመገንባቱን አስፈላጊነት በማመን፤ ከላይ ለገለጽናቸው ዓላማዎች እና እምነቶች ማሰሪያ እንዲሆነን…..ዛሬ ኅዳር 29 ቀን 1987 ዓ.ም ይህን ህገ መንግስት አጽድቀነዋል›› ብለው በአዲስ ጎዳና የህብረት እና የአንድነት፤ የልማት እና የዴሞክራሲ ግንባታ ጎዳና ጉዞውን ጀምረው ለ22 ዓመታት በዚሁ ቀና መንገድ ተጉዘው ከዚህ ደርሰዋል፡፡  
የኢትዮጵያ ህዝብ በክፉ ቀንም ፍቅራቸው የጸና ነበር፡፡ እንኳን ዛሬ ከረፉ የፖለቲካ ስርዓት ውስጥ ሲኖሩ ሳለ ‹‹ከባዶ አቁማዳ›› ፍቅር እየዛቁ በአንድነት ኖረዋል፡፡ ይህ ነገር ከውጭ ሆኖ እኛን ለሚመለከት ሁሉ ግራ አጋቢ ቢሆንም፤ ኢትዮጵያውያን ሐገራቸውን የሚደፍር የውጭ ጠላት ሲመጣ የውስጥ ችግራቸውን ወደ ጎን አድርገው በአንድነት ተሰልፈው ሐገራቸውን ለዘመናት ከጠላት ጥቃት ጠብቀው፤ በነጻነት ኮርተው ኖረዋል፡፡
አሁን ሁኔታችን በእጅጉ ተለውጧል፡፡ ባዶው አቁማዳችን በተስፋ መሙላት ጀምሯል፡፡ እኔ በጣም መለወጣችንን ለመረዳት የሚያስችል አንድ የቅርብ ጊዜ ገጠመኝ አለኝ፡፡ ይህ ገጠመኝ ለመስክ ሥራ በወጣሁበት አጋጣሚ የተፈጠረ ነበር፡፡ ከእኔ ጋር ለሥራ የወጣና በፌዴራላዊት ኢትየጵያ በተቀተጸ ስርዓተ ትምህርት ውስጥ ያለፈ አንድ ወጣት የለውጡ ጎዳና ምን እንደሚመስል ለመገንዘብ የሚያግዝ ሁኔታ ፈጠልኝ፡፡
ወጣቱ የፌዴራላዊት ኢትየጵያ ፍሬ ነው፡፡ ከእኔ ትውልድ የተለየ ቋንቋ አለው፡፡ ከልጆቼ የመማሪያ መጽሐፍ የማውቃቸውን አንዳንድ የትምህርት ቃላትን ሲጠቀም፤ እኔ እርሱ በተለያዩ ስርዓተ ትምህርቶች ማህጸን የተወለድን መሆኑ ገባኝ፡፡ በልጆቼ የመማሪያ መጽሐፍ የማውቃቸውን ‹‹እፍግታ፣ ምድገት፣ ልይ ዘር፤ ዋህድ ዘር፣ ነጥበ ፍሌት፣ ነጥበ ብርደት›› የሚሉ ቃላትን ይጠቀማል፡፡ ከእኔ የተለየ የትምህርት ቤት ህይወት ትውስታ አለው፡፡ በእርሱ የብሔር ብሔረሰብ ቀን አከባበር ልዩ ትርጉም አለው፡፡ በእርሱ የትምህርት ቤት ህይወት ውስጥ የብሔር ብሔረሰብ ቀን ክብረ በዓል፤ በደስታ የሚጠቀስ ትውስታ ነው፡፡
‹‹የብሔር ብሔረሰብ ቀን ስናከብር .…›› እያለ አንዳንድ ገጠመኞቹ ሲያወራልኝ፤ ክብረ በዓሉ የህይወት ዘመኑ ጌጥ መሆኑን አወቅኩ፡፡ በርግጥ የብሔር ብሔረሰብ ቀንን ልጆቼ ምን ያህል በናፍቆት እንደሚጠብቁት አውቃለሁ፡፡ ተማሪዎች በየዓመቱ የተለያዩ የብሔር ብሔረሰቦችን ባህላዊ አለባበስ ለብሶ የመሄድ ጉጉት እንዳላቸውም አውቃለሁ፡፡ ሆኖም የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ለአዲሱ ትውልድ የተለየ ስሜት እንደሚሰጠው በውል የተረዳሁት ከወጣቱ በሰማሁት ጨዋታ ነው፡፡ ምናልባት፤ ክበረ በዓሉ ጨፍሮ የመመለስ ከንቱ ሥራ መስሎ የሚታያቸው ሰዎች ምን ያህል እንደተሳሳቱ ሊያስረዳ የሚችል ነው፡፡ የብሔር ብሔረሰብ ቀን፤ አዲሲቱ ኢትዮጵያ የምትሰራበት አንድ ግብዓት ሆኗል፡፡
ፌዴራላዊው የሚገርም ነው፡፡ ልጄ ቤተ መጻሕፍት ገብታ የምታደረገው ነገር በወቅቱ ብዙም ትርጉም ሳይሰጠኝ አልፎ ነበር፡፡ አሁን ወጣቱ በተከፈተልኝ አዲስ የዕይታ መስኮት ነገሩን ስመለከተው፤ ዓይን ገላጭ ተዐምር አድርጌ አየሁት፡፡ በወቅቱ ብዙም ትርጉም ያልሰጠኝ ድርጊቷ፤ አሁን ልዩ ትርጉም ይዞ ታየኝ፡፡ ሐገራችን ከመሠረቱ መለወጧን አበሰረኝ፡፡ ሥነ ዜጋ እየተማረ፤ ስለ ዴሞክራሲያዊ እና ሰብአዊ መብቶች እያሰበ እና እየተወያየ የሚያድገው ይህ ትውልድ የሐገሪቱ የተስፋ ቡቃያ ነው፡፡ ልጄ ስነ ዜጋ ስታጠና ‹‹የህጎች ሁሉ የበላይ የሆነ ህግ›› እያለች ለምትጠቅሰውና ቤተ መጻህፍት ገብታ ተንደርድራ  ለምትገልጠው የሀገራችን ህገ መንግስት ልዩ ስሜት ይዛ እንደምታግ አሰብኩ፡፡ ልጆቻችን ከእኛ ዘመን በብዙ በተለየ የሥነ ምግባር እሴቶች ታንጸው እያደጉ ነው፡፡ የሐገራችን ተስፋ እነዚህ ናቸው፡፡ እንደ ተረት የልጅነት ህልማቸውን እያቀለመ የኖረውን ይህን ህገ መንግስት በደንብ ለመጠበቅ የሚያስችል የህይወት ልምድ ይኖራቸዋል፡፡ ስለዚህ ‹‹ህገ መንግስቱ የጸደቀው አሁን ነው›› አልኩ፡፡
እንደ ብዙዎቹ ልጆች፤ የእኔም ልጆች ስለብሔር ብሔረሰቦች ቀን የሚያስቡት፤ ከህዳር 29 15 ቀን አስቀድመው ነው፡፡ በዚሁ ሰሞን በሌሎች ብሔሮች ቋንቋ ‹‹እንኳን አደረሳችሁ›› ለማለት ሲሞክሩ አይቻለሁ፡፡ ቃሉን ከሰው ጠይቀው፤ በትምህርት ቤት በሰልፍ ላይ ወጥተው ይናገራሉ፡፡ ይህ ነገር መኖሩን የተረዳሁት፤ ከትምህርት ቤት ሲመለሱ፤ ‹‹ሀሹ ሰሮ ገቴብ….›› እያሉ ደጋግመው ሲያወሩ በማየቴ ጥያቄ አቅርቤ ባገኘሁት መልስ ነው፡፡ ምን እያላችሁ ነው? አልኳቸው፡፡ ‹‹እንኳን በሰላም አደረሳችሁ ማለት ነው›› አሉኝ፡፡ በምን ቋንቋ እንደሆነ ጠየቅኳቸው፡፡ ወላይትኛ መሆኑን ነገሩኝ፡፡ ሌሎች የማላስታውሳቸውን ነገሮችም ብለዋል፡፡ ግን እኔ ማስታወስ የቻልኩት ከላይ የጠቀስኩትን ቃል ብቻ ነው፡፡
ልጆቻችን ከእኛ የተለዩ ሆነዋል፡፡ ከተዛባ አመለካከት ተጠብቀው አድገዋል፡፡ ከሐገሪቱ ልዩ ልዩ ብሔር ብሔረሰቦች ጋር ከልጅነታቸው ጀምረው ተዋውቀው ስለሚያድጉ፤ ሥነ ልቦናቸው በአንድነት ስሜት የታነጸ ይሆናል፡፡ በእውነት ልጆቻችን ይበልጡናል፡፡ ከእኛ ከወላጆቻቸው በተለየ የአስተሳሰብ ዘዬ እያደጉ ነው፡፡ ከፊውዳላዊ እሴቶች እና ከአብዮት እብደቶች ተጠብቀው፤ በዴሞክራሲያዊ እሴቶች ታንጸው ማየት ደስታ ነው፡፡ ልጆቻችን በፌዴራላዊ ስርዓታችን ከሚስተዋሉ አንዳንድ መጥፎ አዝማሚያዎች እና ጉድለቶች ተጠብቀው እንዲያድጉ መሥራት ይኖርብናል፡፡ እግሮቹን በቶሎ ማረም ይገባናል፡፡ ከትናንት የተሻገሩ መጥፎ ጸረ- ዴሞክራሲያዊ እሴቶች እና ባህሎች ወደ ልጆቻችን እንዳያልፉ መትጋት ያስፈልገናል፡፡ ይህን ካደረግን፤ በእውነት የሐገራች መጻዒ ጊዜ በጣም ብሩህ ይሆናል፡፡ እነዚህ ክቡር ፌደራላዊ እሴቶች፤ ወላጆቻችን ባወረሱን ድንቅ የታሪክ ቅርስ መደብ ላይ ሲያድጉ የሚፈጠረው ነገር ያስደስታል፡፡
ወላጆቻችንን ‹‹ከባዶ አቁማዳ የሚዛቅ ፍቅር›› አውርሰውናል፡፡ አኩሪ የነጻነት ተጋድሎ ታሪክም ሰጥተውናል፡፡ ይህን የሐገራችንን ህዝብ ልዩ እሴት ስዜስታሎው ጀስማን[1] (CZESTLAW JEŚMAN) የተባለ አንድ አጥኚ በደንብ እንዳስተውለው አድርጎኛል፡፡  ጀስማን ጥናት የታተመ እኤአ በ1968 ነው፡፡ ‹‹ ETHIOPIA: A TEST CASE OF RACIAL INTEGRATION›› በሚል ርዕስ የቀረበው ጥናት ነው፡፡
ኢትዮጵያ ‹‹በይነ ብሔራዊ›› (RACIAL INTEGRATION) ግንኙነት ወይም ዝምድና የመመሥረት እና የማጽናት ልዩ ችሎታ ያላት ሐገር መሆኗን የሚጠቅሰው ፀሐፊ፤ ‹‹የተለያየ የዘር ሐረግ ያላቸው ሰዎች በአንድ የፖለቲካ ስርዓት አብረው በሚኖሩበት ጊዜ ሊፈጠር የሚችለውን አስቸጋሪ ሁኔታ ለመቋቋም ብቃት ያላትና ለሌሎች ሐገራት ምሣሌ የምትሆን ሐገር መሆኗን ይጠቅሳል፡፡ ብዝሃነት ያላቸው ህዝቦች አብሮ ለመኖር የሚያስችል አውድ ለመፍጠር ሞዴል ሆኖ ሊያገለግል ይችላል›› ይላል -- ጀስማን፡፡ የእርሱን ነገር በዚህ ጽሑፍ ለማየት አልሻም፡፡ ሆኖም ‹‹እነዚህ ሰዎች ይህን ሁሉ ልዩነት አቻችለው በሰላም ለመኖር የቻሉት እንዴት ነው?›› የሚል ጥያቄ የሚያስነሳ የአብሮ መኖር ቅርስ ያለን ህዝቦች ነን፡፡ ቅኝ ገዢዎች፤ ቅኝ ግዛታቸው ለማጽና ሲሉ የኢትዮጵያውያንን ጉዳይ ይመረምሩ ነበር፡፡ ሩሲያም ሰው ልካ የኢትዮጵያን ሁኔታ ታስጠና እንደነበር ጀስማን ይጠቅሳል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በህገ መንግስታቸው ‹‹…. ኢትዮጵያ ሐገራችን በተለያዩ መስኮችና የግንኙነት ደረጃዎች ተሳስረን አብረን የኖርንባት እና የምንኖርባት ሐገር በመሆኗ፤ ያፈራነው የጋራ ጥቅም እና አመለካከት አለን›› የሚሉት ይህንኑ ነገር ነው፡፡


[1] Source: Africa: Rivista trimestrale di studi e documentazione dell’Istituto italiano per l’Africa e l Oriente, Anno 23, No. 4 (DICEMBRE 1968), pp. 471-498